ክብር ለደርግ
““አሁን የደርግ ሠራዊት ጨፍጫፊ ፣ ደፋሪ፣ ዘራፊ እየተባላችሁ በክፋትና በእብደታዊ ድንቁርና የታጨቀ የተሳሳተ ትርክት
ሲነገራችሁ ያደጋችሁ የዚህ ትውልድ ጓደኞቼ እውነቱን አሁን በአይናችሁ አያችሁት አይደል? እንዳለመታደል ሆኖ ሀገር
በገንዘብ ተለውጣ ማፊያዎቹ ቀን ወጥቶላቸው በሆዳም ሹመኞች እየተመሩ ቅድስቲቷን ሀገር አረከሷት። የደርግ የተባለው ያ ድንቅ የኢትዮጵያ ሠራዊት ያኔም የተዋጋው ይህን ማፊያ ቡድን ነበር ዛሬም መከላከያ ሠራዊታችን እየተዋጋ ያለው እነዚህኑ ማፊያዎች ነው እንኳን ከታሪክ ትርክት ተላቆ ትውልዱ እውነቱን በአይኑ አየ። ሀገር መገነጣጠል፣ በዘር ማፋጀት፣ እልፍ ዜጎችን ለስደት መዳረግ ከነአካቴውም ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንዳትኖር ነበር የዛሬ 45 አመት ጫካ የገባው ይኸው ዛሬ ድረስ ይህን አላማውን ለማስፈፀም የሀገር ሀብት ያወድማል ህዝብ እንዳይስማማ ለጦርነት ይማግዳል።”
“ከአማራ ልዩ ሀይል ና ሚሊሺያ የተማርኩት አስገራሚ ነገር፣ የህወሓት ገዳይ ቡድን ሳምረ በሚል መጠሪያ ተደራጅቶ
በእነ ኮሎኔል የማነ ገ/ሚካኤል ንፁሃን አማራዎች በማይካድራ በሳንጃ ና በገጀራ ሲጨፈጨፉ ፤ አስከሬናቸው በጫካ እየተገኘ
አሰቃቂ ነገር እየተመለከቱ እነዚህ የአማራ ልዩ ሀይሎች ግን እጅግ በረቀቀ ወታደራዊ ድሲፕሊን ጠላትን ብቻ ነጥለው
በመምታት ፤ የማረኩትን የህወሓት ልዩ ሀይል ምግብና ውሀ ከራሳቸው አንስተው እየሰጡ ይኸው መቀሌን እስከ መክበብ
ደርሶዋል ፤ በእውነት ይኸ ልዩ ክብር የሚሰጣቸው ጉዳይ ነው፤ በጣም ገርሞኛል።”
“ሳምሪ የሚባል ቡድን የለም ሕወሃት እንጂ፣ ወልቃይቴ የሚባል ብሔርም የለም አማራ እንጂ፡፡ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ሕወሃት
ምንም ያልታጠቁ 600 የአማራ ህዝብን ጨፍጭፈዋል። ይህም የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው። በሰሜን እዝም እንዲሁ በሺህ
የሚቆሩ ብሔራቸው አማራዎች ናቸው ብሎ ያሰባቸውን ወታደሮች በሙሉ በስራና በግብዣ በማዘናጋት ከሀሉም በተለየ
መንገድ ገድለዋል አቃጥለዋል በእሬሳቸው ላይ ጨፍረዋል። እኛም ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድና ትውልድ ይህን እንዲያውቅ መዝግበን ይዘናል። በተረፈ ወልቃይቴ ተገደለ ሳምሪዎች ይህን አደረጉ የምትሉ ሰዎችና ተቋማት ከዚህ የማለባበስና የመደምሰስ ድርጊታችሁ የማትቆጠቡ ከሆነ ከተባባሪነት ተለይታችሁ አትታዩም። ወንጀለኛም ተጎጂም በማንነቱ ይጠራ ዘንድ ህግ ያዛል።
የምንገነባት ሀገር ከይሉኝታ ከሴራና ከአድልዎ ነጻ እንድትሆን መሰል መንሸራተቶች እርምት ሊወሰድባቸው ይገባል።”
“ተተኪ እንዳለው ባወቀ፣ ሞት እንዲህ ባልተጨነቀ። ነው ያሉት ያ የሕወሀት ሴጣኖች ፈጣሪና ፈልፋይ መለስ ዜናዊ የሞተ
ጊዜ አርቲስቶች ተብዬዎቹ። ተተኪ አለው ያሉት ሰው ተተኪዎቹ እዩዋቸው ምን እየሰሩ ነው ያሉት። ተተኪ ማለት ጨፍጫፊ
ማለት ነው።ለማንኛውም መለስ ዜናዊ እንኳን ለአገር ለራሷ ለሕወሀት የሚሆን ሰው ሳያፈራ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል
መርህ ሲመራ የነበረ ሰው ለመሆኑ አሁን የሕወሀት ጁንታ የፈፀማቸውን ጭፍጨፋ በማየት ማረጋገጥ ይቻላል። መለስ ዜናዊ ነፍስህን አይማረው!!”
“፩) የጥቁርና ነጭ ሰው ደም ቀይ ነው!! አባቶቻችን የነጭ የበላይነትን ተቃውመው የላቀ መስዋዕትነትን የከፈሉት ሰው
ሁሉ ዕኩል ነው በሚለው ሃቅ ነው። በዚህ ዕሳቤ ለነጮች የሚደነብር ዋጃግንት ትናንት አባቶቻቸው ለጣሊያን ፋሽስት
እንቁላል ሲቀቅሉ የነበሩ የባንዳ የልጅ ልጆች ናቸው። በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚገባ ወይም እገባለሁ የሚል ሁሉ ወደ
ወጪ ብለን አዝዘናል!! በላይ ይሙት!! ፪) የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዳይሬክተር የሆኑት የጁንታው ቡድን ወኪል ‘ዶ/ር
ቴዎድሮስ አድሃኖም በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ክስ ሊመሰረትባቸው ነው’ የሚለው ከበሮ ድለቃ የነጭ
አምላኪነት ውርስ ነው። ዶ/ር ቴዲ በልደታ ፍ/ቤት ተዳኝተው ቀሪ እድሜያቸውን ቂሊንጦ፣ ቃሊቲ፣ ሽዋ ሮቢት (ሽዋ ፈረስ
ቤትም ኢመቸኛል!!) ወይም ዝዋይ ሊያሳልፉ ይገባል።
“ጨካኞች አሳፋሪ ታሪክ በሰሩባት ሀገራቸው እና መደበቂያ ምሽግ ባደረጓት ትግራይ ባንዲራዎች መካከል በተጣበበች
ሽንቁር ቢሯቸው፣ በደከመ አንደበታቸው፣ በሰለቸና በጥቂት በሳምንታት ውስጥ በተጎሳቆለ ፊታቸው፣ በተቆራረጠ
ድምፃቸው፣ በከፍተኛ ስጋትና ፍርሃት ውስጥ መገኘታቸውን በገህድ በሚያሳብቅ ቁመናቸው የሚሰጡት መግለጫ ተቋርጧል::
አዲሱ ከመሸ የመጣው ቃል አቀባይም የተለመደ ውሸታቸውን አጣጥሞ ሳይናገር መሽቶበት በተቆራረጠ ስልክ ለማውራት
ተገዷል:: አሁን ሁሉም ነገር እያለቀ ነው:: የቀረችው መቀሌ ናት:: ዙሪያዋን የተቆፈረባት ምሽግ እና የተጠመደባት ፈንጅ
ከእይታችን ውጭ አይደለም:: አሸባሪው ቡድን ከሞት የተረፉ ዕድሜና ማጭበርበር ጠገብ አዛውንቶችን ማምሻም ዕድሜ ነው ብሎ ለማስጠበቅ መፍጨርጨሩ እንደማይቀር ገሀድ ዕውነታ ነው:: የዚህን ቡድን በደም የተጨማለቀ ወንጀለኝነት ካስተዋልን
የመቀሌን ህዝብም ለእልቂት ዳርጎ መትረፍ ወይም መጥፋት አያስብም አይባልም:: እንደ ፍልፈል በማሳቸው የቀበሮ ጉድጓዶች ውስጥ ተወትፎ ወይም ራሱን ቀይሮ እና አታሎ ለመሰዎር ሲሞክር መያዙ አይቀርም:: ሁላችንም እርግጠኞች የምንሆነው ግን ፊት ለፊት ተዋግቶ ለመሞት እንደማይወስን ነው:: ምክንያቱም ገዳይ አስገዳይ ዘራፊ እና ስግብግብ ሌባ እንጅ ጀግና አይደለምና:: ኢትዮጵያ በጀግኖቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!”
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ