ታጠቅ

#ዓጼ ቴወድሮስ የቋራ አስተዳዳሪ የነበሩት ደጃዝማች ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደ ጊዮርጊስ (ባጭሩ ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ) ልጅ ናቸው። እናታቸው ወይዘሮ አትጠገብ ወንድበወሰን ሲባሉ አመጣጣቸውም ከጎንደር ከተማ ባላባቶች ነበር። የወይዘሮ አትጠገብ እናት ወይዘሮ ትሻል ስትባል የበጌምድር ክፍል መሳፍንት ዘር ነበረች፣ በአባቷ በኩል አያቷ ራስ ወዳጆ በዘመናቸው ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው ባላባት ነበሩ። የወይዘሮ አትጠገብ ድህነት በታሪክ መጻህፍት በተደጋጋሚ የሚጠቀስ ቢሆንም አመጣጡ እንዲህ ነበር፡ የህጻኑ ቴወድሮስ አባት ደጃች ሃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ ከሱዳኖች ጋር በተነሳ ጦርነት በጀግንነት ሲወድቁ እናት ገና ሁለት አመት የሆነውን ልጇን ይዛ ከቋራ ወደ ጎንደር ከተማ ሄደች። በዚህ ወቅት ሁለተኛ ላታገባ በመቁረብ ልጇን ብቻዋን ማሳደግ ግድ አላት። አንዳንዶች በዚህ ምክንያት እራሷን ለማስተዳደር ኮሶ ትሸጥ ነበር ሲሉ ጸሃፊው ጳውሎስ ኞኞ ወይዘሮ አትጠገብ መቼውንም ኮሶ አትሸጥም ነበር ይላል (ኮሶ ትሸጥ ነበር የሚለው የልጁ ጠላቶች ፈጠራ ወሬ ነበር በማለት ያስረዳል)። ሆኖም ቀረ ህጻኑ ቴወድሮስ በድህነት እንዳላደገ ሁሉም የታሪክ ጸሃፊያን ይስማማሉ።

አንድ ለናቱ ቴወድሮስ በእናቱ በኩል እህትም ሆነ ወንድም አልነበረውም። የወደፊቱ አጼ ቴዎድሮስ በ፲፰፻፴፱ ዓ.ም. ተዋበች አሊ የተባለችውን የዘመነ መሳፍንት ታላቅ ባላባት፣ የራስ አሊ አሉላን፣ ልጅ አገባ። ተዋበች በጊዜው የ፲፭ ዓመት ወጣት የነበረች ሲሆን ቁንጅናዋና አስተሳሰቡዋ በጊዜው በነበሩ ሰወች ዘንድ የተደነቀ ነበር። ሁለቱ በፍቅር በመውደቃቸው ቴወድሮስ በአባቷ ራስ አሊና በአያቷ እቴጌ መነን ላይ ሲያምጽ ባሏን ትደግፍ ነበር።

አጼ ቴወድሮስ የሚስታቸውን መታመም ከዘመቻ መልስ በ፲፰፻፵፰ ዓ.ም ላይ ከሰሙ በኋላ እቴጌ ተዋበች በ፲፰፻፶ አረፉ። በኃዘኑ ወቅት

እስቲ ጠይቁልኝ እርቃ ሳትሄድ
እትጌ ተዋበች ሚስት እናት ገረድ?
ብለው እንደተቀኙ በታሪክ መዛግብት ሰፍሮ ይገኛል።

ከሁለት ዓመት ሀዘን በኋላ በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም ዓፄ ቴዎድሮስ ከሁለተኛ ሚስታቸው ጋር ተገናኙ። «ደራስጌ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀምጠው ሳለ አንድ ወታደራቸው ወደ ርሳቸው ቀረበና «ጌታየ፣ አንዲት ሴት አገኘሁ፣ ፊቷም እንደ ፀሐይ የሚያበራ ነው።» ልጅቱም በኋላ ወደ ቤተመንግሥት ቀረበች፣ ስሟም ጥሩነሽ ውቤ፣ የደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ልጅ ነበረች። ንጉሱም አይተዋት "እውነትም ወርቅ ናት" በማለት አገቧት። በዚህ ወቅት ንጉሠ ነገሥቱ አባቷን ራስ ውቤን አስረዋቸው ነበር። ራስ ውቤ የሰሜን፣ወልቃይት ፣ፀገዴ፣ትግራይ፣ ሰራየ፣ ሐማሴንና አንጎት (ሰሜን ወሎ) አስተዳዳሪ ሲሆኑ ከዓፄ ፋሲለደስ የሚወለዱ ስለነበሩ ለንጉሥነት የሚገዳደሩ ነበሩ። የጥሩወርቅ (ጥሩነሽ) እናት ደግሞ ወይዘሮ ላቂያየ የተባሉ የትግራይ መሳፍንት ዘር ነበሩ። ከኒህ ሚስታቸው ደጃዝማች ዓለማየሁ ቴዎድሮስ የተባለውን ከሁሉ በላይ የሚወዱትን፣ እርሳቸውን እንዲተካ ያጩትን ልጅ ወለዱ። ዓፄ ቴዎድሮስ በአጠቃላይ ፬ ጊዜ ሲያገቡ ፮ ወንድና ፫ ሴት ልጆች ነበሯቸው፣ እነርሱም፦

ወንድ ልጆች ሴት ልጆች ያልተረጋገጠ
፩) ራስ እንግዳ ቴወድሮስ - (የተዋበች ወይም እንግዳወርቅ? ልጅ) 1833 ላይ የተወለዱ። በመቅደላ ጦርነት የተገድሉ። 3ቱ ልጆቹ በእንግሊዞች የታሰሩ። ፩) ወይዘሮ አልጣሽ ቴዎድሮስ -- (ከሁለተኛ ሚስት) መጀመሪያ ጊዜ ከዳግማዊ ምኒልክ ጋር ጥር 1856 ላይ በመቅደላ የተዳሩ። ሁለተኛ ጊዜ ከራስ ባሪያው ጳውሎስ፣ የትግራይ መስፍን ጋር ተጋቡ። ጥቅምት 1882 አረፉ ፩) ፒተር ኡስቲኖቭ - የእንግሊዙ ታዋቂ ጸሃፊ፣ ተዋናይና ድራማ ሰሪ ፒተር ኡስቲኖቭ ቅድም አያቱ የቴወድሮስ ሴት ልጅ እንደነበረች ይናገራል። [2] ተመራማሪወች ቅድም አያቱ እሳተወርቅ የተባለች መቃዶ የተባለ የጎንደር ወታደር ልጅ ናት ይላሉ። [3]
፪) ራስ መሸሻ ቴወድሮስ - (የተዋበች ልጅ) 1840 ላይ የተወለዱ። ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክን ከመቅደላ እንዲያመልጡ የረዱ። በአባታቸው የደጃዝማችነት ማዕረግ ተሰጧቸው በኋላ በዳግማዊ ምኒልክ ራስ የሆኑ። ልጆቻቸው
ደጃዝማች ካሳ መሸሻ - የጎንደር አስተዳዳሪ
፪)ስማቸው ያልታወቀ
፫) ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ - (የጥሩነሽ ውቤ ልጅ) 1853 ላይ የተወለዱ። ሊድስ፣ ዮርክሻየር፣ እንግሊዝ አገር በ1870 ዓ.ም ያረፉ። ፫)ስማቸው ያልታወቀ ... ልጅ አላማ ጉዋሉን ያገቡ
፬) ልጅ ኃይለማርያም ቴዎድሮስ - (ሁለተኛ ሚስት)
፭) ልጅ ይማም ቴዎድሮስ -- (ላቀች ወይም ጣይቱ)
፮) ልጅ ተሰማድንገት ቴዎድሮስ --(ሁለተኛ ሚስት

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ)