አማርኛ
የአማርኛ ፊደላት (ሆሄያት) ፀጋዎች * በዚህ ዓለም ስለራስህ ከአንተ በላይ የሚያውቅ የለም! - ከድሮ አስተሳሰብ ጋር ተቸንክረው የቀሩ ቆሞ ቀሮች፦ 'ስለራስህ ሰዎች ይናገሩልህ እንጂ አንተ ዝም በል' አይነት ይትበሀል እያስፋፉ፤ አባባሉ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ ተንሰራፍቷል። ሆኖም በአፍአዊ ደረጃ (ስለአንተ ሰው ይናገር) በሰፊው ቢናኝም፤ በተግባር ሲገለጥ በእያንዳንዱ ሰው ንግግር ውስጥ 'ከእኛ' ይልቅ 'እኔ' ጎልቶ መውጣቱ፤ ተቀባይነቱን ብላሽ/ ፉርሽ ያደርገዋል። በእርግጥም 'ሰዎች ስለአንተ ይናገሩልህ' የሚለው አገላለፅ ትህትናን ያዘለ ቢመስልም ስሁትና የሰዎችን ግለ _ ታሪክ የመቅበር አሉታዊ አቅሙ ከፍተኛ ነው። * ማነው ከአንተ ጋር ከልጅነትህ ጀምሮ አብሮ የተንከራተተ? * ማነው ከአንተ ጋር አቀበት ቧጥጦ ቁልቁለት ወርዶ የተፍገመገመ? * ማነው በውስጥህ ያመቅኸውን ዕንባና ሰቆቃ _ ብሶትና ምሬት የተጋራ? * ለምሳሌ፦ እንደ Misbah Kedir በወያኔ እስር ቤት አሳር ፍዳህን ስታይ፤ ማነው ከአንተ ጋር 'ቶርቸሩን' የቀመሰ? ማነው እንደ አንዷለም አራጌ በእስር ቤት ውስጥ አብሮህ ፊቱ የከሰለ? እኮ ማነው ስላንተ ከአንተ በላይ ምስክር? * ራስህን ካልወደድህ እመነኝ ቤተሰብህን ሀገርህንም ሆነ የሰውን ዘር አትወድም። (በራስ ወዳድነትና ራስን በመውደድ መሀከል ሰፊ ልዩነት አለ።) በእኔ ምልከታ ሰዎች ከበርካታ መልካም ሥራዎችህ መሀከል መጥፎውን መዞ የማጉላት ባህሪ ስለተጠናወታቸው ስላንተ እንዲናገሩልህ መጠበቅ፤ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ዐይን የሌለው ጥቁር ድመት የመፈለግ ያህል አዳጋች ይመስለኛል። በተቻለ አቅም ለህሊናህና ለፈጣሪህ ታማኝ ሁን እንጂ ስለአንተማ ተናገር! አንድ መሥሪያ ቤ...