የእንግሊዝ ዲፕሎማሲ

#የእንግሊዝ_ዲፕሎማሲ_መበላሸት
ጥቅምት 29፣ 1854 ላይ አጼ ቴዎድሮስ ሁለት ተመሳሳይ ደብዳቤወችን ለእንግሊዟ ንግስት ቪክቶሪያና ለፈረንሳዩ ናፖሊዮን ሳልሳዊ ላኩ። የደብዳቤያቸው ፍሬ ነገር የቱርኮች በኢትዮጵያ ግዛት መኖርን የሚቃወምና እነርሱን ከኢትዮጵያ ምድር ለማባረር ድጋፍ እንዲሰጡ ነበር።[83] ደብዳቤው በ1854 የእንግሊዝ ቆንጽላ በኢትዮጵያ ተብሎ በተሾመው ካፕቴን ካሜሮን አማካኘት የተላከ ነበር። በዚሁ ደብዳቤ ንጉሠ ነገሥቱ ጆን ቤልና ዋልተር ፕላውዴን ለንጉሱ የገቡትን ቃል አስታውሶ ንግስት ቪክቶሪያ የንጉስ "ታላቅ ንግስት" እንደሆነችና "የክርስቲያኖች ወዳጅ" እንደሆነች ያስታውሳል።[83] በዚህ ምክንያት እንግሊዝን እንደሚወዱ በደብዳቤው አስፍረዋል።[83] ከዚህ በተጨማሪ የቱርኮች በኢትዮጵያ ባህር ወደብ ላይ መንሰራፋት በቀይ ባህርል ላይ ጉዞ እንዳያደርጉ የሚከለክልና አምባሳደርም እንዳይልኩ ያደረጋቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።[84]

ጥር 12፣ 1854 ላይ የቴዎድሮስ ደብዳቤ ለንድን ቢደረሰም።[84] የታቀደውን አላማ አልፈጸመም። ለዚህ ምክንያቱ ሩሲያውያን የእንግሊዝን የህንድ ግዛት መገዳደራቸው ነበር።[84] ስለሆነም እንግሊዝ ሩሲያን በጠላትነት ፈርጃ ክሩሲያ ጠላቶች -ከቱርኮች ጋር የጠበቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማድረግ ሩሲያን አንድ ላይ የሚታገሉበት ወቅት ነበር።[84] ስለሆነም የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መሰሪያ ቤት ለቴዎድሮስ ደብዳቤ መልስ እንኳ ሳይጽፍ እንዲሁ በተመላሽ ደብዳቤውን ለእንግሊዝ ወኪል በህንድ ላከ።[84] የህንዱም መስሪያ ቤት ደብዳቤውን ወደ ጎን ከማስቀመጥ ውጭ መልስ አልላከም ነበር።[84] በዚያው አመት ሚያዚያ 1854 ካፒቴን ካሜሮን ክእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ጸሃፊ ኸርል ረስል በደረሰው ደብዳቤ የእንግሊዝ መንግስት የኢትዮጵያን የድጋፍ ጥያቄወች ውድቅ እንዳደረገ ተረዳ።[84] ካሜሮን ወደ ምጽዋ በመሄድ በዚያ እንዲወስን መልዕክቱ ያዝ ነበር።[84] በዚህ መካከል ንጉሱ ከእንግሊዝ መልስ ባለማግኘታቸው የእንግሊዝ መንግስት ሆን ብሎ ችላ እንዳላቸው እምነት አሳደረባቸው።[75][85]

በታሪክ አጥኝው ሪቻርድ ፐንክኽርስት አስተሳሰብ የዚህ እምነት ምክንያት የቴዎድሮስ "እንግሊዝ ግብጽን ትደግፋለች" የሚል "የተሳሳተ እምነት" ነው ይበል እንጂ።[86] በእርግጥም እንግሊዞች ከግብስ ጋር የንግድ ግንኙነት ለመፍጠር ሞክረው ነበር። በ1856፣ በግብጽ ቁጥጥር ስር በነበረው የሱዳን ክፍል የጥጥ ተክልን ለመትከል የሚያስችል እቅድ ለመንደፍ የእንግሊዙ ካፒቴን ካሜሮን ተጉዞ ነበር።[87] እኒህን ነገሮች የሚከታተሉት ንጉሱ፣ ካሜሮን የግብጾቹን በሱዳን ወረራ ዕውቅና እንደሚሰጥና በግልጽም ለነሱ እንደሚያደላ ተረዱ።[75][85] ህዳር 1856 ላይ ከኸርል ሩስል ጸሃፊ ጄምስ መሪይ በመጣ ደብዳቤ መሰረት ካፒቴን ካሜሮን በምጽዋ ላይ እንጂ በኢትዮጵያ እንዳልተሾመ ማስታወሻ ደረስው።[75][85] ነገር ግን ይሄ ደብዳቤ ስህተት ነበር ምክንያቱም የካፒቴን ካሜሮን ሹመት የንግስቲቷ ቆንጽላ በኢትዮጵያ የሚል ነበርና።[75][85]።.

እንኒህ ለውጦችን በጥሞና የሚከታተሉት አጼ ቴዎድሮስ ይህ የብሪታኒያ መንግስት ፖሊሲ በጊዜው ምጽዋን ይቆጣጠር የነበረውን የኦቶማን/ቱርክ ግዛት የሚደግፍ ሆነው አገኙት።[75][85] ለቴዎድሮስ ትልቅ ትርጉም በነበረባት እየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያንና መኖሪያቸው በእንግሊዞች ጥበቃ ያገኝ የነበር ቢሆንም አዲስ የተሾመው የብሪታንያ ቆንጽላ ግን የኦቶማን ቱርኮች ኢትዮጵያውያንን ከሚኖሩበት ሲያባርሩ እንግሊዞቹ አልተቃወሙም ነበር።[86] የእንግሊዝ መንግስት ኦቶማን ቱርክን ለመደገፍ መምረጡ በንጉሰ ነገስቱና በእንግሊዝ መንግስት መካከል ለተፈጠረው ጥል ዋና መነሻ ነበር።[76][85] ንጉሡ ለጻፉት ደብዳቤ አንድ አመት ሙሉ መልሱን ሲጠባበቁ ቢቆዩም ምንም መልስ ባለማግኘታቸው ትዕግስታቸው ተሟጦ [88] ጥር 4፣ 1856 ላይ ካፒቴን ካሜሮንና ሌሎች የዲፕሎማሲው አካሎች በመቅደላ ታሰሩ።[86] እስክዚያው ድረስ መልስ ሳይሰጡ ዝምታን የፈቀዱት እንግሊዞች በርግጥም በዚህ ጊዜ ከዝምታቸው ነቁ [89]። ወዲያውም ወደ ጎን የተጣለው የንጉሱ ደብዳቤ ተፈልጎ ተገኘ፣ ብዙም ሳይቆይ እንግሊዞች ደብዳቤ ላኩ ። "አስቸኳይ" ደብዳቤ ተጽፎ በሆሙዝ ራሳም አማክይነት ጥር 26፣ 1858 ጣና ሃይቅ አጠገብ ለንጉሱ ደረሰ።[80] በዚሁ ደብዳቤ የእንግሊዝ መንግስት እስረኞቹ እንዲፈቱና ይህ ሲሆን እርዳታ እንደሚሰጥ አስታወቀ። በዚህ መልስ ያልረኩት ቴዎድሮስ ራሳምን እንዲሁ በመቅደላ እስር ቤት ከተቱት [90]።

ለሰላም መውረድ የመጨረሻው ተስፋ ነው የተባለው ሚሲዮኑ ማርትን ፍላድ በሐምሌ 1858 ከቴዎድሮስ ወደ እንግሊዝ ተላከ።[80] ጥር 1859 ላይ ንጉሰ ነገሥቱ እስረኞቹን ፈተው ወደ ምጽዋ ከተወሰዱ በምትኩ የእንግሊዝ መንግስት ወታደራዊ እርዳታ እንደሚያደርግ ደብዳቤ ከእንግሊዝ መንግስት ደረሳቸው።[91] በመካከሉ፣ ኢትዮጵያው ውስጥ የነበረቸው የማርቲን ፍላድ ሚስት፣ አውሮጳውያኑ እንደገና እንደታሰሩ ለባሏ አሳወቀች።[85] ታህሳስ 185 ላይ እስረኞቹ ተፈተው ወደ ምጽዋ እንዲላኩ ፍላጎቱን አስታወቀ።[85] በዚህ ወቅት ንጉሰ ነገሥቱ በማያባራ ዘመቻና የማያቋርጥ አመጽ ተጠምደው ስለነበር ከመቅደላ ምጽዋ ያለውን መንገድ መቆጣጠር አይችሉም ነበር።[85] ስለሆነም ሚያዚያ 1859 ከእንግሊዝ የደረሳቸውን ዛቻ መልስ ባለመስጠት ችላ አሉት ፣ በዚህ ሁኔታ የእንግሊዝ መንግስት እስረኞቹን ለማስፈታት ዘመቻ ለማድረግ ወሰነ።[91]

#የቴዎድሮስ መሞት_የእንግሊዞች ዘመቻ
በመረጃ ልውውጥ ላይ በተነሳው ችግርና እንዲሁም እንግሊዞች ለንጉሱ የላኩት ዛቻ መልስ ባለማግኘቱ ምክንያት ነሐሴ 1859 እንግሊዞች በሮበርት ናፒየር የሚመራ 32፣000 ጦር ሰራዊት አዘመቱ።[62] እንግሊዞቹ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ስለሚሆነው ጉዳይ ጥልቅ መረጃ የነበራቸው ሲሆን በየአካባቢው እየተነሳ ስለነበር አመጽ ሙሉ ግንዛቤ ነበራቸው። የቴዎድሮስ ሰራዊት በድሮ ጊዜ ወደ 100፣000 የሚጠጋ የነበር ሲሆን በ1859 ከ5 እስከ 10፣000 በላይ አይሆንም ነበር።[82] ንጉሰ ነገሥቱ የመጨረሻ ዘመቻቸውን ፈጽመው በጥቅምት 1860 ላይ መቅደላ ደረሱ፣ ይሄውም ከናፒየር ሰራዊት 2 ሳምንት ቀድሞ ነበር።[70]

የእንግሊዝ ሠራዊት ያለምንም ችግር ምጽዋ ላይ ካረፈ በኋላ ከሌሎች የኢትዮጵያ ኃይሎች ለምሳሌ ካሳ ምርጫ ድጋፍ በማግኘት፣ ከተክለ ጊዮርጊስ ሐዘን በማግኘት፣ ከዳግማዊ ምኒልክ ድጋፍም ሆነ ተቃውሞ ሳይደርስበት ያለ ችግር ወደ መቅደላ ተመመ።[67][92] የብሪታንያ ሠራዊት በተለይ ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘው ከካሳ ምርጫ ሲሆን፣ በቂ የመጓጓዣና የምግብ እርዳታ ያገኙት ከኒሁ ሹም ነበር።[93] ሚያዚያ ፲ ቀን ፲፰፻፷ ዓ/ም ላይ የመጀመሪያውና የመጨረሻው የፊት ለፊት ጦርነት በቴዎድሮስ ሰራዊትና በናፒየር ሰራዊት መካከል ተካሄደ70። ይህ ጦርነት በታሪክ የአሮጌ ጦርነት ተብሎ ሲታወቅ ከመቅደላ እግርጌ የተደረገ ውጊያ ሲሆን በዚሁ ጦርነት የኢትዮጵያ ሰራዊት ተሸንፎ አፈገፈገ 12።


የእንግሊዝ ወታድሮች የንጉሡን እሬሳ ሲያዩ። ለዚህ ማስታወሻ የተገጠመ ግጥም
ገደልንም እንዳይሉ ..ሞተው አገኟቸው
ማረክንም እንዳይሉ .. ሰው የለ በጃቸው
ምን አሉ እንግሊዞች.. ሲገቡ አገራቸው
ለወሬ አይመቹ .... ተንኮለኛ ናቸው
በሚቀጥለው ቀን፣ ሚያዚያ11 ላይ፣ ናፒየር ለቴዎድሮስ በጻፈው ደብዳቤ ንጉሡ እስረኞቹን ከፈቱና ለ"እንግሊዟ ንግሥት እጅ ከሰጡ" "በክብር እንደሚያዙ" አሳወቃቸው።[94] ሆኖም ንጉሰ ነገሥቱ ከኩራታቸው አንጻር ይህን አይነት መዋረድ እንደማይቀበሉ አሳወቁ።[94] በዚህ ሁኔታ ንጉሱ አቋማቸውን በደምብ የሚያሳውቅ፣ በጊዜው "ድንቅ" የተባለ[94]፣ ማንነታቸውንም በርግጥ የሚይሳይ ደብዳቤ ጻፉ።[93] ለናፒርየር የተጻፈው ይህ ደብዳቤ አጠቃላይ የጊዜውን የኢትዮጵያ ሁኔታ የዳሰሰና ለኢትዮጵያ ህዝብ የገቡት የመጨረሻ ኪዳን ነበር።[94]

"በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ፡ አንድ አምላክ፡ በሥላሴ፣ በክርስቶስ፡ የሚያምነው ፡ ካሳ [...] ለአገሬ ሕዝብ "ግብርን ተቀበሉ፣ ስርዓትንም ተማሩ" ብየ፡ብነገር፡ እነርሱ ፡ ግን፡ ይህን ፡ በመቃወም፡ ከኔ ጋር ጥል ጀመሩ። አንተ ፡ ግን ፡ በስራት፡ በሚመሩ፡ ወታደሮች፡ ታሸንፋለህ። አልባሌ ፡ የብረት፡ ኳስ፡ ፈርተው፡ የሚወዱኝና ፡ የሚከተሉኝ ፡ ሰወች ፡ ጥለውኝ ፡ ጠፉ። አንተ ፡ጥቃት፡ ስታደረስ፡ ከነርሱ፡ ጋር አልነበርኩም። እኔማ፡ እራሴን፡ ትልቅ ፡ አድርጌ፡ ቆጥሬ፡ ዋጋ ፡ በሌለው፡ መድፍ ፡ ተዋጋሁ። [...] እግዚአብሔር ፡ ቢፈቅድ፡ ሁሉን ፡ለመመራት፡ ነበር፡ ሃሳቤ፣ አምላክ ፡ ይሄን፡ ከከለከለኝ ፡ ሞቴን እጠብቃለሁ [...] እራስክን ፡ትላንት ፡ያስደሰትክ ሆይ፣ አምላክ እንደኔ አያድርግህ፣ በተለይ ደግሞ አምላክ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ጠላቶቸን አያድርግህ። እኔማ እየሩሳሌም ሂጄ ቱርኮችን ለማባረር ነበር ሃሳቤ። ወንዶችን የማረከ፣ በሌሎች ሊማረክ አይችልም።[95]
እኒህን "የጀግንነት ቃላት"[94] ካስጻፉ በኋላ ንጉሱ እራሳቸውን ሊያጠፉ ቢሞክሩም ወታደሮቻቸው ሽጉጣቸውን ከጃቸው ነጥቀው አዳኗቸው።[96] ይህ ሁሉ ሲሆን ከእንግሊዞች ጋር የሚደረገው ድርድር አላቋረጠም፣ ንጉሰ ነገሥቱም ጥሉን በሰላም ለመፍታት ከመሞከር አልተቆጠቡም። ለፋሲካ በዓል ማክበሪያ ብለው ንጉሱ ለናፒየር ብዙ ከብቶች በስጦታ ላኩ።[96] የእንግሊዙ ጦር አዛዥ ግን የከብት ስጦታውን አልቀበልም በማለት መልሶ ላከ።[97] የስጦታውን አለመቀበል ንጉሱ ሲሰሙ ከመቅደላ ለመውጣት ሞከሩ ሆኖም ግን መቅደላ በእንግሊዞች ተከቦ ነበር።[97]

በዚህ ወቅት ለብዙ ወቅት የታሰሩት ሚሲዮኖችና የፖለቲከኛ እስረኞች ተፈቱ።[98] የተፈቱትን እስረኞች ያዩ ገለልተኛ ተመልካቾች፣ በፈረንሳይ፣ በሩሲያ፣ በሳውዲ አረቢያ፣ በሆላንድ፣ አውስትራሊያና ስፔን በእስረኞቹ መልካም ጤና በጣም ይደነቁ ነበር፣ ከእስረኞቹ አንዱም «በታስርነበት ወቅት ጥሩ ቤትና ምግብ ነበረን የምንፈራው የንጉሱን ቁጣ ነበር»።[97]

ሚያዚያ ፮ ቀን ሦስት ሰዓት ላይ እንግሊዞች በመቅደላ ምሽግ ላይ የመጨረሻ ጥቃት አደረሱ። ንጉሱ፣ የሃይል ሚዛኑ ወደ እንግሊዞቹ ሙሉ በሙሉ አንዳጋደለ ስለተረዱ ለወታደሮቻቸው እንዲህ በማለተ ተለይተው ሄዱ "ተፈጽሟል! ከርሱ እጅ ከምወድቅ ብሞት ይሻለኛል"።[97] ወዲያውም ከንግስት ቪክቶሪያ የተላከላቸውን ሽጉጥ[95] መዘው በመጉረስ በጀግንነት አለፉ።[97]

እንግሊዞቹ 9 ሚሊዮን ፓውንድ አውጥተው ዘመቻውን ሲያቅዱ የመቅደላን ምሽግ አፍርሰው ንጉሱን ለመማረክ ነበር።[98] ሆኖም ምሽጉ ሲሰበር ንጉሱ ሞተው ስልተገኘ ናፒየር እጅጉን በመናደዱ ሙሉውን መቅደላ እንዲመዘብርና [99] የተረፈው በእሳት እንዲጋይ አደረገ።[99] ሚያዚያ 18 ላይ እንግሊዞቹ የተከፋፈለች አገር ትተው ሄዱ፣ ወዲያም ግንቦት 1860 ላይ የላስታው ዋግሹም ጎበዜ በ60፣000 ጠንካራ ወታደሮቹ በመታገዝ ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጼ ተክለ ጊዮርጊስ በመባል ስልጣን ላይ ወጣ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ)