ሳይበር ጦርነት

 አሜሪካና ሩሲያ ሕዋ ላይ 

የጦር መሳሪያ ያንቀሳቅሳሉ 

ሲባል ሰምተናል! ይህ ሁሉ 

የሚተገበረው በሳይበር 

ቴክኖሎጂ ስለመሆኑ አንጠራጠርም! ይህ 

በእንዲህ እንዳለ ስለማናዉቀው ዓለም 

ከማዉራታችን በፊት በሳይበር ጥቃት 

ስለሚከወኑ ጦርነቶች ብናወራ የተሻለ 

ይሆናል፡፡ እንግሊዛዊው ቻርለስ ዳርዊን የሰው 

ልጅ እዚህ ደረጃ የመገኘቱ ምሥጢር ዝግመተ 

ለዉጥ ነው ይለናል በሳይንስ እይታው! ይህን 

የዳርዊን መነጽር የጦርነትን ዝግመተ ለዉጥ 

ብናስረዳበት ይሻላል፡፡ የጦርነት ቴክኖሎጂ ቀስ 

በቀስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ የሰው ልጅ 

ከደረሰበት ሥልጣኔ ጋር እኩል አብሮ የተጓዘ 

ለዉጥ ነው፤ ለዚህም ራቅ ብሎ መጀመር 

አያስፈልግም የአድዋዉን ድል ማሰብ በቂ 

ነው፡፡ አድዋ ላይ ከጠላት ጋር የተደረገው 

እልህ አስጨራሽ ጦርነት ፊትና ፊት በባህላዊ 

የጦር መሣሪያዎች የተማከቹበት ነው፡፡ 

ጦርነት ከእንደነዚህ ዐይነት መሰል ድርጊቶች 

ተነስቶ ዛሬ ላይ የቴክኖሎጂ ውጤት በሆነው 

ሳይበር ላይ ደርሶ ጦርነቶች በሳይበር ጥቃት 

እየተጋጋሉ ይገኛሉ፡፡ ጦርነቱም በድምጽ 

የለሽ አድቢዎች ይካሄዳል፤ ወይም ጥይት 

በማያጮሁ ጦረኞች ይተኮሳል፡፡ ተኩሶቹም 

ዒላማቸውን እንዲጠብቁ ተደርገው ይሰነዘራሉ፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአሁኑ ጊዜ 

በዓለማችን በጦር መሳሪያ ከሚደረገዉ 

ጦርነት ይልቅ የሳይበር ጥቃቶች እና ዲጂታል 

የስለላ ሥራዎች በሀገራት ብሔራዊ ደህንነት 

ላይ ትልቅ ስጋት እያሳደሩ ነዉ። ሳይበር 

የአገልግሎቱ ደህንነት የተረጋገጠ ካልሆነ 

በአሉታዊ ጎኑ የሚፈጥራቸው ቀውሶች ቀላል 

አይደሉም፡፡ የሳይበር ጥቃት ሆን ተብሎ 

ያልተፈቀዱ የኮምፒውተር ሥርዓቶችን 

መሠረተ ልማቶች እና ኔትዎርኮች ላይ 

አጥፊ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም በሕገወጥ 

መንገድ ዳታዎችን መበዝበዝ እና አገልግሎት 

የማስተጓጎል ተግባር ነው፡፡ ስለዚህም የሳይበር 

ጥቃት ጦርነቶች በግለሰብና ግለሰብ በግለሰብና 

ተቋማት፤ በተቋማትና ተቋማት እንዲሁም 

በዋናነት በሃገርና ሃገራት በኩል ከፍተኛ የጦር 

ሜዳ ዉጊያ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ አንድ ሀገር 

ምንም እንኳ በራሷ ሉአላዊነቷን አስጠብቃ 

የምትተዳደር ቢሆንም የግድ ያለተቃርኖ 

መኖር አትችልም፡፡ ለዚህም የምትከተላቸው 

የፖለቲካ ኢኮኖሚና ማኅበራዊ ትስስሮች 

ተቃርኖዎችን እንድታስተናግድ ትገደዳለች! 

የሳይበር ጥቃት ጦርነት በሃገር ላይ 

ከሚያደርሰው ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ፣ 

አካላዊ/ዲጂታል ሥነ-ልቦናዊ፣ ማህበራዊ እና 

መልካም ስምን ከማጉደፍ አንጻር ሕዝብን 

ወደ እርስ በእርስ ግጭት የፖለቲካ ቀውስ 

የሕዝብ አመኔታ ማጣት የገንዘብ ስርቆት 

የማኅበረሰብ ቀውስ የአገልግሎት መቋረጥ 

የሀገር ሉዓላዊነት ማሳጣት የመሠረተ 

ልማቶችን አገልግሎት ከማቋረጥ አኳያ 

የሳይበር ደህንነት እንዲሁ የዋዛ ፈዛዛ 

መታየት የሌለበት መከላከል ያለበት ዉጊያ 

ነው፤ ለዚህም የሳይበር ጦር ሸማቂዎች እንደ 

ተልዕኮና ዓላማቸው ጥቃት የሚያደርሱበትን 

ተቋም አስቀድመው በግልጽ ይገነዘባሉ! እንደ 

ሰላም ሚኒስቴር የፋይናንስ ደህንነት መረጃ 

ማዕከል ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ብሔራዊ 

የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን 

የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ 

የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሣኝ ኩነት ኤጀንሲ 

የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ 

ጥናት ኢንስቲትዩት ሁሉ በዋነኝነት ሰለባዎች 

መሆናችው እጅጉን ጥንቃቄ ይሻሉ፡፡

ከወራት በፊት ኢቢሲ በዘገባው 

እንዳስደመጠን ኢትዮጵያን ጨምሮ በ150 

አገራት የተከሰተውና “ዲክሪፕት ዎነክራይ” 

በመባል የሚታወቀው የሳይበር ጥቃት ኢላማ 

አድርጓቸዋል የተባለው የቴሌ ኮሚዩኒኬሽን 

መሠረተ ልማት የገንዘብና ፋይናንስ 

የኤሌክትሪክና ኢንዱስትሪ መቆጣጠሪያ 

ሥርዓትና ሆስፒታሎች ዋነኞቹ እንደሆኑ 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ 

ማሳሰቡ ይታወሳል።

የሳይበር ጦርነቶች የራሳቸው ዓላማና ግብ 

አላቸው! በተለይ ጂኦፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ 

አንድምታዎችን እቅድ አድርጎ የሚነሳ ዉጊያ 

ነው፡፡ በኛ ሀገር እንኳን ብንመለከት ፖለቲካዊ 

የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ለማድረስ ከግብጽ 

በኩል መሰንዘሩን ሰምተናል፡፡ እንዲህ ያሉ 

የጂኦ ፖለቲካዊ ጦርነቶች ብዙውን ጊዜ ዝም 

ተብለው የሚታለፉ ሳይሆን ከፍተኛ ምርመራ 

መደረግ የሚገባቸው ናቸው፤ ጂኦፖለቲካዊ 

ጥቃቶች የሚመረመሩበት ምክንያቶች ለብዙ 

የሳይበር ጥቃቶች ምላሽ ስለሚሰጡ ነው። 

የጸረ ሳይበር አጥኚዎች ማንኛዉንም የደኅንነት 

ጥቃቶች ከጂኦፖለቲክስ ጋር አጋብተው 

የሚተነትኑት ምክንያት ለዚሁ በመሆኑ ነው

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ)