ተስፋ

.ተሰፋ አንቆርጥም...(ሳሙኤል አዳነ)
ውሀ በፈረቃ ፣
መብራት በፈረቃ፣
ስልጣን በፈረቃ ፣
ላገር ሲታደሉ ፣
ውሀ አጣጭ ፈለጋ
መብራት ጠፋ ብለሽ ፣
ከባለ ስልጣን ጋር
ትዞሪያለሽ አሉ ።
ይሁና ..
ውሀ የመጣለት ...
ገላዬን ታጥቤ፣
ልብሴን አሳጥቤ ፣
ስልጣንም ካገኘሁ ፣
እሱን ተረክቤ
መብራትም ይመጣና፣
በግዙፍ አዳራሽ
ሰርጌን አከብራለሁ ፣
ብትመጭ አታጭኝም ፣
ግን አታገቢኝም ፣
ካሁኑ ሄጃለሁ ።
እናም የዛንለት ...
በእጣ ፈንታችን
መንግስት እንወቅሳለን ፣
ሀገር እንከሳለን፣
ቆይቶ..ቆይቶ..ቆይቶ..
ጩህታችን ሰምሮ ፣
በሌላ ፈረቃ እንገናኛለን ።
ተሰፋ አንቆርጥም
12/09/2011
ከጧቱ 12:00 ሰአት
መብራት ሳይጠፋ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ)