ልጥፎች

ልጥፎችን ከመለያ Ethiopia ጋር በማሳየት ላይ

አይ አሜሪካ

ምስል
#አይ_አሜሪካ  #ከምርጫ_በኋላ_በኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ውይይት_እንዲደረግ_አሜሪካ ጥሪ_አቀረበች  ambachewmu3.blogspot.com  የኢትዮጵያን የወደፊት አካሔድ ለመወሰን እና የአገሪቱን ዴሞክራሲና ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመሩት መንግሥት እና መላ ኢትዮጵያውያን ከምርጫ በኋላ ለሚካሔድ አካታች የፖለቲካ ብሔራዊ ውይይት ቁርጠኛ እንዲሆኑ አሜሪካ ጥሪ አቀረበች። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሚመሩት የአሜሪካ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለሠራተኞቹ ጥረቶች እውቅና ቢሰጥም፤ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የሚካሔድበት ከባቢ“አሳሳቢ ነው” ብሏል።  የአሜሪካ መንግስትን አቋም የሚያንጸባርቀው መግለጫ ዛሬ አርብ ሰኔ 4፤ 2013 የወጣው፤ አንቶኒ ብሊንከን በሚመሩት የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በኩል ነው። መግለጫው መጪው የኢትዮጵያ ምርጫ አሉበት ያላቸውን ፈተናዎች ዘርዝሮ ሥጋቱን ገልጿል። “የተቃዋሚ ፖለቲከኞች እስር፣ የገለልተኛ ሚዲያ መዋከብ፣ የአካባቢያዊ እና ክልላዊ መንግሥታት ወገንተኝነት እንዲሁም በመላ ኢትዮጵያ በብሔሮች እና በማህበረሰቦች መካከል የተቀሰቀሱ ግጭቶች ለነፃ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንቅፋት ናቸው” ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ ያትታል።  በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ስም ይፋ የሆነው መግለጫ የዘረዘራቸው ጉዳዮች፤ ኢትዮጵያውያን ምርጫውን ተዓማኒ አድርገው እንዳይቀበሉት ሊያደርግ እንደሚችልም ጠቁሟል። መግለጫው እንደሚለው “በጸጥታ ጉዳይ እና በመፈናቀል ምክንያት በርካታ የመራጭ ክፍሎች እንዳይሳተፉ መደረጋቸው በተለይ አሳሳቢ ነው።” መግለጫው ፖለቲከኞች እና የማሕበረሰብ መሪዎች ኹከትን እንዲያስወግዱ እና ሌሎችንም ከማነሳሳት እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል። ሁሉም የፖለቲካ ተ