የሞተ አማራን አይነሳም ብሎ ማመን ይቻላል ነገር ግን የተዳከመ አማራን አይነሳም ብሎ መዘናጋት ቂልነት ነው”


ሩዶልፍ ግራዚያኒ ለምስራቅ አፍሪካ ኮሎኒ አስተዳዳሪዎች ከፃፈው ሜሞ የተወሰደ


ኢትዮጵያም ውስጥ በውጭም ያሉ ብዙ ሀይሎች ለአማራ መደራጀት እጅግ ድንጉጥ ናቸው። በእንስሳት አለም ውስጥ አንበሳ ወደ ሜዳው ሲገባ ድኩላ መደንገጡ ተፈጥሯዊ ነው ። አማራ ተደራጀ ሲባል መደንገጡና መርበትበቱ የዛሬ ጊዜ እውነታ ብቻ ሳይሆን ታሪካዊ መሰረትም አለው።


በአንድ ሁለት ምሳሌ እንመልከተው ።


1~   በ1930ዎቹ አዲስ አበባ ውስጥ በድፕሎማትነትና የምእራባውያን የስለላ ድርጅት ወኪል ሆኖ ይሰራ የነበረው ባሮን ሮማን ፕሮችስካ ለምእራበውያን በፃፈው Abyssenya the powder barrel “የሚል ርእስ ባለው መፅሀፉ ገፅ 3 ላይ ” The African Menace በሚለው ምእራፍ ስር እንደዚህ በማለት ፅፏል… … “ምእራባውያን ወገኖቼ ስሙኝ በምስራቅ አፍሪካ በምትገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ አማራ የሚባል ብሄር አለ ። ይሄ ብሄር እኛ ምእራባውያን በአፍሪካ በምናደርገው የመስፋፋት ፖሊሲ ትልቅ እንቅፋት ነው። አማራ ከተደራጄ እንኳን ለአፍሪካ ለእኛም ትልቅ ስጋት ስለሆነ በዚህ ህዝብ ላይ እያንዳንዱ ምእራባዊ ሀገር የሚከተለው ፖሊሲ ከዚህ አንፃር መቃኘት አለበት ።” በማለት ፅፏል።

በነገራችን ላይ ይሄ መፅሀፍ ላለፉት 70 እና 80 አመታት ምእራባውያን በኢትዮጵያ ላይ ለሚያወጡት ፖሊሲ እንደ ግብአት ሲጠቀሙበት ኖረዋል።


2~ በፋሽስት ኢጣሊያ የአምስት አመት ወረራ ወቅት የምስራቅ አፍሪካ ኮሎኒ አስተዳዳሪ የነበረው ሩዶልፍ ግራዚያኒም ለቀጠናው አስተዳዳሪዎች በፃፈው Memo ማስታወሻ እንደዚህ ይላል… …


” ከሁሉም መርሳት የሌለባችሁ አማራን ነው። በሁለት በሶስት እንኳን እንዳይደራጅ ጠብቁ ። አማራ ለጊዜው የተሸነፈ መስሎን አንገቱን ቢደፋ ቀን ጠብቆ ብድግ ማለቱ አይቀርም። የሞተ አማራን አይነሳም ብሎ ማመን እንጅ የተዳከመ አማራን አይነሳም ብሎ መዘናጋት ቂልነት ነው።” ፕሮፌሰር አልቤርቶ ስባኪ “Ethiopian under Mussoloni and fascist Experience በሚለው መፅሀፉ ላይ ፅፏል።


በአገር ውስጥ ያለውንና “አማራ ተደራጀ ” ሲባል Panic የሚያደርገው እጅግ በጣም ብዙ ከመሆኑ ስንቱን ጠቅሸ እዘልቀዋለሁኝ ። አንድ ምሳሌ ብቻ ጠቅሼ የፌስቡኩም ግድግዳ ስለማይበቃ ብተወው ነው የሚሻለው።


መለስ ዜናዊና ህውሃት በየጫካውና በየሰርጡ ከባድ መሳሪያ ታጥቆ ከሚርመሰመሰው ወደ ሃምሳ ሺህ ከሚጠጋው የኦነግ ሰራዊት ይልቅ ቸርችል ጎዳና ላይ ያለችው ቢሮ ውስጥ የሚቀመጠው ፕሮፌሰር አስራት ሲያስደነግጠው ኖሯል። ህውሃት አሁንም በህይወት ካለው ሌንጮ ለታና ኦነግ በበለጠ ስላሴ ቤተክርስቲያን በሰላም ያረፈው ፕሮፌሰር አስራት መንፈስ ያስደነብረዋል። የኦነግም የአማራ ፍርሃት ቢበዛ እንጅ አያንስም።


ትናንሽ ካፊያ እየተጠራቀመ ውሽንፍራም ዝናብ ይሆናል፡፡ ከዚያም ጎርፍና ወጀብ ይበረታል፡፡ የአማራ ህዝብ ላለፉት 27 አመታት የተፈራረቁበትን የመብት ረገጣ፣ የነፃነት መታፈን፣ የፍትህ እጦትና፣ የአድሏዊ አሰራር ግፍና በደል የፈጠረበትን ሰዋዊ ስሜት የሚከላከሉበትና “የማርያም መንገድ” የሚያገኝበት፣ ጎጆ እንቀልስ ብለው ሲሰባሰቡ ቢጫ ወባ እንደያዘው ሰው የሚያንቀጠቅጠው ብዙ ነው።


አማራ ባለፉት አመታት የማዕበል ገፈት ቀማሽና ተቋዳሽ በመሆን ብዙ ጉዳት አስተናግዷል ። ይሄ የሚቀጥልበት መንገድ ግን በፍፁም መቆም አለበት ። ይሄን የሚያስቆመው ደሞ የተበታተነ ሀይል ሳይሆን የተደራጀ ሀይል መሆኑን የተረዱ ወጣቶች ጀምረውታል። አማራ በተግባር ሲደራጅ ከምእራብ እስከ ምስራቅ ከሰሜን እስከደቡብ ድንኳን ዘርግቶ ሙሾ ማውረድ ይቻላል ማስቆም ግን ፈፅሞ አይቻልም።


በመጨረሻ አንድ ነገር ግን ሳይመረመር የሚገባን አለ። አዲሱ ማሸነፉ አይቀሬ ነው -The new is invincible ይለዋል የጥንቱ የጠዋቱ ፍልስፍና፡፡ አሮጌው እያረጀና እያገረጀፈ የመሄዱን ያህል፣ አዲሱ እየተፈለፈለ ማደሩ ግድ ነው።የአልገዛም ባይነት ስሜት ከሥር እየጋለ መምጣቱና፣ የላይኛው ወገን እንደ ትላንቱ ካልገዛሁ የሚልበት ትንቅንቅ መቀጠሉ፣ በአሮጌው ተሸናፊነት እንደሚያበቃ ታሪክ ይነግረናል፡፡ አዲሱ የአማራ ትውልድ አሸናፊ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም። ታሪኩም ፣ፖለቲካውም እውነታውም ይሄው ነው።


****************


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)