ህዋህት ነቀርሳ
1550 ጀምሮ እስከ ትላንቱ የጥቅምት
ወር መጨረሻ 2013 ዓ.ም ጡት
ነካሹን እና ‹‹የታሪክ አተላውን›› /
ይህችን ቃል ሊቀመንበር መንግሥቱ
ኃይለማርያም ነበሩ የሚጠቀሟት/ ቡድን
ለማስወገድ ሲባል ርምጃ ለመውሰድ መንግሥታዊ
ውሳኔ እስከተላለፈበት ቀን ድረስ በሰሜን፣ በሰሜን
ምሥራቅና በተለይም በሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ
መሬት ቁጥር ሥፍር የሌላቸው ውጊያዎች
ተካሂደዋል፡፡
ከኢጣሊያ ወራሪ ሠራዊትና ለዚያ ሠራዊት
መንገድ ከሚመሩና በምንዳ ካደሩ ከሃዲዎች
ጋር፡፡ ከዓድዋ ዘመቻ በፊትና በዘመቻው ጊዜ፤
በማይጨው ጦርነት ዋዜማ፣ በአምስቱ ዓመታት
የዓርበኝነት ወቅቶችና ከዚያም በኋላ ዛሬ
‹‹ምዕራባዊ ትግራይ ዞን›› በሚባለው ሥፍራና
አዋሳኝ የጎንደር ሁለት አውራጃዎች ሥር በሚገኙ
የተለያዩ ወረዳዎች፤ ብሎም በራያ-አዘቦና በሰሜን
ወሎ ራያ ቆቦ፣ በዋግ ላስታ አውራጃዎች ሥር
በሚገኙ በርካታ ሥፍራዎች፤ የእናት ኢትዮጵያ
ልጆች ርስ በርሳቸው፣ ከቅጥረኛ ወንበዴዎችና
ከውጭ ወራሪዎች ጋር አያሌ ፍልሚያዎችን
አካሂደዋል፡፡
ወደ ፊት ራቅ ብለን ከእነ ራስ አሉላ አባነጋ፣
ከአፄ ዮሐንስ ተጋድሎ አሃዱ ብለን… ቀረብ
ወዳለው በመመለስ፤ የእነ ራስ ዕምሩ ኃይለሥላሴን
ዘመቻዎች፣ የእነ ራስ አሞራው ውብነህንና
በእነሱ ሥር የነበሩ ዓርበኞችን ተጋድሎዎች፣
የእነ ራስ ኃይሉ ከበደን ታላቅ ኢትዮጵያዊ
ዓርበኝነትና መስዋዕትነት፣ የእነ ቢትወደድ
አዳነንና የወልቃይት ጠገዴ ወረዳ ኢትዮጵያውያን
ጀግኖችን ውጣ-ውረድና ወደ ትውልዳቸው
በመንፈስ የተዛመ አይበገሬ የጀግንነት ተግባር
ስናስብ፤ የትም ሆነን በዓይናችን የሚመላለሰው
ከፍ ሲል የተጠቀሱት የደም መሬቶች በተለይም
የሰሜንና የሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ አውራጃ፣
ወረዳዎችና ቀበሌዎች ናቸው፡፡
እጅግ ከረዥሙ በጣም ጥቂት በአጭሩ፤ ከፍ
ሲል በተገለጹት የሃገራችን ሰሜናዊ፣ ሰሜናዊ
ምሥራቅና ምዕራብ አካባቢዎች፤ በኢትዮጵያውያን
መሳፍንቶችና መኳንንቶች መካከል ለሥልጣን
የበላይነትና ለርስት ጉልት ማስፋፊያ ሲባል
አያሌዎች ደማቸውን አፍሰዋል፡፡ በአንደኛውና
በሌላኛው ‹‹ልንገሥ፣ የበላይ ልሁን›› ባይ
መስፍንና መኳንንት ደጋፊነት ስም ወደ ሃገራችን
ጎራ ያሉ ባዕዳንም፤ በኢትዮጵያውያኑ መካከል
ለነበረው ግጭትና ውጊያ መባባስ የበኩላቸውን
ሚና ተጫውተዋል፡፡ የየአውራጃውና የየጎጡ
ጦር አምላኪ መሳፍንቶች ርስ በርሳቸው ሠይፍ
ሲማዘዙና ጡንቻ ሲጠማዘዙ ቆይተው በተዳከሙ
ጊዜም፤ በዘመኑ ኃያል የነበሩት ቱርኮች ጠባቂ
ያልነበረውን የሃገራችንን ባሕረ-ገብ መሬት ወረው
ይዘዋል፡፡
ከቱርኮችም በኋላ ተገዳዳሪዎቻቸው የነበሩት
ፖርቹጋሎች ‹‹ኃይማኖታዊ አጋርነትን ሽፋን
በማድረግ›› በኢትዮጵያ የእጅ አዙርም ይሁን
የቀጥተኛ ቅኝ ገዥነቷን መረብ ለመጣል ሙከራ
አድርጋለች፡፡ የቱርክና የፖርቹጋል ሃገራችንን
በየምክንያቱ ይዘው ለመቆየት አድርገውት
የነበረው ሙከራ ሳይሳካ ሲቀር፤ የእነሱን እግር
ተከትላ ሠራዊት በኢትዮጵያ ላይ ያዘመተችው
ግብፅ ነበረች፡፡ የእሷም ቀዳማይ ቀቢፀ-ተስፋ
ወይም ሊሳካ ያልቻለ ዓላማ፤ አንድም በእነ አፄ
ቴዎድሮስና አፄ ዮሐንስ ባደረጉት ወሰን-የለሽ
የኢትዮጵያን ጠላቶች የመመከት ጥረት የተኮላሸ
ሲሆን በሌላ በኩል እስከ ዛሬ ድረስ አልሰክን ያለው
ፍላጎቷ ዓይነተኛ መለያ የሆነው ‹‹የዓባይን ወንዝ
እስከ ምንጩ በቁጥጥሯ ሥራ የማዋል›› ነበር፡፡
ከግብፅ ኢትዮጵያን የመውረር ድርጊት
በስተኋላ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ
የቀጠለው፤ የአውሮፓ ኃያላን ሃገሮች ኢትዮጵያን
የመቀራመት ሤራና በተግባርም ቅኝ ለመግዛት
ብሎም የራሳቸው ርስት የማድረግ ሙከራ ነው፡
፡ በዚህ በኩል ዓይነተኛዎቹ የሃገራችን አጥቂ
ሃገሮች እንግሊዝና ኢጣሊያ መሆናቸውንም ታሪክ
ይመሰክራል፡፡ በተለይ ታላቂቱ ብሪታኒያ በራሷ
አቅም ሊሆንላት ያልቻለውንና በግብፅ ተይዞ
የቆየውን የኢትዮጵያን መሬት፤ በግብፅና በሱዳን
በነበረው የቅኝ ገዥ አስተዳደሯ ሥር ለመጠቅለል
ያደረገችው ሙከራ ሳይሳካለት በመቅረቱ፤ ለሸሪኳ
ኢጣሊያ በ1885 ዓ.ም አሳልፋ መስጠቷ ወዘተ
/ የፀረ-ሕዝቦች እንቅስቃ በሰሜን ሰሜን ምዕራብ
ኢትዮጵያ፤መስከረም 1977 ዓ.ም ቅጽ ፩ /የሃገርና
ሕዘብ ደኅንነት ጥበቃ ሚኒስቴር ተቋም ጥናታዊ
ሰነድ./ ታሪክ ምስክርነቱን ሰጥቶ ያለፈበት ጉዳይ
ብቻ ሳይሆን ያኔ በሰሜን ኢትዮጵያ ምድር
የተቀበረው መርዝ ወይም ልዩነትን ፈጣሪ
የፖለቲካ ፈንጂ፤በቅብብሎሽ ለዛሬዎቹ የእናት
ጡት ነካሾች የደረሰ መሆኑን በግልጽ አመልካች
ነው፡፡
ሕወሓት የውንብድና ተግባሩን -ሀ- ብሎ
በጀመረ ሰሞን በብሔር ትግል ዙሪያ ጠመንጃ
እስከማንሳት ድረስ ለመሄድ ‹‹ተገደድኩ››
ያለበትን ምክንያት በርካታ የመንደርተኛ፣
የአኩራፊና ከአስተዳደጋቸው ጉድለት ያለባቸው
ጎረምሶች በየሰፈሩ የሚያመነጩትን ጮርቃ ቃላት
እየደረደረ…. ‹‹ፖለቲካው ትንተና›› ያለውን
የጥላቻ ዘር መዝራቱን ሥራዬ ብሎ ይዞታል፡
፡ ለምሣሌ ያህል ከወያኔዎች ቀደምት የበረሃ
መራር፣ ጥንስሱ የተንኮልና የተንኮል ብቅልና
ጌሾ ብቻ የነበረ አስተምሮ አንዱ፡- የትግራይ
ሰው ‹‹…በዐማራ ገዥዎች ዘንድ እንደጠላትና
እንደ ሁለተኛ ዜጋ ስለሚታይ ይጠረጠራል፡፡
አይታመንም፡፡ በዚህም የትግራይ ሕዝብ ጠባብ
የሆነ የዐማራ ጥላቻ አለው፡፡ ስለዚህ ጭቁኑ
የትግራይ ሕዝብና ጭቁኑ የዐማራ ሕዝብ በአንድ
ላይ ተሰልፈው በአሁኑ ወቅት መደባዊ ትግል
ሊያካሂዱ አይችሉም፡፡ ምክንያቱም በመካከላቸው
ጠባብነት ሰፍኖ ስለሚገኝ ነው፡፡ በመሆኑም
በኢትዮጵያ ውስጥ የመደብ ትግል ከማደረግ
በፊት ለብሔረሰቦች ዕኩልነት መታገል አማራጭ
የሌለው የትግል ስልት ነው›› የሚለው ተጠቃሽ
ነው፡፡
ከማለዳው ‹‹ለብሔረሰቦች መብትና ዕኩልነት
እታገላለሁ›› የሚል ዓላማ እንደሚያራምድ
ፍንጭ ሰጥቶ የነበረው ሕወሓት፤ በ1968
ዓ.ም ደግሞ ቀዳሚ የስብከት አጀንዳውን
በመለወጥ ‹‹ወታደራዊው መንግሥት በሥልጣን
እስካለና የኢትዮጵያን ሕዝብ አስተባብሮ በአንድ
‹ዴሞክራቲክ የኅብረት ግንባር› የሚያታግል መሪ
የፖለቲካ ድርጅት እስከሌለ ድረስ ‹ትግራይን
ከኢትዮጵያ በመገንጠል ነፃ መንግሥት
ለመመሥረት እታገላለሁ›…›› የሚለውን
የገንጣይነት ዓላማውን እንደሚያራምድ ግልጽ
አድርጎ ነበር፡፡
ዛሬ ወደ በረሃ በወረደበት ጊዜና በትጥቅ
ትግሉ ወቅትም በይፋ ሲስተዋልበት በነበረው
ዕብሪቱ እንዲሁም ራሱን ‹‹የኢትዮጵያ ፌደራላዊ
ዴሞክራሲያዊ መንግሥት›› አስኳልና ወሳኝ
ኃይል አድርጎ በመላው ሃገራችን ያሻውን
በታኝ፣ ከፋፋይ፣ አጥፊና አውዳሚ ድርጊቶችን
በግልጽ ዝርፊያና ቅጥ የለሽ በሆነው የአፈና፣
የአረመኔነትና የወደር-የለሽ የጭካኔ ተግባራት
አጅቦ ለመቀጠል ባለው የማይሰክን ፍላጎት
መሠረት የቀደመ የዕብሪትና ኢትዮጵያን የዕልቂት
ዐውድማ የማድረግ ዐመሉን ይዞ ‹‹ጦር አውርድ››
በማለት የመቀበሪያ ጉርጓዱን በጥልቁ ቆፍሮ
ተነስቷል፡፡
ሕውሓት ‹‹ትግራይ ከ700 ዓመተ ዓለም
ጀምሮ እስከ 10ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ‹ብሔረ
አግዐዚ፣ ብሔረ ሃበሽ፣ አክሱማዊ መንግሥት›
በሚሉ የተለያዩ ስሞች የተጠራች ሃገር ነበረች፤
ከ14ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በአፍሪቃ ቀንድ
የነበሩ መሳፍንት መንግሥታት አንዱ የሌላውን
የመውረር መልክ ቢኖራቸውም የየራሳቸው
ታሪካዊ አመጣጥና ዕድገት ያላቸው የተለያዩ
መንግሥታትና ሕዝቦች ነበሩ፤ በ14ኛው ክ/ዘ
የአክሱም መንግሥት ቢወድቅም እስከዚያው ድረስ
በዓለም ታሪክ ጎልቶ የሚታወቀው መንግሥትና
ሕዝብ የአክሱም ብቻ ነበር፤ ኢትዮጵያ
እንደማንኛውም የሦስተኛ ዓለም ሃገሮች የአሁኑን
ዳር ድንበሯንና መልካ-ምድራዊ ቅርጿን ይዛ
የቆመችው ከ1881 እስከ 1890 ዓ.ም በአፄ
ምኒልክ ዘመነ-መንግሥት ነው፤ የትግራይ ሕዘብ
ባለው ታሪካዊ አመጣጥ ምክንያት ‹ዐሜን ብሎ
ተረግጦ የማይገዛ ሕዝብ መሆኑን አፄ ምኒልክ
ስለተገነዘቡ› የትግራይን መሳፍንት በመከፋፈል
ሕዝቡን እርስ በርሱ ለማጨፋጨፍ ወስነዋል፡፡
በውሳኔያቸውም መሠረት ራስ አሉላን ከራስ ሐጎስ
ጋር አዲ-ጓደድ ላይ፣ ደጃዝማች ገብረሥላሴን ከራስ
ስዩም ጋር ጊዳሩ ላይ፣ ራስ ስብሃትን ከደጃዝማች
ገበረሥላሴ ጋር ገኸረ ላይ እንዲዋጉ አድርገዋል
ወዘተ.›› / የፀረ-ሕዝቦች እንቅስቃ በሰሜን ሰሜን
ምዕራብ ኢትዮጵያ፤መስከረም 1977 ዓ.ም ቅጽ
፩ /የሃገርና ሕዘብ ደኅንነት ጥበቃ ሚኒስቴር
ተቋም ጥናታዊ ሰነድ./ የሚል የማወናበጃ ታሪክ
ፈጥረውና መርዙን በማር ለውሰው ሲያወናብዱት
ለነበረው የ1960ዎቹ የትግራይ ክፍለ ሃገር ወጣት
ትውልድ ሲግቱት ኖረዋል፡፡
ከ1983 ዓ.ም ግንቦት ወር ማግስት ጀምሮም
ይህንና ይህንኑ የመሰለውንና የኢትዮጵያን ሕዝብ
በአንድነት የማያቆም፣ በጥርጣሬና በጠላትነት
ዓይን እንዲተያይ የሚያስገድድ፤ ብሎም
ኢትዮጵያን የሚበትን መርዝ በ‹ብሔር ብሔረሰቦች
ሕዝቦች ፈጣሪ ነን› ባይነታቸው ዕብሪትና
ለኢትዮጵያ ጭቁን ዜጎችና ብሔሮች ነፃነትና
መብት መስዋዕትነት የከፈልን፣ የትግሉንም ችቦ
ለሌሎች የብሔር መብት፣ ዕኩልነትና ነፃነት
አቀንቃኞች የሰጠን ብቸኛዎቹ ተጋዳላዮች እኛ
ነን›› በሚለው ትምክህታቸው፤ በመላው ሃገራችን
የጥላቻን ዘር ዘርተዋል፡፡
ከእነሱ ወደ ትግል መውጣት በፊት ጀምሮም
ይሁን አነሱ የገንጣይ አስገንጣይነታቸውን
ትግል እስካጧጧፉበት፣ ‹‹መንግሥት ሆነናል››
ብለውም ኢትዮጵያን እንዳሻቸው ሲያተራምሷት
እስከ ነበሩበትና በሕዝባዊ ግፊት የዝንተ-ዓለም
አሻንጉሊታቸው ሆኖ ይቀጥል ዘንድ ይመኙት
በነበረው ‹‹ኢሕአዴግ›› ውስጥ ‹‹ትራንስፎርሜሽ››
የሚባለው የለወጥ ማዕበል ተነስቶ ወደ መቀሌ
እንዲሰባሱበ እስከተገደዱበት ጊዜ ድረስ፤ በሃገራችን
‹‹እነሱን የመሰለ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን
የሚያስብና የሚጨነቅ መንግሥትም ይሁን
የፖለቲካ ፓርቲ እንዳልተፈጠረ አድርገው ሲቆጥሩ
የቆዩት እነሆ ዛሬ በጫሩት እሳት እየነደዱ ነው፡፡
ያም ሆነ ይህ ከትላንት ወዲያ፣ ትላንትና
ዛሬም ጭምር፤ በሰሜን ጎንደር መሬት፡፡
በሰሜናዊ ምሥራቅ ሰሜናዊ ምዕራብ አቀበትና
ቁልቁለቶች፣ ኮረብታዎችና ጉድባዎች፣ የተከዜ፣
የራያ ጨረጨር፣ መሆኒ፣ ማይጨው፣…
ሸለቆዎችና በረሃዎች፣ የአድርቃይ ማይፀምሪ
ጋራና ሸንተረሮች፡፡ ከደባርቅና ከወገራ አውራጃ
ጀምሮ እስከ ሁመራና የሱዳኗ ዐመዳይት የወሰን
ከተማ ድረስ በተንጣለለው መሬት፤ የኢትዮጵያ
ልጆች ደም የፈሰሰው አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት ጊዜ
ብቻ አይደለም፡፡ በስሜን አውራጃ የጠለምት፣
የበየዳና፣ የጃን አሞራ ወረዳዎች፤ በወገራ አውራጃ
የወልቃይትና የጠገዴ ወረዳዎች፤ በትግራይም
እነ ፈረስማይ፣ ሀበስት፣ ዓዲ-ገብሩ፣ ዓዲ-ዳዕሮ፣
ዕንዳባህጸማ ወዘተ. ያሉት ወረዳዎችና ሌሎች
ተጓዳኝ ሥፍራዎች የወያኔው ልዩ ይዞታዎች
ወይም ቀዳማይ ‹‹ነፃ›› የሚባሉ መሬቶች የሚባሉ
ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ግፍ የተዋለባቸው፣ የሰው
ልጅ ዕልቂትን ያስከተሉ መራር ፍልሚያዎች
የተካሄዱባቸውም ነበሩ፡፡ ሁመራ፣ ቃፍታ፣
ጽንብላ፣ ሽሬ፣ዓዲ-ዳዕሮ፣ ባድሜ፣ ሽራሮ፣
ማይ ተመን፣ ማይ ህበይ በረሃ፣ ማይ ተኒ፣ ማይ
ኩህሊን፣ ግይጽ በረሃ፣ ሰፈዋ፣ ገዳሪፍ፣ ዓዲ-
ጎሹ፣ ዓዲ-ረመጽ፣ ሰየምት አድያቦ፣ ደደቢት፣
ይርጋ፤በጥቅሉ በአብዛኛው የወልቃይትና የሽሬ
አውራጃ…. የተዓምራትና የሰው ልጅ ከባባድና
የሚዘገንኑ የስቃይ ዓይነቶችን እየተቀበለ
ያሸለበባቸው የግፍ መሬቶችና ሸለቆዎች…
የትየለሌ ናቸው፡፡
በተለይ ‹‹በትግራይ ክፍለ ሃገር በሽሬ አውራጃ
በሰየምት አድያቦ ወረዳዎች ውስጥ የሰው አፅም
ያልተከሰከበት በረሃና ቋጥኝ የለም፡፡ ከሠላሳ
ሁለት ጊዜ የወያኔና የኢድኅ ጦርነት ዕልቂት
ሌላ፤ ሃገሩ በወያኔ ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ
‹የኢዲኅ ደጋፊ ነበርክ፣ ነበርሽ› ተብለው በወያኔ
አፈሙዝ እየተረሸኑ በየፈፋው… የተደፉት፣
አፈር ተነፍጓቸው ፀረ-ትግራይ ‹ኾራ ኹር
አምሐሩ› (የአማራ ቡችላ) እየተባሉ ለአሞራ
ቀለብ የሆኑትን፤ የወለደና የተዋለደ፣ ተሸማቆ ያየ
ቤት ጎረቤት ይቁጠረው›› እያሉ እንደ ግደይ ባሕሪ
ሹም ያሉ ኢትዮጵያውያን ‹‹አሞራ›› በተሰኘውና
በ1985 ዓ.ም ለንባብ በበቃው መፅሐፋቸው ገጽ
196. ላይም ይሁን በሌሎች ገጾች የሚያስነብቡን
ብዙ ያልተነገረ ወይም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ
በአግባቡ ያልደረሰ ሐቅም አለ፡፡
የራሱን መቃብር በራሱ የክፋት አንካሴ
መልሶ በጥልቁ መቆፈር የጀመረው የዛሩው
ወያኔ፤ ዓላማው ምንም የነበረ ይሁን ምን፤
‹‹የትግራይ መሬት የሚሸከመው አንድ ለትግራይ
ሕዝብ ነፃነት የሚታገል ድርጅት ብቻ ነው››
የሚለውን አቋም ከመነሻው በመያዝ፤ በመሪዎቹ
አማካይት የ‹‹ግንባር ገድሊ ትግራይ›› ወይም
የግገት ድርጅት መሪ የሆኑትን ሰዎች፤ በ1968
ዓ.ም በአጋሜ አውራጃ ‹‹ማርዋ›› በተባለ ሥፍራ
አስቀድመው ያደረጉትን የ‹‹አንድ እንሁን›› ቃል
ምክንያት በማድረግ አታለውና ቃላቸውን አጥፈው
በተኙበት ከማረኩና ‹‹ወረአትሊ›› ወደተባለው ቦታ
ወስደው ዮሐንስን፣ ታደሠንና ሌሎችን ከገደሉ
በኋላ ድርጅቱን አፍርሰዋል፡፡ ያፈረሱትንም
ድርጅት አባሎች በትነዋል፡፡ በዕኩይ ስብከታቸው
አጥምቀውም የእነሱ ጀሌዎች አድርገዋል፡፡ ያን
የመሰለ ድርጊት እነ ስብሃት ነጋ ዓባይ ፀሐዬ…
የፈፀሙ ስለመሆናቸውም፤ በወቅቱ ከሕወሓት
እስር ቤት ማምለጥ የቻለው ተፈራ ካሣ እና
በጊዜው በአፈናው ቦታ ባለመኖሩ ምክንያት
ወጥመዳቸው ውስጥ ያልገባው ኃይለኪሮስ አሰግድ
/ የፀረ-ሕዝቦች እንቅስቃ በሰሜን ሰሜን ምዕራብ
ኢትዮጵያ፤መስከረም 1977 ዓ.ም ቅጽ ፩ /የሃገርና
ሕዘብ ደኅንነት ጥበቃ ሚኒስቴር ተቋም ጥናታዊ
ሰነድ./ የመሰከሩት ነው፡፡
የግገት መሪዎች በሕወሓት መሪዎች
ክህደትና ፍፁም ጭካኔ የተመላበት ሠይፍ
ከተቀሉ፣ ደብዛቸው እንዲጠፋ፣ ድርጅታቸው
እንዲፈርስና አባሎቻቸውም እንዲበተኑ ከተደረገ
በኋላ በ1969 ዓ.ም ሕወሓቶች የዘመቱት
በትግራይ እና በዐማራ ልጆች ኅብረት ተቋቁመው
በነበሩት እና አፍላውን ወታደራዊ መንግሥት
ተዋግተው ዘውዳዊ ሥርዓቱን መልሰው ለማንገስ
ፍላጎት በነበራቸው የኢ.ዲ.ሕ.ን ታጣቂዎች ላይ
ነበር፡፡ ከእነሱም ጋር ብዙ ዕልቂት የታየበትን
አሰቃቂ ውጊያ ካካሄዱ በኋላ ከትግራይ መሬት
ወደ ጎንደር ወደዛሬው ወልቃይት ፀገዴ አውራጃ
እንዲያፈገፍጉ አስገድደዋቸዋል፡፡
ወያኔዎች በኢዲዩ ላይ ካካሄዱት የድምሰሳ
ዘመቻ በኋላ፤ የትግራይ ክፍለ ሃገር ተወላጆችን
ጨምሮ ከመላው ኢትዮጵያ ተሰባስበው፤
የወታደራዊውን አብዮታዊ መንግሥት መርሆዎች
ገና በማለዳው በመቀናቀን ስም የትጥቅ ትግል
ለማካሄድ የተሰባሰቡትን የኢሕአፓን ሠራዊት
አባላት፤ ከየካቲት ወር እሰከ ሚያዚያ ወር 1970
ድረስ በአጋሜ አውራጃ ውስጥ በመውጋት
ከትግራይ መሬት እንዲወጡ አድርገዋል፡፡ ከፍ
ሲል በተገለጸው መፅሐፋቸው ከገጽ 200-201
ግደይ ባሕሪ ሹም እንደሚሉን ሕወሓቶች፡- ‹‹ላምና
ፍየሉን እንጠብቅልሃለን ብለው ያለ ፍላጎቱ ለስደት
የዳረጉትነረ ሕዝብ (ሕፃን ሽማግሌን ጨምሮ)
‹ወዲ ኸውሊ› በተባለው በረሃ በበሽታ፣ በረሃብና
በቁርጥማት፣ በተቅማጥ እየተነዳ፤ እንደ ቅጠል
በጅምላ ሲረግፍ፤ የዓለም ጋዜጠኞችን ጋብዘው
ለበጎ አድራጊ ድርጅቶች ‹ለሕዝባችን የሰጣችሁን
የእህል ዕርዳታ አልበቃ ብሎ ይኸው በረሃብ
እየረገፈ ነውና መጥታችሁ ማየት ትችላላችሁ›
እያሉ መለመኛ አድርገውታል፡፡ በዚህ መልክ
ያገኙትን እህልም ሽታውን ብቻ ለተለመነበት
ወገን አቅርበው ቀሪውን በቶን ለሱዳን ሀብታም
ነጋዴዎች በመሸጥ ተዝናንተውበታል…››
ብለዋል፡፡
ሰኔ 5 ቀን 1968 ዓ.ም የሽሬን ግምጃ
ቤት ከመዝረፍና ከዚያም በእነ ፍቅረይ አርዓያ
አማካይነት ‹‹በፈረስ ካብ›› አካባቢ ገሠሠ አየለን
የገደሉ፤ በየካቲት 14/1968 በሽራሮ ከተማ የገሠሠ
ሞት እንዳይሰማ ወይም ተድበስብሶ እንዲቀር
‹‹ምስጢር ሊገልጡ ይችላሉ›› ተብለው የተገመቱ
የሕወሓትን ደጋፊዎች የጨፈጨፉ… /‹‹አሞራ››
በግደይ ባሕሪሹም በ1985 ዓ.ም የተፃፈ መፅሐፍ
ከገጽ 165-166 መመልከት ይቻላል/ ሰው
የፊጥኝ አስረው ገድለው የቀበሩ፣ እናትን በልጇ
አስከሬን ላይ እንድትቀመጥ ያስገደዱ፣ ‹‹ወንድ
ነን›› ብለው ወንድ ልጅን አስገድደው የደፈሩና
ያስደፈሩ፣ በበረሃ ሳሉ በገዛ ወንድሞቻቸው ላይ
የመጨረሻውን የጭካኔ ተግባር ሁሉ ፈፅመውና
ተለማምደው ሲያበቁ ወደ መንግሥትነት ደረጃ
የመጡ መሆናቸው የማይታወቅ ይመስል፤ ስለ
ሰብዓዊነት፣ ስለ ፍትሕ፣ ስለ ‹‹ብሔር ብሔረሰቦች
ሕዝቦች›› ፈጣሪነታቸው፣ ስለ መብትና ነፃነት
ተጋዳላይነታቸው፣ ከእነሱ ውጭ የአብዮታዊ
ዴሞክራሲም ይሁን የነጭ ካፒታሊዝም…
ርዕዮት አራማጅ እንደሌለ በዓለም አደባባይ
ያለ አንዳች ሃፍረት ስለራሳቸው የመሰከሩ፤
አጨብጫቢዎቻቸውን እና በእነሱ ብልት የሚፎክሩ
ሎሌዎቻቸውን እንደ ሰም አቅልጠው፣ እንደ ብረት
ቀጥቅጠው ከሠሯቸው በኋላ ‹‹መለስ ሌጋሲያችን
ነው…›› እያሉ በየደረሱበት እንዲለፍፉላቸው
ያደረጉ፣ የፍፁም አድርባይነትን ርጉም ስብዕና
ኩሩ ሆኖ በኖረው ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ ውስጥ
ያለማመዱ ወያኔዎች መሆናቸውን፤ ይኸው
ዛሬ ታሪክ በአደባባይ በራሳቸው ዕኩይ ግብር
መስክሮባቸዋል፡፡
ስለዛሬዎቹ ጡት-ነካሾች ይነገር ከተባለ
የሚጠቀሰው እስካሁን የተባለው ብቻ አይደለም፡
፡ ከተባለውና ከተፃፈውም በላይ ቃላት ሊገልፁት
የማይቻላቸው አያሌ የግፍ ታሪኮችም አሏቸው፡
፡ ለምሳሌ ያህል በወያኔዎች የውንብድና መርህ
መሠረት እንደ ሰየምት አድያቦ ባሉ በረሃዎች
በራሳቸው ታጣቂዎች በሚገደሉ ተጋዮች ምክንያት
አሞራ ጦም አድሮ አያውቅም፡፡ በደደቢት በትግራይ
ሕዝብ ላይ የናዚ ሥርዓት የሚፈፀምበት ‹‹ባዶ
ሹድሽተ›› ወይም ዜሮ ስድስት ተብሎ የሚጠራ
እሥር ቤትመረ ነበር፡፡ በዚያን መሰሉ እስር ቤት፣
የቁም ገሀነም የሰው ልጅ በተለይም ሕወሓትን
ዕምቢኝ ያሉ የትግራይ ክፍለሃገር ተወላጅ
ኢትዮጵያውያን እንዴት ያለውን የስቃይ ዓይነት
እየተጋፈጡ ሕይወታቸው እንዳለፈ በጥቂቱም
ቢሆን ለመገንዘብ፤ የግደይ ባሕሪሹምን ‹‹አሞራ››
የተሰኘ መፅሐፍ ከገጽ 207 እስከ 209 በጥሞና
መቃኘት መልካም ነው፡፡ በዚሁ ተጠቃሽ ሊሆን
የሚችል መፅሐፍ በገጽ 198 እና 199 ላይ
የሠፈረውን በአስተውሎት በማንበብም ‹‹ንትግራይ
ዓደይ በል›› ወይም ‹‹ለሃገሬ ትግራይ በል››
እየተባለ የትግራይ ክፍለ ሃገር ሰው ‹‹ኢትዮጵያዊ
ነኝ›› በማለቱ ምክንያት እንዴት ያለው የዘረኝነት
ጅራፍ ሲወርድበት እንደነበርም ማወቅ ይቻላል፡፡
ስለ ወያኔ አመጣጥ፣ የግፍና የግፈኝነት፣
የዘረኝነትና የበታኝነት ባሕሪያት ታሪክ ብዙ
ይመሰክራል፡፡ አብዛኞቹ የሰሜን፣ የሰሜን
ምሥራቅና ምዕራብ የኢትዮጵያ ምድሮችም
አንደበት ቢኖራቸው ከተነገረውና ከተፃፈውም
በላይ ስለ ሕወሓት አምሳለ የጭካኔ አውራነት
ለኢትዮጵያዊው ትውልድ እጅግ ብዙ በነገሩት
ነበር፡፡ ይሁንና የቅርቡ ሃገራዊ ዘመቻና ዳግማዊው
መስዋዕትነት፤ በትግራይ ሽሬ፣ አክሱም፣ ዓድዋ፣
አጋሜ፣ ክልተ-አውላሎ፣ እንደርታ፣ ራያና አዘቦ፣
ተምቤን አውራጃዎች፤ በጎንደር፣ በወሎ፣ በአፋር
በኩል ወደፊት ገስግሶ ወደ ወርቅ አምባና ጎያ፣
ወደ ሕንጣሎና ሽኩት፣ ወደ አጉላ ተቃርቧል፡
፡ ይህ ፅሑፍ ወደ ኅትመት ሲሄድ፤የመጨረሻው
ፍልሚያ ኅዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም በመቀሌና
አቅራቢያዋ መካሄዱ ይፋ ሆኖ ነበር፡፡ ከዚያስ
መቀሌ ምን ትሆናለች? የኢትዮጵያውያኑ
የትግራይ ልጆች ነፃነት ትንሳዔ ወይስ የሕወሓትና
የድርጅቱ ዕብሪተኛ መሪዎች የመከፈኛ ጨርቅ?
ለማንኛውም የ‹‹ታሪክ አተላና የኢትዮጵያውነት
ክህደት አዝመራ የለማበት›› የወያኔ ነገር ‹‹እጅግም
ስለት ይቀዳል አፎት፤ እጅግም ዕብሪት ያደርሳል
ከሞት›› ይሉት ነገር ሆኗል፡፡ ታሪክም በሂደቱ
ወደ አዲስ ታሪካዊ አስተምህሮ ክፍል የሚወስደን ይመስለኛል
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ