ልጥፎች

የሞተ አማራን አይነሳም ብሎ ማመን ይቻላል ነገር ግን የተዳከመ አማራን አይነሳም ብሎ መዘናጋት ቂልነት ነው” ሩዶልፍ ግራዚያኒ ለምስራቅ አፍሪካ ኮሎኒ አስተዳዳሪዎች ከፃፈው ሜሞ የተወሰደ ኢትዮጵያም ውስጥ በውጭም ያሉ ብዙ ሀይሎች ለአማራ መደራጀት እጅግ ድንጉጥ ናቸው። በእንስሳት አለም ውስጥ አንበሳ ወደ ሜዳው ሲገባ ድኩላ መደንገጡ ተፈጥሯዊ ነው ። አማራ ተደራጀ ሲባል መደንገጡና መርበትበቱ የዛሬ ጊዜ እውነታ ብቻ ሳይሆን ታሪካዊ መሰረትም አለው። በአንድ ሁለት ምሳሌ እንመልከተው ። 1~   በ1930ዎቹ አዲስ አበባ ውስጥ በድፕሎማትነትና የምእራባውያን የስለላ ድርጅት ወኪል ሆኖ ይሰራ የነበረው ባሮን ሮማን ፕሮችስካ ለምእራበውያን በፃፈው Abyssenya the powder barrel “የሚል ርእስ ባለው መፅሀፉ ገፅ 3 ላይ ” The African Menace በሚለው ምእራፍ ስር እንደዚህ በማለት ፅፏል… … “ምእራባውያን ወገኖቼ ስሙኝ በምስራቅ አፍሪካ በምትገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ አማራ የሚባል ብሄር አለ ። ይሄ ብሄር እኛ ምእራባውያን በአፍሪካ በምናደርገው የመስፋፋት ፖሊሲ ትልቅ እንቅፋት ነው። አማራ ከተደራጄ እንኳን ለአፍሪካ ለእኛም ትልቅ ስጋት ስለሆነ በዚህ ህዝብ ላይ እያንዳንዱ ምእራባዊ ሀገር የሚከተለው ፖሊሲ ከዚህ አንፃር መቃኘት አለበት ።” በማለት ፅፏል። በነገራችን ላይ ይሄ መፅሀፍ ላለፉት 70 እና 80 አመታት ምእራባውያን በኢትዮጵያ ላይ ለሚያወጡት ፖሊሲ እንደ ግብአት ሲጠቀሙበት ኖረዋል። 2~ በፋሽስት ኢጣሊያ የአምስት አመት ወረራ ወቅት የምስራቅ አፍሪካ ኮሎኒ አስተዳዳሪ የነበረው ሩዶልፍ ግራዚያኒም ለቀጠናው አስተዳዳሪዎች በፃፈው Memo ማስታወሻ እንደዚህ ይላል… … ” ከሁሉም መርሳት የሌለባችሁ አማራን ነው። በሁለት በሶስት እንኳን እ...

Chemical Formula

 file:///storage/emulated/0/Chemical formula.pdf https://www.ambachewmu3.blogspot.com

ደስታ

 “ደስተኛ የምሆነው የራሴ ቤት ሲኖረኝ ነው።” “ደስተኛ የምሆነው የምፈልገውን ሥራ ካገኘሁ ነው።” “ደስተኛ የምሆነው . . .” አንተስ እንደዚህ ተሰምቶህ ያውቃል? ግብህ ላይ ከደረስክ ወይም የተመኘኸውን ነገር ካገኘህ በኋላስ ደስታህ ዘላቂ ሆኗል? ወይስ ቀስ በቀስ መክሰም ጀምሯል? ግባችን ላይ ስንደርስ ወይም የተመኘነውን ነገር ስናገኝ ደስተኛ እንደምንሆን የተረጋገጠ ቢሆንም እንዲህ ዓይነቱ ደስታ ቀስ በቀስ እየከሰመ ሊሄድ ይችላል። ዘላቂ ደስታ የሚኖረን ስኬት ወይም አንድ ዓይነት ንብረት ስላገኘን አይደለም። ከዚህ ይልቅ አንድ ሰው ጤናማ መሆኑ በተለያዩ ነገሮች ላይ የተመካ እንደሆነ ሁሉ እውነተኛ ደስታም የተለያዩ ነገሮች ድምር ውጤት ነው። ሁላችንም የተለያየን ሰዎች ነን። አንተን የሚያስደስትህ ነገር ሌላውን ሰው ላያስደስተው ይችላል። በተጨማሪም ዕድሜያችን እየጨመረ ሲሄድ ፍላጎታችንም ይለወጣል። ሆኖም ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙት አብዛኛውን ጊዜ እውነተኛ ደስታ ከማግኘት ጋር ተያይዘው የሚጠቀሱ አንዳንድ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ያህል ባለን ረክተን መኖር፣ ምቀኝነትን ማስወገድ፣ ለሌሎች ፍቅር ማሳየት እንዲሁም ችግሮችን ተቋቁሞ የማለፍ ችሎታ ማዳበር ለእውነተኛ ደስታ ቁልፍ የሆኑ ነገሮች ናቸው። እንዲህ የምንለው ለምን እንደሆነ እስቲ እንመልከት።  1. ባለን ረክተን መኖር የሰውን ተፈጥሮ በሚገባ ያጠና አንድ ጠቢብ ሰው “ገንዘብ ጥላ ከለላ [ነው]” በማለት ተናግሯል። ይሁን እንጂ “ገንዘብን የሚወድ፣ ገንዘብ አይበቃውም፤ ብልጽግናም የሚወድ፣ በትርፉ አይረካም፤ ይህም ከንቱ ነው” ሲልም ጽፏል። (መክብብ 5:10፤ 7:12) ይህ ጠቢብ ሰው ለማስተላለፍ የፈለገው ቁም ነገር ምንድን ነው? ለመኖር ገንዘብ እንደሚያስፈልገን ግልጽ ቢሆንም ስግብግብነት እንዳይጠና...