ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ)
ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ) ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ) ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በ ደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በእንጾር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በጥቅምት 7 ቀን 1902ዓ.ም. ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት በቤተሰባቸው አጠገብና ባባታቸው አገር ደብረ- ኤልያስ ሄደው የግእዝ ትምሕርት ቤት ቅኔ ተቀኝተዋል። የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ-ኤልያስ፣ በደብረ-ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በኋላ ወደ በ1918 ዓ.ም አዲስ አበባ በመሄድ በስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በኋላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ለትንሽ ጊዜ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ። የኢጣልያ ወረራ ሲከሰት ከልዑል ራስ ዕምሩ ኃይለሥላሴ ጦር ጋር በምዕራብ ኢትዮጵያ በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው በመያዛቸው ጣሊያን ከልዑል ራስ ዕምሩ ጋር በግዞት ለሰባት ዓመታት በፖንዞ ደሴት ና በሊፓሪ ደሴት ታስረው ቆይተዋል። ከዚያም የተባባሪ ኃያላት ወታደሮች በ1935 ዓ.ም. ሲያስመልጧቸው በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና በኦክስፎርድ ከገፉ በኋላ በተለያዩ የ መንግስት ተቋማት በተለይም በ ትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል። 1936 - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኛ 1937 - 1938 - የኢትዮጵያ ቆንሱል በኢየሩሳሌም 1938 - በ International Telecommunications Conference አትላንቲክ ከተማ ፣ ኒው ጄርዚ ወኪል 1938- 1942 - በተባበሩት መንግሥታት ቢሮ ኒውዮርክ ሠራተኛ 1942- 1948 - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይረክተርና ምክትል ...
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ