ቴወድሮስ

#ቴዎድሮስ_ቀደምት_የተንሰራፋውን_የባሪያ_ንግድ_ስርዓት ያጠቃ ንጉስ ነበር ። በዚህ ወቅት ባሪያ መሸጥም ሆነ መለወጥ እንዲሁም ማጓጓዝን የሚያግዱ ብዙ ድንጋጌወችን ንጉሱ በማወጅ ቀደምት የባርነት ስርዓት ተቃዋሚ ንጉስ ሆነ። ለምሳሌ ጎጃም፣ ባሶ ውስጥ ባደረገው ዘመቻ በገበያው የተገኙ ባሪያወችን በነጻ ለቋል። ወሎ ውስጥ የተማረኩ ባሪያወች እንዳይሸጡ አግዷል።ሆኖም ግን ከህጉ ውጭ በኮንትሮባንድ ውስጥ ለውስጥ በአገሪቷ ዳርቻወች ባሪያ መሸጡና መለወጡ አላቆመም።

#ከባህል አንጻር የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ንጉሥ ዘመን ማደግና መሻሻል አሳይቷል። ከፍተኛው የመንግስት ስራ በአማርኛ ይካሄድ ነበር። ዜና መዋእላቸውን በአማርኛ ለመጀሚርያ ጊዜ ያስጻፉ ንጉሥ ነበሩ።]፣ ከዚህ በፊት በግዕዝ ነበር። ከዚህ በኋላ አማርኛ የአገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ ሆነ።ቴዎድሮስ ከግዕዝ ይልቅ ሰወች በሚረዱት አማርኛ መጽሃፍ ቅዱስ እንዲተረጎም አደርጉ።
#የመጀመሪያው_የጂዖግራፊያ መጽሃፍ በአማርኛ የታተመውም በኒሁ ንጉስ ዘመን ነበር።
# ህዝቡ ለጋብቻ ከፍተኛ ዋጋ እንዲሰጥም በጣም ጥረት አድርገዋል፣ እራሳቸውም በአንድ ሴት በመወሰን መሪ ምሳሌ ለመሆን ሞክረዋል። 
#ከቴዎድሮስ በፊት ይሰራበት የነበረውን ከወገብ በላይ እራቁት መሆን የአለባበስ ዘዴን በማስቀረት ሹሞች በጥሩ ሁኔታ እንዲለብሱ አድርገዋል። በአጠቃላይ ህዝቡ የሃይማኖትና የባህል ህጎችን አጥብቆ እንዲከተል ጥረት አድርገዋል።

#ከአስተዳደር ስልት አንጻር ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ እስከፈጸሙት ድረስ የነበረውን አገሪቱን በማዕከላዊ ሃይል የማስተዳደር ስራ ጀምረዋል። በአዲሱ ስርዓት መሰረት የግብር እና የፍርድ ባለስልጣናት ከማዕከላዊ መንግስት ደመወዛቸውን እንዲያገኙ ተደረገ፣ ይህም በየቦታው የነበሩ ባላባቶችን የመፍለጥ የመቁረጥ ሃይል የቀነሰ ተግባር ነበር።] የሆኖ ሆኖ ንጉሡ የገዥውን መደብ ሙሉ በሙሉ አልቀየሩም፣ አንድ አንድ ገዥወች በነበሩበት እንዲቀጥሉ አድርገዋል። ለምሳሌ የትግራይ ገዥ የነበሩት ደጅ አዝማች ሰባጋዲስ ዘር የሆኑትን ካሳ ምርጫን በትግራይ ሾሙ፣ እንዲሁም የንጉስ ሳህለ ስላሴ ዘር የሆኑትን ሃይለ ሚካኤልን በመሾም በየቦታው የነበሩትን የሃይል ማዕከላት በነበሩበት እንዲጸኑ አድርገዋል።] በአንዳንድ ክፍሎች የራሳቸውን ዘመዶች ስልጣን ያወጡበት ሁኔታ ይገኛል፣ ለምሳሌ ራስ እንግዳን በጎጃም። ይህ ስርዓት በመጀመሪያ እጅግ የተሳካ ነበር ምክንያቱም በዘመነ መሳፍንት እንኳ ሳይቀር ጠንካራ ባላባቶች ለንጉሳዊው ስልጣን የመገዛት ባህርይ ያሳዩ ነበርና። ከሸዋ መርዕድ አዝማች ሃይለ ሚካኤል በየጊዜው ወደ ንጉሱ የጓዙ ነበር። ትግራይ ደግሞ ለንጉሱ ዋና የገቢ ምንጭ ነበር (200፣000 ማሪያ ቴሬሳ በአመት)፣ ከበጌምድር የሚያገኙት 50፣000 ማሪያ ቴሬሳ ብቻ ነበር። ሆኖም ግን አንድ አንድ ጥቃቅን ባላባቶች አመጽ ለማስነሳት መመኮራቸው አልቀረም፣ ስለሆነም ንጉሱ ሰራዊቱን ማሻሻል እንዳለባቸው ተገነዘቡ።
*#ዘመናዊ ሠራዊት
ሠራዊቱ በፖለቲካው ውስጥ ባለው መሰረታዊ ተፅዕኖ ምክንያት ንጉስ ቴዎድሮስ በዚህ ክፍል ላይ ብዙ ትኩረት አድርገዋል። እራሳቸውን ከስሎሞኑ ስርወ መንግስት በመጀመሪያ የአገዛዛቸው ዘመን በማራቃቸው ብቸኛው ወደላይ የሚያወጣቸው መሰላል የውትድርና ብቃት እንደሆነ ጠንቅቀው ተረዱ። አገራዊ ሠራዊቱን ለማጠናከርና ብሔራዊ አንድነትን እውን ለማድረግ፣ ዋልተር ፕላውዴን "ታላቁ ለውጥ" ያለውን አጼ ቴዎድሮስ አከናወኑ ። ይህ ታላቅ ለውጥ በ3 አብይ ክፍሎች ላይ ያተኮረ ነበር፡ ፩.መዋቅር ፪.ዲሲፕሊንና ፫.ትጥቅ ናቸው።[] እኒህ ለውጦች ከሞላ ጎደል የተወደዱና ለብዙ ድሎች ያበቃቸው ሲሆን ስልጣናቸውንም ለማንሰራፋት አይነተኛ ምክንያት ናቸው። እኒህ ለውጦች የአገሪቱ ዜጎች በ"አንጻራዊ ደህነነት" እንዲኖሩ ረድተዋል 9።

ከመዋቅር አንጻር ከዘመነ መሳፍንት ሲወርድ የመጣውን የተከፋፈለ የባላባቶች ሰራዊትን በአንድ ብሔራዊ ሰራዊት ቀይረዋል። ከተለያዩ ክፍለ ሃገሮች የመጡት ወታደሮች በንጉሠ ነገሥቱ በተዋቀረ አንድ የጦር ክፍል ስር ተደራጁ።እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ሰራዊት የሚሰራበት የአስር አለቃ፣ የሀምሳ አለቃና መሰል ማዕረጎች የተፈጠሩት በዚሁ ዘመን ነበር።ንጉሡን የሚያጅቡትን ወታደሮች ቁጥር በመቀነስ፣ የዚህን ክፍል እዳተኝነትን ቀነሱ።ወታደሮች ከዚህ በኋላ ቋሚ ደሞዝ ተቆርጦላቸው ስለሚተዳደሩ የሰፈሩበትን ቦታ መበዝበዝ በህግ ተከለከሉ።በፊውዳሉ ስርዓት ወታደሮች በረገጡበት ቦታ ያሉ ገበሬወች ምግብና መኝታ እንዲያቀርቡ ይገደደዱ ነበር።ይህ ሁኔታ በንጉሠ ነገሥቱ አጥብቆ የተከለከለ ነበር።ይህን በሚያሳይ መልኩ ለምሳሌ አንድ ገበሬ የ12 ጫጩት እናት የሆነችን ዶሮ እንዲያርድ በንጉሱ ወታደር ይገደዳል። ድርጊቱ ንጉሱ ድረስ ቀርቦ በዳኝነት ከታየ በኋላ ወታደሩ በሞት ሲቀጣ ገብሬው ላም ተሰጥቶት እንዲሄድ ተደረገ።በዚህ ዘመን ወታደሮች ቀለብ የሚባል ገቢ ከንጉሱ የሚሰፈርላቸው ሲሆን ከዚህ ውጭ ማንም ገበሬውን ያስገደደ ወታደር ከፍተኛ ቅጣት ይቀጣ ነበር።
ንጉሡ በሠራዊቱ ዘንድ እንደ ብረት የጠነከረ ዲሲፕሊን ለማቋቋም ሞክረዋል።ለምሳሌ ወደ ወሎ ባደረጉት ዘመቻ ያለትዕዛዝ ጦርነት የሚገቡ ወታደሮች ያለርህራሄ ይገደሉ ነበር። በሸዋው ዘመቻ እርስ በርስ ሽኩቻ ያሳዩ ወታደሮች በሙሉ በጥይት ተደብድበዋል። ባህሩ ዘውዴ እኒህ ድርጊቶች ደም መፋሰሱ እንዲባባስ በማድረግ ብዙ ጥቅም አላመጡም ያላል።ሆኖም ወታደሩ በራሱ ፈቃድ ብዙ ጥፋት እንዳያደርግ ረድቷል።

አብዛኛው የአጼ ቴዎድሮስ ሰራዊት ጦር መሳሪያ ከጦር ሜዳ የተማረከ ነበር ። ቆይተው ግን ከአውሮጳ ቴክኖሎጂ በማስመጣት በኢትዮጵያ ምድር ላይ የመሳሪያ ማምረቻ ለማቋቋም ሞክረዋል።] ለዚህ ተግባራቸው እንዲረዳ የአውሮጳ ሚስዮኖችን በጋፋት፣ ደብረታቦር ሰብስበው መሳሪያ እንዲሰሩ አደርጉ ከዚህ ትይዩ ትምህርት ቤት በማቋቋም ጥበቡን ተማሪወች እንዲቀስሙ አደረጉ።[ የመጀመሪያው ትክክለኛ የመሳሪያ ዝርዝር የተገኘው ከመቅደላ በአጼ ቴዎድሮስ ዘመን ነበር፡ #15_መድፎች፣ #7_አዳፍኔዎች፣ #11063_ጠመንጃዎች፣ #875ሽጉጦች፣ #481 ሳንጃዎችና ጥይቶችን ያጠቃልላል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ)