ልጥፎች

ልጥፎችን ከመለያ Ethiopia ጋር በማሳየት ላይ

YouTube

 https://youtube.com/channel/UC1uGQhXKz3wwjCgUNTpWR8g https://youtube.com/channel/UC1uGQhXKz3wwjCgUNTpWR8g

Background Information on Ethiopia

ምስል
Background Information on Ethiopia Ethiopia has many diverse topographical, climatic, linguistic, and religious  features. Geographically, Ethiopia is located within the hot zone. Its southern tip is only  30 degrees north of the equator. However, due to its high altitude, the country has a  predominantly moderate climate with an average temperature in its vast central highland  plateaus no more than 20°C (68°F). The Great East African Rift Valley traverses the  central highland plateau into the north-west and south-east highlands. The majority of  the population lives in scattered villages in the highlands as farmers and pastoralists. The  three popular indigenous foodstuff plants, teff (Eragrostis teff), nug (Guizotia  abyssinica), and enset (Edulis edule) have been cultivated since at least the 5th  millennium BC (Pankhurst, 2005, p. 13).The highlands are surrounded by lowlands, the  largest part of which lies on the south-eastern side adjacent to Somalia. The Ethiopian  Rift Valley...

ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!"

ምስል
➊."ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!" : ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው፤ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር፤ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም። : ➋.የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነት አይገልፅም! ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው፤ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል፤ ለሁሉም ጊዜ አለውና ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና። : ➌.መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል! : ጊዜህ ሲደርስ መኪናዎች ወይም ‘አውሮፕላን’ ትገዛለህ ፣ ያውም ለመኖር አስፈላጊ ከሆነ ፣ ደግሞስ እንዴት እንደገዛው የት ታውቃለህ? እርሱን ተወውና በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው። : ➍."ለሰዎች ለደስታቸው እንጂ ለሀዘናቸው መንስዔ አትሁን!" : ►በሰዎች ደስታ→ደስ ይበልህ! : ►ለሰዎች→ክፉ አትመኝ፣ ፡ ►በሃዘናቸውም→አብረህ እዘን፣ ፡ ►ሰዎች ሲያዝኑ→አትደሰት፣ ፡ ►ሰው ከሆንክ→የሰው ነገር ይሰማህ፣ ፡ ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ጋር ተደሰት ማለት አይደለም። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋ ሁን፣ አስተውል። : ➎."በጊዜ ስራ እንጂ ጊዜ ባንተ ላይ አይስራ!" ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም። አንተንም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት፤ በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን። ➏. "መክሊትህን ፈልግ!" ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁና። አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለም እየኖረች ያለችው። በጣ...

እጅግ በጣም የሳትነው ብዙ ነገር አለ።

ምስል
እጅግ በጣም የሳትነው ብዙ ነገር አለ። እነዛ የሶሻሊዝምን ጽንሰ-ሃሳብ በውል ያልተረዱ፣ ጺማቸውንና ጠጉራቸውን የሚያሳድጉ የ60'ዎቹ ተማሪዎች "ማርክስ እንዳለው …፣ ኤንግልስ እንዳለው…፣ ሌኒን እንዳለው …፣ ማኦ እንዳለው …፣ ቼጉቬራ እንዳለው…፣ ሆቺሚኒ እንዳለው…፣ እስታሊን    እንዳለው…፣ " ወዘተ እያሉ ታሪካችና እሴቶቻችን እንዲጠለሽ አድርገዋል። Twitter  የ60'ዎቹ ትውልድ ባህሉን፣ ወጉን፣ ሥርዓቱን፣ ሥነ-ጽሑፉን፣ ታሪኩን ጭምር ነቅፎ በባዶ እጁ ነው የሸፈተው። ከቆዳ ቀለማቸው በስተቀር የኢትዮጵያዊነትን ነባር እሴት፣ ባህል፣ ወግ፣ ታሪክ... ፍቀው የነማርክስንና የነስታሊን ፍልስፍና ይዘው ነው የሸፈቱት። መፍትሔው እግዚአብሔርን መካድ የመሰለው ማርክሲዝምን ርዕዮተ ዓለም አድርጎ የተነሣው የሶሻሊስት አቀንቃኝና የብሔር ፖለቲካን ቀይጦ የያዘው ወጣት የኢትዮጵያዊነት አስኳል ከውስጣቸው አውጥተው ጣሉት። በአጉል ማርክሳዊ-ሌኒናዊነት እግዚአብሔር-አልባ አደረጋቸው። ትውልዱንም ሳይቀራረብ የሚተያይ፣ በማያውቀው ታሪክ ተተብትቦ ወደኋላ እንጂ ወደፊት መራመድ የማይችል፣ ባዕድን እንደ ዘመድ፤ ዘመድን እንደ ባዕድ የሚመለከት ሽባ ትውልድ አደረጉት። እንጥፍጣፊ ሳያስቀር የኩራቱንና የክብሩን ካባ አውልቆ ጣለው፣ ኢትዮጵያዊነትን በአፍጢሙ ደፋው፣ የመንፈስ ኃይሉ ደቀቀ፣ በመጨረሻም አንገቱን ደፋ፣ ችግሩንም ሁሉ ለመፍታት የፈረንጆችን እርዳታ የሚፈልግ ትውልድ ተፈጠረ። ቀጥሎስ.....ቀጥሎ ደግሞ የኢትዮጵያ እደ ጥበብ ሠራተኞችን፦ ለምሳሌ ብረት ሰሪዎችን "ቀጥቃጭ"፣ ልብስ ሰሪዎችን "ሸማኔ"፣ ቆዳ ሰሪዎችን "ፋቂ" በማለት እንዲጠፉና ከማኅበረሰቡ እንዲገለሉ አደረገ። ይህ ቅስቀሳ በሚሲዮናውያን የተ...

የታንጉት ምስጢር

ምዕራፍ አንድ ከፋሲል ዘመነ መንግሥት ጀርሞ የሥልጣን ማዕከል ሆና የኖረችው የጎንደር ከተማ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ፤ ከአዲሱ የቴዎድሮስ ሥርዓት፤ አዲስ የጦር አበጋዞች አዲስ ሠራዊት ጋር ለመስማማት አዲስ ቅኝት ሲከረክር ድንገተኛ ከባድ እንግዳ ወይም ሠርገኛ ደሶበት የቤቱን ዕቃ የሚያተረማምሰ ባለቤት መስሏል። የሚተራመሰው ማኅበራዊ ግንኙነት ግን በወጉ ሊቀመጥ አልቻለም። ሊቀመጥም አይችልም ነበር። ጎንደር ጥንት ከተቆረቆረች፤ ፈጽሞ የተለየ አዲስ ማኅበራዊ ዛፍና ፍሬ ለምቶባት ነበር። ከተማ እንደ ማሳ ነው። ማኅበራዊ አኗኗር ማኅበራዊ አስተሳሰብ የዘራዉን ማኅበራዊ ሕይወት ያበቅላል፤ ያሸታል፤ ያፈራል፤ ማሳው በወቅቱ ካልታረመ ዝባዝንኬው እስከ ገሰሱ በርክቶ ይገኛል። ማሳው ራሱ በሚገባ ካልተያዘ እንክርዳዱም፤ እረሙም እየበዛ ሔዶ ጠቃሚ ፍሬ የማይሰጥበት ጊዜ ይመጣል። ዕዳሪ ይሆናል። የጎንደር ከተማ ማኅበራዊ ሕይወትም አንድ መቶ ስልሳ ዓመት በሚሆን ጊዜ ውስጥ እየተበላሸና ከመልካም ፍሬ ይልቅ፤ ሙጃ የበዛበት ማሳ እየሆነ ሔዶ ነበር። ፋሲል፤ ጎንደርን ሲቆረቁር ሠራዊቱ ገና መዝናናት ያልለመደ ለተግባሩ ያልተሰላቸ፤ ምቾት ገና ያላሰናነፈው፤ ትዕዛዝ አቆብቁቦ የሚጠባበቅ ትኩስ አፍለኛ ነበር። አላማም ነበረው። በሃይማኖት ምክንያት ተነሥቶ የነበረው ሁከትና የርስ በርስ ጦርነት ጨርሶ እስኪረጋጋ ከሥፍራ ሥፍራ እየተንቀሳቀሰ አጥፊ ይቀጣል። አስቸጋሪ ይነገራል። ሰላም ያስከብራል። ከጦር መሪዎቹ ሌላ በስብከት፤ በውግዘት፤ በምርቃት መንፈሳዊ ሕይወቱን የሚያንቀሳቅሱና የሚመሩ፤ ከዚያም አልፎ መስቀል ከሰላጢን ይዘው አብረውት የሚሰለፉ፤ አዲሱን የካቶሊክ ሃይማኖት ነበሩ። የነጋሹም፤ የአንጋሹም፤ የዘማቹም የቀዳሹም ማኅበራዊ ሕይወትና አስተሳሰብ በአንዳች ዐይነት የዘመቻና የዘማች መንፈስ የ...

ዕንቁጣጣሽ_እና_የከንፈር ወዳጅ

ምስል
#ዕንቁጣጣሽ_እና_የከንፈር ወዳጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ በየዓመቱ በታላቅ ስሜት ከሚያከብራቸውና ከሚያዘክራቸው በዓላት አንዱና ተወዳጅ የዘመን መለወጫ በዓል ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በየዓመቱ በታላቅ ስሜት ከሚያከብራቸውና ከሚያዘክራቸው በዓላት አንዱና ተወዳጅ የዘመን መለወጫ በዓል ነው። እንደ ዕፅዋት ሁሉ ሰው በመስከረም ላይ በተስፋ ስሜት ይለመልማል። ከቅዱስ ዮሐንስ ዋዜማ ጀምሮ በየቤቱ ጨፌና ቄጠማ ይጐዘጐዛል። አበባ በሥርዓት እየተዘጋጀ በየቦታውይቀመጣል። በተለይም ልጆች አዳዲስ ልብሳቸውን ለብሰው በደስታ ይፈነድቃሉ። በአመሻሽ ላይ ችቦ አቀጣጥለው «እዮሐ አበባዬ መስከረም ጠባዬ፣ እዮሐ የበርበሬ ውኃ፣ በሸዋ በጐንደር በትግራይ በሐረር... ያላችሁ እንዴት ከረማችሁ፣እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ። እንጉርጉሮገባሽ በየአመቱ ያምጣሽ..» እያሉ ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች (በተለይ በገጠር) ሲዘፍኑና ሲጨፍሩ ያድራሉ። የሚያበሩት ችቦና የሚያነዱት እሳት በግርማ ምሽት ሲንቀለቀል ውጋገኑ ካገር አገር ከሰፈር ሰፈር ከቦታ ቦታ ይታያል።በዕንቁጣጣሽ መዓልት በተደመረው አድባር ሰፈርተኞች ከርቀትም ከቅርበትም ይሰበሰባሉ። አባቶች ይመርቃሉ። «ዝናሙን ዝናመ ምሕረት፣ እህሉን እህለ በረከት ያድርግልን፣ ሰላም ይስጠን፣ እህል ይታፈስ፣ ገበሬ ይረስ፣ አራሽ ገበሬውን፣ ሳቢ በሬውን ይባርክ፣ ቁንጫን፣ አንበጣን፣ ትልን... ያጥፋ፣ ምቀኛን ሸረኛን ያጥፋ፣ ወጡ ገቡ ሰቡ ረቡ የሚለውን ሁሉ እግሩን ቄጠማ ዓይኑን ጨለማ ያድርገው፣ ያርገው፣ ያረገው፣...» ይባባላሉ። እናት አባት ዘመድ አዝማድ በልጆቻቸውና በወዳጅ ዘመዶቻቸው የተበረከተላቸውን የዕንግጫ ጉንጉን (የአበባ አክሊል) በራሳቸው፣ እንጀራ ማቡኪያቸው፣ በመሶባቸው፣ በወጋግራቸው... ላይ ያስራሉ። ይህም የአበባ ጉንጉን ተፈትቶና ወጥቶ የ...

ዶክተር መሀሪ ፍሰሃ ማናቸው

ምስል
#ዶክተር_መሃሪ_ፍሰሃ ማናቸው   #4 PHD #8ሁለተኛ ዲግሪ 1ዲግሪ ባለቤት ኢትዮጵያዊ ሙህር #በማኅበራዊ ሳይንስ ውስጥ የሥልጣን ጊዜ ተመራማሪ (ፒ.ዲ.) ፡፡  #በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግና በአለም አቀፍ ግንኙነቶች ተነሳሽነት ፣ በስደት ፣ በስደተኞች ጥበቃ ፣ በሰብአዊ ጣልቃ ገብነት ፣ በዲፕሎማሲ ፣ በሰላም እና በግጭቶች ባለሙያ  ፡፡  #ከሊሜሪክ - አየርላንድ የኤልኤልቢ (የሕግ እና የአውሮፓ ጥናቶች) ተመራቂ  ፣ #(MA) የአስተዳደር እና የፖለቲካ ለውጥ ከነፃ ግዛት - ደቡብ አፍሪካ ፣ (ኤምኤ) የወንጀል ፍትህ ፣ የአስተዳደር እና የፖሊስ ሳይንስ ከ ፋኩልቲ በጀርመን እና በጋንት ዩኒቨርሲቲ የሩር-ዩኒቨርስቲ ቦቹም (አር.ቢ.) ሕግ ፣ (ኤም.ኤስ.ሲ.) ከሉንድ ዩኒቨርስቲ የሕግ ሶሺዮሎጂ ፣ - ስዊድን ፣ (ኤምኤ) ከኮቨንትሪ ዩኒቨርሲቲ (ዩኬ) የሰላም ግንባታ ፣ (ኤምኤ) ዓለም አቀፍ የልማት ልምዶች ከሜሪ ኢንስቴጅ ኮሌጅ የሊሜሪክ ዩኒቨርሲቲ - አየርላንድ ፣ (ፒ.ዲ.) ከማሽሪክ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ፖሊሲ እና ማህበራዊ ሥራ - ቼክ ሪፐብሊክ ፣ (ፒ.ዲ.) ከግራናዳ ዩኒቨርሲቲ የፍልሰት ጥናቶች - እስፔን ፡፡ ከዚህም በላይ በጀርመን ፣ በስዊድን ፣ በማልታ ፣ በፖርቹጋል ፣ በሮማኒያ ፣ በአየርላንድ ፣ በሞልዶቫ ፣ በፖላንድ ፣ በኢጣሊያ ፣ በቼክ ሪፐብሊክ እና በስፔን ኮርሶችን እና ኮንፈረንሶችን ተከታትሏል ፡፡ #የስደተኞች ጥበቃ - በፖርቱጋል የሕግ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ፋኩልቲ ፣ በስቴት ልማት-የስቴት ሪፎርም-የህዝብ አስተዳደር እና የክልል ልማት ቡካሬስት የኢኮኖሚ ጥናት አካዳሚ ፣ የስደተኞች ሁኔታ ውሳኔ UNHCR እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ተቋም በጋራ ያዘጋጁት በስደት እና በስደተኞች ላይ ያሉ የሕግ ተግዳሮቶች ሎው ሳንሬሞ ፣ የድህረ ምረቃ ምር...