በአድዋ ማግስት የሮማ ጳጳስ ልመና ለእምዬ ምኒልክ ! 💚💛❤ በጣም ኃያል ለሆኑት ምኒልክ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ ሰላምና ገናናነት ለርስዎ ይሁን። ዛሬ አንድ ንጉሳዊ ልግስና እንዲያደርጉ የምክር ቃላችንን ክርስቲያናዊና ንጉሳዊ ለሆነው ልብዎ ለመላክ አሰብን። ይህ ድል ብዙ ምርኮኞች በእጅዎ ጥሎልዎታል። እነዚህ ምርኮዎች በወጣትነት ዘመን የኑሮኣቸው ተስፋ ባበበትና የብርሃን ጎህ በቀደደበት ሰዓት ከአገራቸው ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው ይገኛሉ። የነርሱ ምርኮ የግርማዊነትዎን ዝናና ገናናነት ምንም ሊያስፋፋው አይችልም። ይልቅ የምርኮ ዘመን ጊዜ በረዘመ መጠን በሺህ የሚቆጠሩት ቤተሰቦቻቸው የመንፈስ ሀዘን እየበዛ ሄዷል። ከእየሱስ ክርስቶስ በተቀበልነው የተቀደሰ መልእክት እንደ ልጆቻችን እንወዳቸዋለን። ስለዚህ ያንድ ልብ በቅድስት ስላሴ በተባረከችይቱ ድንግል ወይም ከዚህ ዓለም በሚወዱት ስም የሚያቀርብልዎትን ልመና ይቀበሉና ሳይዘገዩ ነፃነታቸውን ይስጡዋቸው። ኃያሉ ንጉሠ ነገስት ሆይ ይኽን የደግነት ስራ ባለመስራት እምቢታዎን ባለም ነገስታት ዐይን ፊት አይግለፁ። በወንድማማችነት እና በሰብአዊ ተግባር አንፃር ያለው የጦር መብትዎ ምንድን ነው የዚህን ብድር ርኀሩኅ አባት እግዚያብሔር በብዙ ይክስዎታል። ይህን ክብር ያላትን ደብዳቤ በመንግስትዎ ዜና መዋዕል ያስመዝግቧት። እስከዚያው ለንጉሳዊ ቤተሰብ እግዚያብሔር በረከት እንዲያወርድ እንለምናለን። ሮማ ቅዱስ ጴጥሮስ ግንቦት 11 ቀን 1896 ዓ.ም በ19ኛው ዘመነ ጵጵስና ተፃፈ ዋቢ፦ አፄ ምኒሊክና የኢትዮጵያ አንድነት The day after Adwa, the Pope's request to Menelik! 💚💛❤ To the most powerful Menelik Emperor Zeitopia Peace and prosp...