ልጥፎች

ልጥፎችን ከመለያ ታሪክ ጋር በማሳየት ላይ

YouTube

 https://youtube.com/channel/UC1uGQhXKz3wwjCgUNTpWR8g https://youtube.com/channel/UC1uGQhXKz3wwjCgUNTpWR8g

ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!"

ምስል
➊."ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!" : ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው፤ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር፤ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም። : ➋.የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነት አይገልፅም! ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው፤ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል፤ ለሁሉም ጊዜ አለውና ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና። : ➌.መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል! : ጊዜህ ሲደርስ መኪናዎች ወይም ‘አውሮፕላን’ ትገዛለህ ፣ ያውም ለመኖር አስፈላጊ ከሆነ ፣ ደግሞስ እንዴት እንደገዛው የት ታውቃለህ? እርሱን ተወውና በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው። : ➍."ለሰዎች ለደስታቸው እንጂ ለሀዘናቸው መንስዔ አትሁን!" : ►በሰዎች ደስታ→ደስ ይበልህ! : ►ለሰዎች→ክፉ አትመኝ፣ ፡ ►በሃዘናቸውም→አብረህ እዘን፣ ፡ ►ሰዎች ሲያዝኑ→አትደሰት፣ ፡ ►ሰው ከሆንክ→የሰው ነገር ይሰማህ፣ ፡ ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ጋር ተደሰት ማለት አይደለም። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋ ሁን፣ አስተውል። : ➎."በጊዜ ስራ እንጂ ጊዜ ባንተ ላይ አይስራ!" ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም። አንተንም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት፤ በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን። ➏. "መክሊትህን ፈልግ!" ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁና። አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለም እየኖረች ያለችው። በጣ

እጅግ በጣም የሳትነው ብዙ ነገር አለ።

ምስል
እጅግ በጣም የሳትነው ብዙ ነገር አለ። እነዛ የሶሻሊዝምን ጽንሰ-ሃሳብ በውል ያልተረዱ፣ ጺማቸውንና ጠጉራቸውን የሚያሳድጉ የ60'ዎቹ ተማሪዎች "ማርክስ እንዳለው …፣ ኤንግልስ እንዳለው…፣ ሌኒን እንዳለው …፣ ማኦ እንዳለው …፣ ቼጉቬራ እንዳለው…፣ ሆቺሚኒ እንዳለው…፣ እስታሊን    እንዳለው…፣ " ወዘተ እያሉ ታሪካችና እሴቶቻችን እንዲጠለሽ አድርገዋል። Twitter  የ60'ዎቹ ትውልድ ባህሉን፣ ወጉን፣ ሥርዓቱን፣ ሥነ-ጽሑፉን፣ ታሪኩን ጭምር ነቅፎ በባዶ እጁ ነው የሸፈተው። ከቆዳ ቀለማቸው በስተቀር የኢትዮጵያዊነትን ነባር እሴት፣ ባህል፣ ወግ፣ ታሪክ... ፍቀው የነማርክስንና የነስታሊን ፍልስፍና ይዘው ነው የሸፈቱት። መፍትሔው እግዚአብሔርን መካድ የመሰለው ማርክሲዝምን ርዕዮተ ዓለም አድርጎ የተነሣው የሶሻሊስት አቀንቃኝና የብሔር ፖለቲካን ቀይጦ የያዘው ወጣት የኢትዮጵያዊነት አስኳል ከውስጣቸው አውጥተው ጣሉት። በአጉል ማርክሳዊ-ሌኒናዊነት እግዚአብሔር-አልባ አደረጋቸው። ትውልዱንም ሳይቀራረብ የሚተያይ፣ በማያውቀው ታሪክ ተተብትቦ ወደኋላ እንጂ ወደፊት መራመድ የማይችል፣ ባዕድን እንደ ዘመድ፤ ዘመድን እንደ ባዕድ የሚመለከት ሽባ ትውልድ አደረጉት። እንጥፍጣፊ ሳያስቀር የኩራቱንና የክብሩን ካባ አውልቆ ጣለው፣ ኢትዮጵያዊነትን በአፍጢሙ ደፋው፣ የመንፈስ ኃይሉ ደቀቀ፣ በመጨረሻም አንገቱን ደፋ፣ ችግሩንም ሁሉ ለመፍታት የፈረንጆችን እርዳታ የሚፈልግ ትውልድ ተፈጠረ። ቀጥሎስ.....ቀጥሎ ደግሞ የኢትዮጵያ እደ ጥበብ ሠራተኞችን፦ ለምሳሌ ብረት ሰሪዎችን "ቀጥቃጭ"፣ ልብስ ሰሪዎችን "ሸማኔ"፣ ቆዳ ሰሪዎችን "ፋቂ" በማለት እንዲጠፉና ከማኅበረሰቡ እንዲገለሉ አደረገ። ይህ ቅስቀሳ በሚሲዮናውያን የተ

የታንጉት ምስጢር

ምዕራፍ አንድ ከፋሲል ዘመነ መንግሥት ጀርሞ የሥልጣን ማዕከል ሆና የኖረችው የጎንደር ከተማ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ፤ ከአዲሱ የቴዎድሮስ ሥርዓት፤ አዲስ የጦር አበጋዞች አዲስ ሠራዊት ጋር ለመስማማት አዲስ ቅኝት ሲከረክር ድንገተኛ ከባድ እንግዳ ወይም ሠርገኛ ደሶበት የቤቱን ዕቃ የሚያተረማምሰ ባለቤት መስሏል። የሚተራመሰው ማኅበራዊ ግንኙነት ግን በወጉ ሊቀመጥ አልቻለም። ሊቀመጥም አይችልም ነበር። ጎንደር ጥንት ከተቆረቆረች፤ ፈጽሞ የተለየ አዲስ ማኅበራዊ ዛፍና ፍሬ ለምቶባት ነበር። ከተማ እንደ ማሳ ነው። ማኅበራዊ አኗኗር ማኅበራዊ አስተሳሰብ የዘራዉን ማኅበራዊ ሕይወት ያበቅላል፤ ያሸታል፤ ያፈራል፤ ማሳው በወቅቱ ካልታረመ ዝባዝንኬው እስከ ገሰሱ በርክቶ ይገኛል። ማሳው ራሱ በሚገባ ካልተያዘ እንክርዳዱም፤ እረሙም እየበዛ ሔዶ ጠቃሚ ፍሬ የማይሰጥበት ጊዜ ይመጣል። ዕዳሪ ይሆናል። የጎንደር ከተማ ማኅበራዊ ሕይወትም አንድ መቶ ስልሳ ዓመት በሚሆን ጊዜ ውስጥ እየተበላሸና ከመልካም ፍሬ ይልቅ፤ ሙጃ የበዛበት ማሳ እየሆነ ሔዶ ነበር። ፋሲል፤ ጎንደርን ሲቆረቁር ሠራዊቱ ገና መዝናናት ያልለመደ ለተግባሩ ያልተሰላቸ፤ ምቾት ገና ያላሰናነፈው፤ ትዕዛዝ አቆብቁቦ የሚጠባበቅ ትኩስ አፍለኛ ነበር። አላማም ነበረው። በሃይማኖት ምክንያት ተነሥቶ የነበረው ሁከትና የርስ በርስ ጦርነት ጨርሶ እስኪረጋጋ ከሥፍራ ሥፍራ እየተንቀሳቀሰ አጥፊ ይቀጣል። አስቸጋሪ ይነገራል። ሰላም ያስከብራል። ከጦር መሪዎቹ ሌላ በስብከት፤ በውግዘት፤ በምርቃት መንፈሳዊ ሕይወቱን የሚያንቀሳቅሱና የሚመሩ፤ ከዚያም አልፎ መስቀል ከሰላጢን ይዘው አብረውት የሚሰለፉ፤ አዲሱን የካቶሊክ ሃይማኖት ነበሩ። የነጋሹም፤ የአንጋሹም፤ የዘማቹም የቀዳሹም ማኅበራዊ ሕይወትና አስተሳሰብ በአንዳች ዐይነት የዘመቻና የዘማች መንፈስ የ

ዕንቁጣጣሽ_እና_የከንፈር ወዳጅ

ምስል
#ዕንቁጣጣሽ_እና_የከንፈር ወዳጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ በየዓመቱ በታላቅ ስሜት ከሚያከብራቸውና ከሚያዘክራቸው በዓላት አንዱና ተወዳጅ የዘመን መለወጫ በዓል ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በየዓመቱ በታላቅ ስሜት ከሚያከብራቸውና ከሚያዘክራቸው በዓላት አንዱና ተወዳጅ የዘመን መለወጫ በዓል ነው። እንደ ዕፅዋት ሁሉ ሰው በመስከረም ላይ በተስፋ ስሜት ይለመልማል። ከቅዱስ ዮሐንስ ዋዜማ ጀምሮ በየቤቱ ጨፌና ቄጠማ ይጐዘጐዛል። አበባ በሥርዓት እየተዘጋጀ በየቦታውይቀመጣል። በተለይም ልጆች አዳዲስ ልብሳቸውን ለብሰው በደስታ ይፈነድቃሉ። በአመሻሽ ላይ ችቦ አቀጣጥለው «እዮሐ አበባዬ መስከረም ጠባዬ፣ እዮሐ የበርበሬ ውኃ፣ በሸዋ በጐንደር በትግራይ በሐረር... ያላችሁ እንዴት ከረማችሁ፣እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ። እንጉርጉሮገባሽ በየአመቱ ያምጣሽ..» እያሉ ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች (በተለይ በገጠር) ሲዘፍኑና ሲጨፍሩ ያድራሉ። የሚያበሩት ችቦና የሚያነዱት እሳት በግርማ ምሽት ሲንቀለቀል ውጋገኑ ካገር አገር ከሰፈር ሰፈር ከቦታ ቦታ ይታያል።በዕንቁጣጣሽ መዓልት በተደመረው አድባር ሰፈርተኞች ከርቀትም ከቅርበትም ይሰበሰባሉ። አባቶች ይመርቃሉ። «ዝናሙን ዝናመ ምሕረት፣ እህሉን እህለ በረከት ያድርግልን፣ ሰላም ይስጠን፣ እህል ይታፈስ፣ ገበሬ ይረስ፣ አራሽ ገበሬውን፣ ሳቢ በሬውን ይባርክ፣ ቁንጫን፣ አንበጣን፣ ትልን... ያጥፋ፣ ምቀኛን ሸረኛን ያጥፋ፣ ወጡ ገቡ ሰቡ ረቡ የሚለውን ሁሉ እግሩን ቄጠማ ዓይኑን ጨለማ ያድርገው፣ ያርገው፣ ያረገው፣...» ይባባላሉ። እናት አባት ዘመድ አዝማድ በልጆቻቸውና በወዳጅ ዘመዶቻቸው የተበረከተላቸውን የዕንግጫ ጉንጉን (የአበባ አክሊል) በራሳቸው፣ እንጀራ ማቡኪያቸው፣ በመሶባቸው፣ በወጋግራቸው... ላይ ያስራሉ። ይህም የአበባ ጉንጉን ተፈትቶና ወጥቶ የ

ዶክተር መሀሪ ፍሰሃ ማናቸው

ምስል
#ዶክተር_መሃሪ_ፍሰሃ ማናቸው   #4 PHD #8ሁለተኛ ዲግሪ 1ዲግሪ ባለቤት ኢትዮጵያዊ ሙህር #በማኅበራዊ ሳይንስ ውስጥ የሥልጣን ጊዜ ተመራማሪ (ፒ.ዲ.) ፡፡  #በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግና በአለም አቀፍ ግንኙነቶች ተነሳሽነት ፣ በስደት ፣ በስደተኞች ጥበቃ ፣ በሰብአዊ ጣልቃ ገብነት ፣ በዲፕሎማሲ ፣ በሰላም እና በግጭቶች ባለሙያ  ፡፡  #ከሊሜሪክ - አየርላንድ የኤልኤልቢ (የሕግ እና የአውሮፓ ጥናቶች) ተመራቂ  ፣ #(MA) የአስተዳደር እና የፖለቲካ ለውጥ ከነፃ ግዛት - ደቡብ አፍሪካ ፣ (ኤምኤ) የወንጀል ፍትህ ፣ የአስተዳደር እና የፖሊስ ሳይንስ ከ ፋኩልቲ በጀርመን እና በጋንት ዩኒቨርሲቲ የሩር-ዩኒቨርስቲ ቦቹም (አር.ቢ.) ሕግ ፣ (ኤም.ኤስ.ሲ.) ከሉንድ ዩኒቨርስቲ የሕግ ሶሺዮሎጂ ፣ - ስዊድን ፣ (ኤምኤ) ከኮቨንትሪ ዩኒቨርሲቲ (ዩኬ) የሰላም ግንባታ ፣ (ኤምኤ) ዓለም አቀፍ የልማት ልምዶች ከሜሪ ኢንስቴጅ ኮሌጅ የሊሜሪክ ዩኒቨርሲቲ - አየርላንድ ፣ (ፒ.ዲ.) ከማሽሪክ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ፖሊሲ እና ማህበራዊ ሥራ - ቼክ ሪፐብሊክ ፣ (ፒ.ዲ.) ከግራናዳ ዩኒቨርሲቲ የፍልሰት ጥናቶች - እስፔን ፡፡ ከዚህም በላይ በጀርመን ፣ በስዊድን ፣ በማልታ ፣ በፖርቹጋል ፣ በሮማኒያ ፣ በአየርላንድ ፣ በሞልዶቫ ፣ በፖላንድ ፣ በኢጣሊያ ፣ በቼክ ሪፐብሊክ እና በስፔን ኮርሶችን እና ኮንፈረንሶችን ተከታትሏል ፡፡ #የስደተኞች ጥበቃ - በፖርቱጋል የሕግ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ፋኩልቲ ፣ በስቴት ልማት-የስቴት ሪፎርም-የህዝብ አስተዳደር እና የክልል ልማት ቡካሬስት የኢኮኖሚ ጥናት አካዳሚ ፣ የስደተኞች ሁኔታ ውሳኔ UNHCR እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ተቋም በጋራ ያዘጋጁት በስደት እና በስደተኞች ላይ ያሉ የሕግ ተግዳሮቶች ሎው ሳንሬሞ ፣ የድህረ ምረቃ ምር

አይ አሜሪካ

ምስል
#አይ_አሜሪካ  #ከምርጫ_በኋላ_በኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ውይይት_እንዲደረግ_አሜሪካ ጥሪ_አቀረበች  ambachewmu3.blogspot.com  የኢትዮጵያን የወደፊት አካሔድ ለመወሰን እና የአገሪቱን ዴሞክራሲና ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመሩት መንግሥት እና መላ ኢትዮጵያውያን ከምርጫ በኋላ ለሚካሔድ አካታች የፖለቲካ ብሔራዊ ውይይት ቁርጠኛ እንዲሆኑ አሜሪካ ጥሪ አቀረበች። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሚመሩት የአሜሪካ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለሠራተኞቹ ጥረቶች እውቅና ቢሰጥም፤ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የሚካሔድበት ከባቢ“አሳሳቢ ነው” ብሏል።  የአሜሪካ መንግስትን አቋም የሚያንጸባርቀው መግለጫ ዛሬ አርብ ሰኔ 4፤ 2013 የወጣው፤ አንቶኒ ብሊንከን በሚመሩት የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በኩል ነው። መግለጫው መጪው የኢትዮጵያ ምርጫ አሉበት ያላቸውን ፈተናዎች ዘርዝሮ ሥጋቱን ገልጿል። “የተቃዋሚ ፖለቲከኞች እስር፣ የገለልተኛ ሚዲያ መዋከብ፣ የአካባቢያዊ እና ክልላዊ መንግሥታት ወገንተኝነት እንዲሁም በመላ ኢትዮጵያ በብሔሮች እና በማህበረሰቦች መካከል የተቀሰቀሱ ግጭቶች ለነፃ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንቅፋት ናቸው” ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ ያትታል።  በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ስም ይፋ የሆነው መግለጫ የዘረዘራቸው ጉዳዮች፤ ኢትዮጵያውያን ምርጫውን ተዓማኒ አድርገው እንዳይቀበሉት ሊያደርግ እንደሚችልም ጠቁሟል። መግለጫው እንደሚለው “በጸጥታ ጉዳይ እና በመፈናቀል ምክንያት በርካታ የመራጭ ክፍሎች እንዳይሳተፉ መደረጋቸው በተለይ አሳሳቢ ነው።” መግለጫው ፖለቲከኞች እና የማሕበረሰብ መሪዎች ኹከትን እንዲያስወግዱ እና ሌሎችንም ከማነሳሳት እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል። ሁሉም የፖለቲካ ተ

አድዋ

#risingethio https://Facebook.com/risingethiop https://twitter.com/ambachew44 https://imstagram.com/ambachew44 https://telegram.com/ambachew44 https://facebook.com/mulernews

ወርቃማ አፈር

ወርቃማው ዐፈር ⚜ በአጼ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት በርካታ ተጓዦች ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋት፣ ለጉብኝት እና ለስለላ ወደ ኢትዮጵያ ይመላለሱ ነበር፡፡ እነዚህ ተጓዦች ባብዛኛው ይመጡ የነበረው ከአውሮፓ አህጉር ሲሆን በመላው የኢትዮጵያ ምድርም ተዟዙረው ይጎበኙ ነበር፡፡ ከሰሜን ጫፍ ተነስተው እስከ ደቡብ ጫፍ ድረስ ከተጓዙ በኋላ እንደገና ደሞ ከምስራቅ ጫፍ ይጀምሩና እስከ ምዕራብ ጫፍ ድረስ ይጓዙ ነበር፡፡ በጉዞአቸውም የተራሮችን ጫፍ ይረግጡ ነበር፡፡ ወንዞችንም ይሻገሩ ነበር፡፡ በሸለቆዎች መሃል ለመሃልም ሰንጥቀው ያልፉ ነበር፡፡ በረሃዎችንም ያቋርጡ ነበር፡፡ እንዲህ እንዲህ እያሉ ጎብኝተው ሲያበቁ ያዩትን መልከዓ ምድሮች በሙሉ በካርታ አዘጋጅተው ለአጼ ቴዎድሮስ በስጦታ አስረከቡ፡፡ አጼ ቴዎድሮስም ካርታውን ከመረመሩ በኋላ “ካርታው እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡ በዚህ ካርታ አማካኝነት የአባይን መነሻ ማወቅ እንችላለን፡፡ በዚህ ካርታ አማካኝነት የተራሮቻችንን ጫፍ ምን ያህል ከፍታ እዳለው መገንዘብ እንችላለን፡፡ የአገራችን ወንዞች የት የት እንደሚገኙ በቀላሉ መረዳት እንችላለን፡፡ ስለዚህ በሥራችሁ በጣም ተደስተናል፡፡ መልካም ሥራ ነው ያከናወናችሁት፡፡ ስለዚህ በጣም ተደስቼባችኋሉ፡፡” ብለው ለጎብኚዎች ትልቅ ግብዣ አደረጉላቸው፡፡ በግብዣው ወቅት እንጀራውና ወጡ፣ ጠላውና ጠጁ፣ ጮማው ሁሉ ሳይቀር የተትረፈረፈ ነበር፡፡ ግብዣው ካበቃ በኋላ ንጉሱ ለአውሮፓውያኑ የወርቅና የብር ስጦታም አበረከቱላቸው፡፡ ጎብኚዎችም በጣም ተደሰቱ፡፡ ይህ ከሆነ ከጥቂት ቀናት በኋላ ተጓዦቹ ወደ አገራቸው ለመመለስ ተነሱ፡፡ አጼ ቴዎድሮስም በርከት ያሉ አሽከሮቻቸውን ጠርተው “በሉ እነዚህን ተጓዦች መርከቡ ድረስ ሸኟቸው፡፡” ሲሉ ትዕዛዝ ሰጡ፡፡ አሽከሮችም እሺ ብለው የተጓዦችን ሻንጣዎች ተሸክመ