ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!"
➊."ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!" : ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው፤ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር፤ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም። : ➋.የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነት አይገልፅም! ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው፤ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል፤ ለሁሉም ጊዜ አለውና ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና። : ➌.መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል! : ጊዜህ ሲደርስ መኪናዎች ወይም ‘አውሮፕላን’ ትገዛለህ ፣ ያውም ለመኖር አስፈላጊ ከሆነ ፣ ደግሞስ እንዴት እንደገዛው የት ታውቃለህ? እርሱን ተወውና በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው። : ➍."ለሰዎች ለደስታቸው እንጂ ለሀዘናቸው መንስዔ አትሁን!" : ►በሰዎች ደስታ→ደስ ይበልህ! : ►ለሰዎች→ክፉ አትመኝ፣ ፡ ►በሃዘናቸውም→አብረህ እዘን፣ ፡ ►ሰዎች ሲያዝኑ→አትደሰት፣ ፡ ►ሰው ከሆንክ→የሰው ነገር ይሰማህ፣ ፡ ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ጋር ተደሰት ማለት አይደለም። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋ ሁን፣ አስተውል። : ➎."በጊዜ ስራ እንጂ ጊዜ ባንተ ላይ አይስራ!" ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም። አንተንም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት፤ በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን። ➏. "መክሊትህን ፈልግ!" ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁና። አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለም እየኖረች ያለችው። በጣ...