እጅግ በጣም የሳትነው ብዙ ነገር አለ።

እጅግ በጣም የሳትነው ብዙ ነገር አለ። እነዛ የሶሻሊዝምን ጽንሰ-ሃሳብ በውል ያልተረዱ፣ ጺማቸውንና ጠጉራቸውን የሚያሳድጉ የ60'ዎቹ ተማሪዎች "ማርክስ እንዳለው …፣ ኤንግልስ እንዳለው…፣ ሌኒን እንዳለው …፣ ማኦ እንዳለው …፣ ቼጉቬራ እንዳለው…፣ ሆቺሚኒ እንዳለው…፣ እስታሊን 

 እንዳለው…፣ " ወዘተ እያሉ ታሪካችና እሴቶቻችን እንዲጠለሽ አድርገዋል።

Twitter 

የ60'ዎቹ ትውልድ ባህሉን፣ ወጉን፣ ሥርዓቱን፣ ሥነ-ጽሑፉን፣ ታሪኩን ጭምር ነቅፎ በባዶ እጁ
ነው የሸፈተው። ከቆዳ ቀለማቸው በስተቀር የኢትዮጵያዊነትን ነባር እሴት፣ ባህል፣ ወግ፣ ታሪክ... ፍቀው የነማርክስንና የነስታሊን ፍልስፍና ይዘው ነው የሸፈቱት።

መፍትሔው እግዚአብሔርን መካድ የመሰለው ማርክሲዝምን ርዕዮተ ዓለም አድርጎ የተነሣው የሶሻሊስት አቀንቃኝና የብሔር ፖለቲካን ቀይጦ የያዘው ወጣት የኢትዮጵያዊነት አስኳል ከውስጣቸው አውጥተው ጣሉት። በአጉል ማርክሳዊ-ሌኒናዊነት እግዚአብሔር-አልባ አደረጋቸው።

ትውልዱንም ሳይቀራረብ የሚተያይ፣ በማያውቀው ታሪክ ተተብትቦ ወደኋላ እንጂ ወደፊት መራመድ የማይችል፣ ባዕድን እንደ ዘመድ፤ ዘመድን እንደ ባዕድ የሚመለከት ሽባ ትውልድ አደረጉት።
እንጥፍጣፊ ሳያስቀር የኩራቱንና የክብሩን ካባ አውልቆ ጣለው፣ ኢትዮጵያዊነትን በአፍጢሙ ደፋው፣ የመንፈስ ኃይሉ ደቀቀ፣ በመጨረሻም አንገቱን ደፋ፣ ችግሩንም ሁሉ ለመፍታት የፈረንጆችን እርዳታ የሚፈልግ ትውልድ ተፈጠረ።

ቀጥሎስ.....ቀጥሎ ደግሞ የኢትዮጵያ እደ ጥበብ ሠራተኞችን፦ ለምሳሌ ብረት ሰሪዎችን "ቀጥቃጭ"፣ ልብስ ሰሪዎችን "ሸማኔ"፣ ቆዳ ሰሪዎችን "ፋቂ" በማለት እንዲጠፉና ከማኅበረሰቡ እንዲገለሉ አደረገ። ይህ ቅስቀሳ በሚሲዮናውያን የተጀመረ ቢሆንም በዚህኛው ትውልድም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

እንዲያው ለመሆኑ ብረት ሰሪዎች ባይኖሩ ኖሮ ገበሬው በምን ያርስ ነበር? በምንስ ታጭዶ ይገባ ነበር? የኢትዮጵያ ነፃነትስ ተጠብቆ የቆየው በጦርና በጉራዴ አይደለምን? ሸማኔዎች ልብስ ባይሸምኑ፣ ሴቶች ጥጥ ባይፈትሉ፣ ገበሬው ጥጥ ባይዘራ ኖሮ ምን እንለብስ ነበር? ቆዳ ሠራተኞች ባይኖሩ ኖሩ አርበኞቻችን በጦርነት ጊዜ የሚለብሱት ጋሻ ከዬት ይመጣ ነበር። ይህን ጋሻ የሠራ ሰው እንደምን ይናቃል?

Facebook 

አሁን ይሄን የሚያስተካክል የተፍታታ፣ የነቃ፣ የበቃ ትውልድ ያስፈልገናል። መንቃትና መነሳት አለብን። በጣም የሚያስገርመው ያለፈው ትውልድ የመሬት ልብ እየሰነጠቀ ሐውልት ገንብቷን፤ ቤተ መቅደስ አንጿል፤ ሀገር ከነነፃንቱ አስረክቧል፤ ነገርግን
ጥንት ከነበረው ትውልድ ተከታታይ ትውልዶች አንድ እርከን ወደላይ አላሳደገውም። ሌላው ቀርቶ
ከአንድ ዓለት ተፈልፍሎ የተሠራው የላሊበላ ኪነ-ሕንፃ ግማሹ ወድቆ ተሰባብሯል የሚጠግነው ትውልድ ገና አልመጣም? 

website 


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)