ሌባ

 ሌቦች ጋር ተሆኖ ሌባ-ሻይ መሆን አይቻልም፡፡ 

 ስርቆት የፈለገ ወደ ወያኔ ፤ ለውጥ የምንፈልግ #ክእውነት ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንጋዝ

 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እውነትን ስንጋፈጥ እድገትንና ለውጥን እናያለን

ፖለቲካ ማሸነፍ እና መሸነፍ ሳይሆን ስራ ነው፡፡


ጥያቄው ለእኔ ፤ያለው ገዢ መጥፎ ነው ጥሩ ነው

የሚለው አይደለም፡፡ያሳሳበኝ ነገር ሁልግዜ ከዘመንዘመን እየተሸጋገረ እና እያደገ የመጣው የሰባአዊነት ነገር እየጠፋ የሰዎች ፍላጎት በእራስ ወዳድነት እየተመሰረተ መሄዱ ነው፤በኢ/ያውስጥ የተደረጉ ማንኛውም ለውጦች አስፈላጊነታቸው

ትክክል የነበረእና አንገብጋቢም የሕዝብ ጥያቄ የነበረ ቢሆንም ግን የተመለከትነው ሁልግዜ በቤተመንግስት ውስጥ የተወሰነ የሀይልእና የስልጣን ብሎም እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ የሆነ እንጂ ሕዝቡን ወደአስፈላጊ ዲሞክራሲና የመብት ጉዳይ ሊያመጣው አልቻለም፡፡ ይህም አሳሳቢ የሆነው ነገር ድህነት እየተስፋፋ እህል ባለበት አገር ሰው ጾሙን እያደረ የሚሄድበትን ጉዳይ ትክክል እንዳልሆነ እና አላግባብ የሚያካብቱም ሰዎች ትክክል እንዳልሆኑ የሚያገናዝብ የአብ ሮነት የስበአዊነት ስራግንዛቤ ካልተሰራ ህዝብ

ወደሚፈልገው ለውጥ ሊመጣ አይችልም፡፡ ግን

ሁልግዜ የተወሰኑሰዎች ያመኑበትየቤተመንግስት

ለውጥ ሊያመጡለት ይችላሉ፡፡ይህ የለመድነው ነው፤ካፒታሊዝም የሚደግፈው ቢኖርም ካፒታሊስት የሆኑ አገሮች እንደኢትዮጲያ ጾሙን የሚያድር ሰው የለበትም፡፡ ስለዚህ ካፒታሊዝም በኢትዮጲያ የህልም እሩጫ ነው፡፡ በካፒታሊስት የሆኑ አገሮች የሚኖረው ህዝብ፤ ሰውን ጾም አሳድረው ግለሰቦች የነሱን ከፍታ የሚገነቡበት ጭካኔውም የላቸውም፡፡ ለዚህ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ንቃተ ሕሊና ገንብተዋል፡፡ እኛ ጋር ግን

የሚቀድመው ከፖለቲካው ስራ በፊት የበላይነት፣

ስልጣን፣ ከሕዝብ መሃል አባል ሰብስቦ ያን ክፍል

ማክበር ማሰዳግ እና እንደልቡ እንዲሆን ማድረግ

የራሱን ገነት መገንባት ነው፡፡ ይህ የሞኝ ጉዞ ነው፡

ዘላቂነት የለውም፡ሕዝብ ዝምአለ ማለትአላወቀም

ማለት አይደለም፡፡ጦምአዳሪው ስራ አጡ እየበዛ

በሚሄድበት አገር ኢትዮጲያ፣ በልቶ የሚያድረው ክፍል ያኛውን ክፍል ልክ እንደዳቢሎስ በማየት ወይምንእንዳልተሳካለት በመቁጠር“ ጆሮ ዳባ ልበስ“ ብሎ ይባስም ብሎ የተቸገረ እንደለለ በማስመሰል ሁኔታውን መርሳት እጅግ የሚያሳስብ ሁኔታ ነው፡፡ሴቶች ከመቸውም በላይ በድካም በሚገኙበት ወቅት የጥቂት ሴት ሚኒስተሮች ቦታ መያዝ ወይም በስልጣን

መቀመጥ ሴቶች እተሸለ ደረጃ ላይ ደርሰዋል ማለት ያሳዝናል፡፡ እንዳውም ከመቸውም በላይ ማጣት ያሰማራቸው የስራ ዘርፍ ወይም መንገድ ሁሉ ለከፍተኛ ጥቃት ዳርጎአቸዋል፡፡ በላጩ ሕዝብ እየተቸገረ በድህነት እየተቆራመደ ጦሙን እያደረ የሚሄድበት አገር ላይ የሚደረጉ መረን የለቀቁ የማተርያል ውድድሮች ፤ካፒታሊዝም የሚለውን ሲስተም ወይም አመለካካት እየጠላ እንዲሄድ እና ህዝብንም ወደኮሚኒስት ሪቮሊሽን እንዲሄድ እንደሚያደርገው ምእራቡ አለም መጠርጠርም ያስፈልጋቸዋል፡፡ ኮሚኒዚም እያቆጠቆጠ በመሄድ ላይ ይገኛል እና፡፡ ሰው ወደእዛ የሚሄደው ይጠቅመኛል ብሎ ሳይሆን

ያለበት ሁኔታ መክፋት ይሆናል፡ይህን የኢትዮጲያን በድግግሞሽ የምናልፍባቸው የማንአለብኝነት ሁኔታ ሰባአዊነትን በእጅጉ እያጠፋው እየሄደ ነው፡ኢንቬስትሜንት የሚያስፈልግበትን ትምህርት የሚሰጥ አካል ከመፈጠሩ በፊት ወይምተገቢውን መተካካያ ሳይስተካከል ስፍራ ማስለቀቅ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡እሱም ፖለቲከኞችን

እንዳይታመኑ እና ደግሞም ኢንቬስተሮችን እንዲጠሉ የሚያደርግ ሀይል አለው ይህ በእጅጉ ቀውስ ፈጣሪ ነው፡፡ የአካባቢን ደግሞ ሁኔታ አንድ ኢንቬስተር ሳያጠና አይገባም፡፡ ከበሳል አገሮች የሚገቡ ኢንቬስተሮች የሚመለከቱት የሚጠብቃቸውን ጥበቃ ብዛት ሳይሆን ከማን እንደሚጠበቅ የሚያደርገውን ምንጭ ነው፡፡ ወደአፍሪካ የሚገቡ ኢንቬስተሮች ተቃዋሚ በሕዝብ መካከል የሚጫወተውን ሀይለኛ

ሚና ስለሚያቁት በቀላሉ ሰፍ ብለው ነዋያቸውን

ሊያፈሱ አይገቡም፡፡ ሕዝብ ካልተመቸው ጉሬላም

በለው ሰላማዊ ወደትግል መግባቱ አይቀርምእና

ስለዚህ በኢትዮጲያ ያየሁት ችግር ለሕዝብ

የሚገባውን መረጋጋት የሚሰጥፖለቲካአመራሮች

ሊፈጠሩ አለመቻላቸው ነው፡አልያም ባላወቅነው

ምክናያት ቤተመንግስቱን ከጨበጡ በሁዋላ

ጥበቃቸውም ስጦታቸውም ስራቸውም ቤተመንግስት አካባቢ ለሚገኙት ለመረጡዋቸው ሰዎች ብቻ ነው፡፡ቤተመንግስት ስል በሁሉም ክልል የምናየው የፖለቲከኞቻችን ቤተመንግስት አላቸው፡፡ በፓርቲ ስም የታቀፈው ክፍል እንደልቡ ሆኖ ሰዎችን በማሰላቸት አገሪቱን ልክ እነሱ ብቻ እንዲዝናኑበት፣ እንዲናገሩበት እንዲመሩበት የተሰጣቸው እስከሚመስል ድረስ ሌላውተሸማቆ የሚኖርበት ሲስተም የተገነባበት ነው፡፡

በዚህም የተነሳ ተበዳዩ ሕዝብ ለመኖርሲልየሀሰት

መስካሪ ከሳሽ እና ተበዳይም እርስ በእርሱ በማድረግ የበላይነትን እንዱ ተቀናጅቶ አስታራቂ በመምሰል ሰነልቦናን በመግደል ይገኛል፡፡ ተቃዋሚም በአንድነት ሊሰሩበት ያልቻሉት የንቃተ ህሊና አለመዳበር ጉዳይ ነው እላለሁ፡፡ይህ ትልቅ ቀውስ ያመጣብን ነገር ብዬ የምገምተው፤

ፖለቲከኞች ቤተመንግስቱን ሲጨብጡ ልክ

የእግዚአብሄርን ወንበር እንደተረከቡ ሆኖ

ስለሚሰማቸው የሚሞላቸው ትምክህት ወይም

የአሸናፊነት ስሜት ፖለቲካ ስራ እንዳለው ይዘነጉታል ፖለቲካን እንደስራ ሳይሆን እንደድል መቀናጀት ስለሚያዩት አንደዬ የጨበጡትን ስልጣን የሚያጡት አይመስላቸውም፡፡ ይህ ሁሉንም ፖለቲከኞች ባያካትትም፤ የበለጠው ግን በግልስግብግብነት እና በመሰረታዊ ድህነት የተነሳ ስሕተት ይፈ›ጸማል፡፡ ግን ድንገት ያንን ማጣቱ ሲሰማቸው ትኩረታቸውም አሁንም ለመስራት ሳይሆን በመከላከል ስልጣንን

መቀጠል ነው፡፡ የግል ጥቅም የአገሪቱን ጉዳይ

ያዘናጋል እና፡፡ ብልፅግና ዛሬ ላርመው ቢልም በብዙው መረን ለቆት የነበረውን ነገር ዛሬ ሊያስተካክለው አይችልም፡፡ችግርም የተፈጠረው እዚህ ላይ ነው፡ባህሪ ይለመዳል እና፤ ያስለመደው ባሕሪ በእራሱ አባል እንዲናቅ እንዳይከበር የማድረግ ጫና ፈጥሮአል፡፡ ህዝብን የሚያንገላቱ ሰዎች መፈጠር የበላዮቹን እንዲናቁ ያደርጋልና፡፡ ይህ ልቅነት የፈጠረው ጉዳይ አገሪቱን ወደሙስና እንድትገባ አድርጎአታል፡፡ይህም ብዙው ያመጣው ችግር ፖለቲካ ከስልጣን በላይ የሆነ ስራ እንዳለው በመዘንጋቱ ነው፡፡#ሌቦች ጋር ተሆኖ ሌባ-ሻይ መሆን አይቻልም፡፡ 

 ስርቆት የፈለገ ወደ ወያኔ ፤ ለውጥ የምንፈልግ #ክእውነት ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንጋዝ

 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ስለዚህ ውስጥን መመርመርና መፈተሽ የማናቸውም አዲስ የለውጥ ሥርዓት አሀዱ እርምጃ ነው፡፡ ሌብነት ከምዝበራና ከብዝበዛም ባሻገር፡- ሥራን  ማዳከምን፣ የቢሮክራሲውን ሞተር እንዳይሠራ አሻጥር ማድረግን፣ የተዛባ መረጃ መስጠትንና ህዝብን ማደናገርን፤ የነባር-አፍቃሪያንን ጎራ ምሉዕ- በኩለሄ (በሁሉም የተነካ) እንደነበረ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብን ቅራኔው የማይታረቅ መሆኑ ይፋ እስኪወጣ ድረስ በጥድፊያ ውስጥ ውስጡን መርዝ መርጨትን፣ አዲስ መዋቅር ብቅ ካለ፣ አናት አናቱን መምታትን… ይጨምራል፡፡ በሩሲያ አብዮት ዘመን የፓርላማ ሰዓት አይሠራም ነበር- የክሬምሊን ደወል ከቆመ አገር ምን ዋጋ አላት? እያሉ ክፉኛ መፃረራቸውን ያንፀባርቁ ነበር፡፡  ልባምና ንቁ የሆነ ትውልድ ክፉና ደግ ለይቶ ህዝቡን በደጉ ወገን ማንቃትና ማገዝ አለበት፡፡፡ በአንዳንድ  ወቅት ስሜታዊነት  የህዝብ ጠላት ነው ይላሉ፤ አበው ፈላስፎች፡፡ በተለይም ጩኸትና ሆታ ሲበዛ “ግርግር ለሌባ ይመቻል” የሚለው ተረት ይሠራል፡፡ በዚህ ላይ የውስጥ ቦርቧሪ ከተጨመረበት አደጋና ሥጋት አረበበ ማለት ነው፡፡ 

“እኔስ መች ኖርኩ፣ እኔስ መች ተወለድኩ ከጠላቶቼ ጋር አብሬ እየዶለትኩ” ያለው ፎካሪ ወዶ አይደለም! ልብ ይሏል፡፡ 

ደራሲ ዘውዴ ረታ፤ “የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት” በሚለው መጽሐፋቸው፤ 

“ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ በዚያን ዘመን የሥራ ትጋትና ብልህነት ከሚታይባቸው አንዱ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ሆነው ስላገኟቸው፤ የማንንም ሀሳብ ሳይ ጠይቁ፤ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና ፀሐፊነት አንሥተው ለጥቂት፣ ወራት ልዩ ፀሐፊያቸው በማድረግ የሥራ ጠባያቸውን ካላመዷቸው በኋላ፣ በ1927 ዓ.ም የጽሕፈት ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር ብለው ሾሟቸው፡፡”.. ለተሿሚው ኃ/ሥላሴ ባደረጉት ንግግር፡- 

“ያሳደግኩትን አበባ እኔው ቆርጬ መጣሉ

ከሁሉ የበለጠ የሚያሳዝነኝ ስለሆነ፤

ይህ ሐዘን እንዳይደርስብኝ ተጠንቀቅ” ብለው ነበር፡፡

ከጃንሆይ ተግባርና ንግግር መማር እጅግ ትልቅ አስተውሎትን ያስጨብጣልና ልብ እንበለው! የምንሾማቸው ሰዎች የሥራ ትጋትና “ጨው ሆይ! ብትጣፍጥ ጣፍጥ፤ አለበለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሃል” የሚለውን እናስገንዝባቸው፡፡ 

አሮጌን ሥርዓት ማፍረስ ቀላል ባይሆንም አዲስ ሥርዓት ማነፅ እጅግ ውስብስብ ነው፡፡ “ከአብሮ አደግህ አትሰደድ” የሚል አንደምታም አያጣም! ስለሆነም የሌት ተቀን ልፋትና መስዋዕትነት ጭምር ግድ ይሆናል! ከምንጠራ እስከ አጥር-አጠራ የመቶ ጀምበር ስራ ብቻ አይደል፡፡ “ትርፉን ነግሮ መከራውን ሳይነግረኝ” እንዳንል ውጣ-ወረዱን ከወዲሁ ማወቅ ይበጃል! ‹ሠንሠለቱን ለመበጠስ ከላላው ቀለበት ጀምር› የሚለውን ጥበባዊ መርህ አንዘንጋ፡፡ ደረጃ በደረጃ የምንሠራው ሥራ ደርዝና ብሰለት ይኖረዋል፡፡ 

እንደ ሩሲያው መሪ እንደ ጎርባቾቭ፤ የግልፅነት ክስተት (ግላስኖስት) ሁሉን በር በረጋግዶ አንድ መወርወሪያ መዝጊያ እንኳ ሳያበጁ  መቅረት ተገቢ አይሆንም፡፡ “ከተናገርክ ፍርጥ፣  ከመታህ ድርግም” ይላሉ የታክቲክ ጠበብት፡፡ አለበለዚያ እሷ ታስራ፣ በሩ ተከፍቶ ተትቶ፣ ሌባ ገብቶ ሲዘርፍ እንዳየችው ውሻ፤ “በራቸውን ሳይዘጉ ሌባ ሌባ ይላሉ” እንዳንል እንሰጋለን፡፡ ስለዚህም፤ 

“ላገሩ አልሆን ብሎ ሁኔታው ሲጠጥር 

ጠጣሩ እንዲላላ የላላውን ወጥር!” እንላለን-ዛሬም

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)