ሰላማዊነት
አንድ ሰው በአለማዊ ኑሮውም/ስራም ሆነ በመንፈሳዊ አገልግሎቱ ወሬ መስማት ሲጀምር ደረጃ አንድ ውድቀት ይወድቃል፡፡ በCOC ሕግ ደረጃ አንድ የወደቀ ሰው ቀጣዪን ደረጃ መማር እንደማይቸችል ሁሉ በወሬ የሚያምን ሰው የመስቀልን ጉዞ ሊይዝ አይችልም፡፡ በራስ መተማመኑ እየጠፋ መርማሪ፣አጣሪ መሆኑ ቀርቶ ተመርማሪ እና በሌሎች ላይ የሚደገፍ ይሆናል፡፡ መጨረሻው ላይ እርሱ ራሱ ወረኛ ሆኖ ቁጭ ይላል፡፡ ወረኛ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሊፈጽምም ሆነ ልያስፈጽም አይችልም፤ልክ የክርስቶስን አምላክነት በአይሁድ ዘንድ እንዳስካደ፣የሐውርያትን ልብ የፈተነ (ሉቃስ እና ቀለዮጳ-የኤማዉስ መንገደኞች)፣ዛሬም በአለም ዘንድ እንዳይረዳ ያደረገ ክፉ ወሬ፡፡ ለመሆኑ የእግዚአብሔርን እንስማ ወይስ የሰይጣን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ወሬኛ ቦታ የለውም ልክ ወሬኛው የሳዖልን ሞት ለዳዊት በነገረው ጊዜ ዳዊት እንዳስገደለው ወረኛ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረ 2ጢሞ. 3፡1-5 በመጨረሻው ዘመን የሚመጡ ሰዎች ሐሜተኞች/ወረኞች-ስለ ሰው ማውራት እንጂ ስራ የማይሰሩ፣የማያገለግሉ፤ለስብሰባ እንጂ ስራ አገልግሎት ላይ የማይገኙ፣ሀሳብ የመሰንዘር ብቃት እንጂ ተግባር ላይ የማይገኙ ይሆናሉ…… ለመሆኑ እኛ ከማን ወገን ነን ከወረኞች ወይ ከተቀባዮች፡፡ወረኛን ማመን ልክ አዳም እና ሔዋን በገነት እያሉ የእግዚአብሔርን ትተው የሰይጣንን ምክር እንደሰሙ፤የመጀመሪያውን ሀሳብ ትተው አድስ ሀሳብ እንደተቀበሉ ነው፡፡ ሀሰትን ተከትለው እውነትን ሳይፈልጉ ከሰሩ፣ሞት የሚባል እንግዳ ነገር ወደ ምድር አመጡ፡፡ ወረኛ ሆይ ከእግዚአብሔር ነህ ወይስ ከሰይጣን? መረጃ ማቀበል እና ወሬ ማቀበል አንድ ይመስልሃል? መረጃ ካቀበልክ ሀገርን፣ወገንን፣ህዝብን፣ቤተክርስቲያንን፣ማኅበርን ታደግህ ነገር ግን በወሬ እነኚን ሁሉ አበላሸህ፡፡ ለዚ...