Ethiopia
ሁላችንም ልንገነዘበው የሚገባው የኢትዮጵያ
ዕጣ ፈንታ በአሜሪካ ወይም በአውሮፓ
የሚወሰን አለመኾኑን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሕዝብና
በኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ነው፡፡ ይኸንን በደንብ
አድርገን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ለሦስት ሺህ ዘመን
ነፃነታችንን ያስጠበቅነው የነጮችን ወይም
የአውሮፓውያንን እግር እየሳምን አይደለም፡
፡ እንደውም አውሮፓውያን እኛ ጋር መጥተው
ሊያንበረክኩን ሲሉ አስተምረን የላክናቸው ነን፡
፡ በአድዋ ቢባል በሁለተኛው የዓለም ጦርነት፣
ቀደም ባሉት ዘመናት ግብጽ ለመውረር በሞከረች
ጊዜ ሁሉ በራሳችን አቅም በመተማመን
መክተናል፡፡ ስለዚህ እኛ የምንቀጥለው እኛ
በወሰንው ውሳኔ ብቻ ነው፡፡ በርግጥ ከውጭ
ብዙ ተጽዕኖ ሊያደርሱብን ይችላል፡፡ እነዚያ
ተጽዕኖዎች ምናልባት የኢትዮጵያን ልማታዊ
ግስጋሴ ሊያዘገዩት ይችሉ ይኾናል፡፡ ግን መጨረሻ
ላይ መደርሳችን አይቀርም፡፡ ይኽንን ሁሉ ትግል
አልፈን መጨረሻ ላይ ስንደርስ ለአፍሪካ ጮራ
ነው የምንኾነው፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያን
ተመልከቷት፣ ያ ኹሉ ተጽዕኖ ደርሶባት፣ ያ
ጫና ተደርጎባት ሊያሸንፏት አልቻሉም፡፡
ሦስት ሺህ ዘመን ነጻነቷን አስጠብቃ ቅኝ
ሳትያዝ እስከዛሬ የደረሰችበት የራሷ ምክንያት
አላት፡፡ በእኔ እምነት ኢትዮጵያውያን በጣም ልዩ
ሕዝቦች ነን፡፡ ኢትዮጵያ ከሌላው የምትለይባቸው
ብዙ ማሳያዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ በመጽሐፍ ቅዱስ
ከ40 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች፣ ነብዩ መሐመድ
ተከታዮቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ ሒዱ እዚያ
ጥሩ አገር ጥሩ መንግሥት አለ ኢትዮጵያን
አትንኩ ብለው የተናገሩባት ሀገር ናት፡፡ የአፍሪካ
ሕብረት የተቆረቆረባት ሀገር ኢትዮጵያ ናት፣
የመንግሥታቱ ድርጅት ሲመሠረት ግንባር
ቀደም መሥራቿ ኢትዮጵያ ናት፡፡ በ1940ዎቹ ደማ፣ በዓለም ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ
ኢትዮጵያ ሁልጊዜ ነበረች፡፡ ከአፍሪካ ሀገራትም
ትለያለች፣ ከሌላውም ዓለም እንዲሁ፡፡ ስለዚህ
እኛ እራሳችንን አለማወቃችን እንጂ ከዓለም
የተለየንና ገናና ማንነት ያለን ኩሩ ሕዝቦች ነን፡፡
ሁሌ እኛ የምንዳከመው ራሳችን በራሳችን እንጂ
ማንም የውጭ ኃይል በግሮን አይደለም፡፡ ይኽን
ደግሞ እኔ ሳልኾን ታሪክ ምሥክር ነው፡፡ ወደኋላ
ዞረን እንመልከት እስቲ፣ ግራኝ አሕመድ ሞከረ
ጠፋ፣ ጣሊያን ሞከረ ጠፋ፣ ፖርቱጋሎች ሞከሩ
ጠፉ፣ እንግሊዞች አጼ ቴዎድሮስ ላይ ሞከሩ
ጠፉ፣ ግብጾች ሞከሩ ጠፉ፡፡ ከውጭ ያሸነፈን
ኃይል የለም፡፡ ስለዚህ የሚያጠፋን የራሳችን
ጥላቻና የራሳችን አለመተማመን ብቻ ነው፡፡
የእንስሳት መብት እንኳን በተከበረበት በ21ኛው ከፍለ ዘመን ብልት መስለብ፣አይን ማውጣት፣ ሰው መብላት የመሳሰሉ አረመኔአዊ ድርጊቶች መስማት ይዘገንናል።
ምላሽ ይስጡሰርዝ