አድዋ

በአድዋ ማግስት የሮማ ጳጳስ ልመና ለእምዬ ምኒልክ !
💚💛❤

በጣም ኃያል ለሆኑት ምኒልክ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ
ሰላምና ገናናነት ለርስዎ ይሁን። ዛሬ አንድ ንጉሳዊ ልግስና እንዲያደርጉ የምክር ቃላችንን ክርስቲያናዊና ንጉሳዊ ለሆነው ልብዎ ለመላክ አሰብን። ይህ ድል ብዙ ምርኮኞች በእጅዎ ጥሎልዎታል። እነዚህ ምርኮዎች በወጣትነት ዘመን የኑሮኣቸው ተስፋ ባበበትና የብርሃን ጎህ በቀደደበት ሰዓት ከአገራቸው ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው ይገኛሉ።
የነርሱ ምርኮ የግርማዊነትዎን ዝናና ገናናነት ምንም ሊያስፋፋው አይችልም። ይልቅ የምርኮ ዘመን ጊዜ በረዘመ መጠን በሺህ የሚቆጠሩት ቤተሰቦቻቸው የመንፈስ ሀዘን እየበዛ ሄዷል። ከእየሱስ ክርስቶስ በተቀበልነው የተቀደሰ መልእክት እንደ ልጆቻችን እንወዳቸዋለን።

ስለዚህ ያንድ ልብ በቅድስት ስላሴ በተባረከችይቱ ድንግል ወይም ከዚህ ዓለም በሚወዱት ስም የሚያቀርብልዎትን ልመና ይቀበሉና ሳይዘገዩ ነፃነታቸውን ይስጡዋቸው። ኃያሉ ንጉሠ ነገስት ሆይ ይኽን የደግነት ስራ ባለመስራት እምቢታዎን ባለም ነገስታት ዐይን ፊት አይግለፁ። በወንድማማችነት እና በሰብአዊ ተግባር አንፃር ያለው የጦር መብትዎ ምንድን ነው የዚህን ብድር ርኀሩኅ አባት እግዚያብሔር በብዙ ይክስዎታል። ይህን ክብር ያላትን ደብዳቤ በመንግስትዎ ዜና መዋዕል ያስመዝግቧት።
እስከዚያው ለንጉሳዊ ቤተሰብ እግዚያብሔር በረከት እንዲያወርድ እንለምናለን።

ሮማ ቅዱስ ጴጥሮስ
ግንቦት 11 ቀን 1896 ዓ.ም በ19ኛው ዘመነ ጵጵስና ተፃፈ

ዋቢ፦ አፄ ምኒሊክና የኢትዮጵያ አንድነት
The day after Adwa, the Pope's request to Menelik!
💚💛❤

To the most powerful Menelik Emperor Zeitopia
Peace and prosperity be to you. Today we intend to send our advice to your Christian and royal heart to make a royal donation. This victory has left many captives in your hands. These captives were separated from their families in the days of their youth, at a time when their lives were at stake.
Their captivity will not enhance your majesty and fame. Instead, during the long period of captivity, the grief of thousands of their families increased. We love them as our children do in the sacred message we receive from Jesus Christ.

Therefore, accept the request of a heart in the name of the Blessed Virgin of the Holy Trinity, or in the name of your loved ones in this world, and grant them freedom without delay. O mighty emperor, do not express your refusal in the eyes of the emperors for not doing this kind deed. What are your military rights in terms of brotherhood and humanitarian action? God, the Compassionate Father of this loan, will reward you g
#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_125
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)