ልጥፎች

ከኦክቶበር, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

Background Information on Ethiopia

ምስል
Background Information on Ethiopia Ethiopia has many diverse topographical, climatic, linguistic, and religious  features. Geographically, Ethiopia is located within the hot zone. Its southern tip is only  30 degrees north of the equator. However, due to its high altitude, the country has a  predominantly moderate climate with an average temperature in its vast central highland  plateaus no more than 20°C (68°F). The Great East African Rift Valley traverses the  central highland plateau into the north-west and south-east highlands. The majority of  the population lives in scattered villages in the highlands as farmers and pastoralists. The  three popular indigenous foodstuff plants, teff (Eragrostis teff), nug (Guizotia  abyssinica), and enset (Edulis edule) have been cultivated since at least the 5th  millennium BC (Pankhurst, 2005, p. 13).The highlands are surrounded by lowlands, the  largest part of which lies on the south-eastern side adjacent to Somalia. The Ethiopian  Rift Valley

ኢትዮጵያ_ባንተ_አልተጀመረችም_ባንተ_አትፈርስም

ምስል
#ኢትዮጵያ_ባንተ_አልተጀመረችም_ባንተ_አትፈርስም  ኢትዮጵያ ጉደኛና ታምረኛ ሀገር ናት !! ***************** * ኢትዮጵያን እንቀብራታለን ያሉትን ኢትዮጵያ ቀድማ ቀብራቸዋለች ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን ያሉትን ኢትዮጵያ ቀድማ አፍርሳቸዋለች በኢትዮጵያ ላይ ችግር ፣ሰቆቃ፣ማዕበል እናመጣለን ያሉትን ፈጣሪዋ ቀድሞ ለእነርሱ ያደርግባቸዋል ኢትዮጵያን እናበረክካለን ያሉትን ሁሉ ፈጣሪዋ ሰው ያስነሳና እንደገና እነርሱን ያንበረክካቸዋል አበቃላት ፣ ሞተች ፣ ፈረሰች ፣ አለቀች ፣ ደቀቀች ፣ተያች፣ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ገባች ስትባል እርሷ ግን እንደገና እያደር እያበበች ትሔዳለች በቃ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ጉደኛና ታምረኛ ሀገር መሆኗን ሁሉም አውቋል።< ኢትዮጵያ አትፈርስም።> ሃገር ሲፈርስ እንደ ድንጋይ ካብ ሲናድ የሚታይ ለሚመስለው ግምቱ ፖለቲከኛ ነኝ ባይ ኢትዮጵያ አልፈረሰችም።  #Ethiopia_not_be_in_you Ethiopia is a friendly and wonderful country !! ***************** * Ethiopia has already buried those who say they will bury Ethiopia Ethiopia has already destroyed those who say they will destroy Ethiopia The Creator will first bring trouble, misery, and storm to Ethiopia The Creator will resurrect all those who claim to bring Ethiopia to their knees and bring them to their knees again Ethiopia is now a friendly and wonderful country. Everyone knows. "Ethiopia

የሕወሐት የክህደት ጦርነት፣ ከጽንሰት እስከ እርጅና

ምስል
የሕወሐት የክህደት ጦርነት፣ ከጽንሰት እስከ እርጅና (ለውይይት የቀረበ ሰነድ) ሰላምሁን አየለ የነገሩ መነሻ -፩ ሕወሐት ለ27 ዓመታት የኢትዮጵያን ፖለቲካና ኢኮኖሚ በበላይነት ሲዘውር ነበር፡፡ በዚህ ዘመኑም አልፎ አልፎ የኢኮኖሚ ዕድገትና የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ታይቷል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ኢፍትሐዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል፣ የአንድ አካባቢ ሰዎች የበላይነት፣ የዴሞክራሲ መቀጨጭ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና የኢትዮጵያን አንድነት የማዳከም ሥራ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ይህ ሁኔታ እየከፋ በመምጣቱ በኢሕአዴግ ውስጥ በተደረገ ትግል እና በሕዝባዊ ተቃውሞ የሕወሐት የበላይነት ዘመን አክትሟል፡፡ የሕወሐትም ዕጣ ፈንታ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት በውድድር ብቻ የሚወሰን ሆኗል፡፡ ማንም የበላይ ወይም የበታች ሆኖ የሚኖርበት የፖለቲካ ምኅዳርም ተዘግቷል፡፡ ‹የበላይ ሆኖ የኖረ እኩልነት ውርደት ይመስለዋል› እንደሚባለው ከሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ጋር በእኩል ሜዳ መወዳደርን ሕወሐት ለመቀበል አልወደደም፡፡ በዚህም የተነሣ ወደ ቀደመ የሽፍትነት ጠባዩ ተመለሰ፡፡ የሕወሐት መዛግብት እንደሚያሳዩት በቀደመው የሽፍትነት ዘመኑ የገዛ ጓዶቹን መግደል፤ ሕዝብን በጠላትነት መፈረጅ፣ ንኡስ የገዥ መደብን በፓርቲ ውስጥ መፍጠር፤ ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ችግርን ለፖለቲካ ስሕበት መጠቀም ዋነኛ የትግል መንገዶቹ ነበሩ፡፡ የነገሩ መነሻ - ፪ ሕወሐት በዘመኑ የነበረውን የዓለም የፖለቲካ ለውጥ ተጠቅሞ ወደ ሥልጣን ሲመጣ በሁለት እግሩ እያነከሰ ነበር፡፡ በአንድ እግሩ ኢትዮጵያን ለመግዛት፣ በሌላ እግሩ ደግሞ በትግራይ ውስጥ ያለውን አካባቢያዊ ገዥነት ላለመልቀቅ ይታገል ነበር፡፡ ነገ የኢትዮጵያ ሕዝብ ገዥነቱን ባይቀበለው ወደ ደደቢት ተመልሶ በሽፍትነቱ ለማሰብ ዐቅዶ ነው የመጣው፡፡ ልክ ሲያገቡ ስለ ፍቺው

ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!"

ምስል
➊."ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!" : ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው፤ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር፤ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም። : ➋.የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነት አይገልፅም! ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው፤ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል፤ ለሁሉም ጊዜ አለውና ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና። : ➌.መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል! : ጊዜህ ሲደርስ መኪናዎች ወይም ‘አውሮፕላን’ ትገዛለህ ፣ ያውም ለመኖር አስፈላጊ ከሆነ ፣ ደግሞስ እንዴት እንደገዛው የት ታውቃለህ? እርሱን ተወውና በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው። : ➍."ለሰዎች ለደስታቸው እንጂ ለሀዘናቸው መንስዔ አትሁን!" : ►በሰዎች ደስታ→ደስ ይበልህ! : ►ለሰዎች→ክፉ አትመኝ፣ ፡ ►በሃዘናቸውም→አብረህ እዘን፣ ፡ ►ሰዎች ሲያዝኑ→አትደሰት፣ ፡ ►ሰው ከሆንክ→የሰው ነገር ይሰማህ፣ ፡ ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ጋር ተደሰት ማለት አይደለም። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋ ሁን፣ አስተውል። : ➎."በጊዜ ስራ እንጂ ጊዜ ባንተ ላይ አይስራ!" ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም። አንተንም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት፤ በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን። ➏. "መክሊትህን ፈልግ!" ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁና። አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለም እየኖረች ያለችው። በጣ

እጅግ በጣም የሳትነው ብዙ ነገር አለ።

ምስል
እጅግ በጣም የሳትነው ብዙ ነገር አለ። እነዛ የሶሻሊዝምን ጽንሰ-ሃሳብ በውል ያልተረዱ፣ ጺማቸውንና ጠጉራቸውን የሚያሳድጉ የ60'ዎቹ ተማሪዎች "ማርክስ እንዳለው …፣ ኤንግልስ እንዳለው…፣ ሌኒን እንዳለው …፣ ማኦ እንዳለው …፣ ቼጉቬራ እንዳለው…፣ ሆቺሚኒ እንዳለው…፣ እስታሊን    እንዳለው…፣ " ወዘተ እያሉ ታሪካችና እሴቶቻችን እንዲጠለሽ አድርገዋል። Twitter  የ60'ዎቹ ትውልድ ባህሉን፣ ወጉን፣ ሥርዓቱን፣ ሥነ-ጽሑፉን፣ ታሪኩን ጭምር ነቅፎ በባዶ እጁ ነው የሸፈተው። ከቆዳ ቀለማቸው በስተቀር የኢትዮጵያዊነትን ነባር እሴት፣ ባህል፣ ወግ፣ ታሪክ... ፍቀው የነማርክስንና የነስታሊን ፍልስፍና ይዘው ነው የሸፈቱት። መፍትሔው እግዚአብሔርን መካድ የመሰለው ማርክሲዝምን ርዕዮተ ዓለም አድርጎ የተነሣው የሶሻሊስት አቀንቃኝና የብሔር ፖለቲካን ቀይጦ የያዘው ወጣት የኢትዮጵያዊነት አስኳል ከውስጣቸው አውጥተው ጣሉት። በአጉል ማርክሳዊ-ሌኒናዊነት እግዚአብሔር-አልባ አደረጋቸው። ትውልዱንም ሳይቀራረብ የሚተያይ፣ በማያውቀው ታሪክ ተተብትቦ ወደኋላ እንጂ ወደፊት መራመድ የማይችል፣ ባዕድን እንደ ዘመድ፤ ዘመድን እንደ ባዕድ የሚመለከት ሽባ ትውልድ አደረጉት። እንጥፍጣፊ ሳያስቀር የኩራቱንና የክብሩን ካባ አውልቆ ጣለው፣ ኢትዮጵያዊነትን በአፍጢሙ ደፋው፣ የመንፈስ ኃይሉ ደቀቀ፣ በመጨረሻም አንገቱን ደፋ፣ ችግሩንም ሁሉ ለመፍታት የፈረንጆችን እርዳታ የሚፈልግ ትውልድ ተፈጠረ። ቀጥሎስ.....ቀጥሎ ደግሞ የኢትዮጵያ እደ ጥበብ ሠራተኞችን፦ ለምሳሌ ብረት ሰሪዎችን "ቀጥቃጭ"፣ ልብስ ሰሪዎችን "ሸማኔ"፣ ቆዳ ሰሪዎችን "ፋቂ" በማለት እንዲጠፉና ከማኅበረሰቡ እንዲገለሉ አደረገ። ይህ ቅስቀሳ በሚሲዮናውያን የተ

የታንጉት ምስጢር

ምዕራፍ አንድ ከፋሲል ዘመነ መንግሥት ጀርሞ የሥልጣን ማዕከል ሆና የኖረችው የጎንደር ከተማ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ፤ ከአዲሱ የቴዎድሮስ ሥርዓት፤ አዲስ የጦር አበጋዞች አዲስ ሠራዊት ጋር ለመስማማት አዲስ ቅኝት ሲከረክር ድንገተኛ ከባድ እንግዳ ወይም ሠርገኛ ደሶበት የቤቱን ዕቃ የሚያተረማምሰ ባለቤት መስሏል። የሚተራመሰው ማኅበራዊ ግንኙነት ግን በወጉ ሊቀመጥ አልቻለም። ሊቀመጥም አይችልም ነበር። ጎንደር ጥንት ከተቆረቆረች፤ ፈጽሞ የተለየ አዲስ ማኅበራዊ ዛፍና ፍሬ ለምቶባት ነበር። ከተማ እንደ ማሳ ነው። ማኅበራዊ አኗኗር ማኅበራዊ አስተሳሰብ የዘራዉን ማኅበራዊ ሕይወት ያበቅላል፤ ያሸታል፤ ያፈራል፤ ማሳው በወቅቱ ካልታረመ ዝባዝንኬው እስከ ገሰሱ በርክቶ ይገኛል። ማሳው ራሱ በሚገባ ካልተያዘ እንክርዳዱም፤ እረሙም እየበዛ ሔዶ ጠቃሚ ፍሬ የማይሰጥበት ጊዜ ይመጣል። ዕዳሪ ይሆናል። የጎንደር ከተማ ማኅበራዊ ሕይወትም አንድ መቶ ስልሳ ዓመት በሚሆን ጊዜ ውስጥ እየተበላሸና ከመልካም ፍሬ ይልቅ፤ ሙጃ የበዛበት ማሳ እየሆነ ሔዶ ነበር። ፋሲል፤ ጎንደርን ሲቆረቁር ሠራዊቱ ገና መዝናናት ያልለመደ ለተግባሩ ያልተሰላቸ፤ ምቾት ገና ያላሰናነፈው፤ ትዕዛዝ አቆብቁቦ የሚጠባበቅ ትኩስ አፍለኛ ነበር። አላማም ነበረው። በሃይማኖት ምክንያት ተነሥቶ የነበረው ሁከትና የርስ በርስ ጦርነት ጨርሶ እስኪረጋጋ ከሥፍራ ሥፍራ እየተንቀሳቀሰ አጥፊ ይቀጣል። አስቸጋሪ ይነገራል። ሰላም ያስከብራል። ከጦር መሪዎቹ ሌላ በስብከት፤ በውግዘት፤ በምርቃት መንፈሳዊ ሕይወቱን የሚያንቀሳቅሱና የሚመሩ፤ ከዚያም አልፎ መስቀል ከሰላጢን ይዘው አብረውት የሚሰለፉ፤ አዲሱን የካቶሊክ ሃይማኖት ነበሩ። የነጋሹም፤ የአንጋሹም፤ የዘማቹም የቀዳሹም ማኅበራዊ ሕይወትና አስተሳሰብ በአንዳች ዐይነት የዘመቻና የዘማች መንፈስ የ