Chemical Formula አገናኝ አግኝ ፌስቡክ X Pinterest ኢሜይል ሌሎች መተግበሪያዎች - ዲሴምበር 20, 2020 file:///storage/emulated/0/Chemical formula.pdfhttps://www.ambachewmu3.blogspot.com አገናኝ አግኝ ፌስቡክ X Pinterest ኢሜይል ሌሎች መተግበሪያዎች አስተያየቶች
ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ) - ፌብሩዋሪ 10, 2021 ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ) ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ) ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በ ደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በእንጾር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በጥቅምት 7 ቀን 1902ዓ.ም. ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት በቤተሰባቸው አጠገብና ባባታቸው አገር ደብረ- ኤልያስ ሄደው የግእዝ ትምሕርት ቤት ቅኔ ተቀኝተዋል። የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ-ኤልያስ፣ በደብረ-ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በኋላ ወደ በ1918 ዓ.ም አዲስ አበባ በመሄድ በስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በኋላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ለትንሽ ጊዜ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ። የኢጣልያ ወረራ ሲከሰት ከልዑል ራስ ዕምሩ ኃይለሥላሴ ጦር ጋር በምዕራብ ኢትዮጵያ በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው በመያዛቸው ጣሊያን ከልዑል ራስ ዕምሩ ጋር በግዞት ለሰባት ዓመታት በፖንዞ ደሴት ና በሊፓሪ ደሴት ታስረው ቆይተዋል። ከዚያም የተባባሪ ኃያላት ወታደሮች በ1935 ዓ.ም. ሲያስመልጧቸው በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና በኦክስፎርድ ከገፉ በኋላ በተለያዩ የ መንግስት ተቋማት በተለይም በ ትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል። 1936 - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኛ 1937 - 1938 - የኢትዮጵያ ቆንሱል በኢየሩሳሌም 1938 - በ International Telecommunications Conference አትላንቲክ ከተማ ፣ ኒው ጄርዚ ወኪል 1938- 1942 - በተባበሩት መንግሥታት ቢሮ ኒውዮርክ ሠራተኛ 1942- 1948 - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይረክተርና ምክትል ... ተጨማሪ ያንብቡ
YouTube - ፌብሩዋሪ 11, 2022 https://youtube.com/channel/UC1uGQhXKz3wwjCgUNTpWR8g https://youtube.com/channel/UC1uGQhXKz3wwjCgUNTpWR8g ተጨማሪ ያንብቡ
በራራ - ቀዳሚት አዲስ አበባ (1400 - 1887 ዓም) - ፌብሩዋሪ 13, 2021 በራራ - ቀዳሚት አዲስ አበባ (1400 - 1887 ዓም) በራራ - ቀዳሚት አዲስ አበባ (1400 - 1887 ዓም) እድገት ውድመት እና ዳግም ልደት፣ ያልተነገረው የኢትዮጵያ ታሪክ (በሀብታሙ መንግስቴ ተገኘ) በተለያዩ አጋጣሚዎች፣ በቃለ መጠይቅ፣ በጻፍኳቸው አጫጭር ጽሁፎች፣ ባሳተምኳቸው መጽሐፎች የኔ ትውልድ ከነበረው ቀናነትና የሃገር ፍቅር ባሻገር ከድንቁርና በመጣ ድፍረት የተናገራቸው፣ የጻፋቸውና የሰራቸው ስራዎች ዛሬ ሃገራችን ላለችበት አሳፋሪ ድህነት፣ ደም መፋሰስና አስከፊ የኑሮ ሁኔታ ጉልህ የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል በማለት በተደጋጋሚ ተናግሬያለሁ። ይህ ትወልድ ተምሬያለሁ የምንለውን ትውልድ ብቻ የሚመለከት እንደሆነ ልብ በሉልኝ። ይህ በሀብታሙ መንግስቴ ተገኘ የተጻፈ መጽሐፍ የኔ ትውልድ ብቻ ሳይሆን ከኔ ትወልድ በፊት የነበረውንና ከኔ ትውልድ በኋላ የመጣው ትውልድ፣ በተለይ ታሪክን አስመልክቶ የነበረው እይታ ከድንቁርና በመጣ ድፍረት ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ግልጥልጥ አድርጎ በመረጃ የሚያሳይ ነው። ትልልቆቹ የሃገራችን ስመጥር የታሪክ ምሁራን ሳይቀሩ የኢትዮጵያን ታሪክ በተለይ የመካከለኛው ዘመን የሚባለውን ከ13ኛው ምዕተ ዓመት መጨረሻ ጀምሮ እስከ 16 ምዕተ ዓመት መጨረሻ የዘለቀውን ታሪክ አስመልክተው የሰነዱት ታሪክ ስህተት የተሞላበትና ትልቅ ጉድለት የታየበት እንደሆነ ያሳያል። በተለይ ደግሞ ወደ ዘመናችን ስንመጣ ታሪክን የፖለቲካ መሳሪያ ለማድረግ በማሰብ በጽንፈኛ ብሔርተኞች የተጻፉ መጽሐፎችና በምሁራኑ የሚቀርቡ ትርክቶች ከማናችንም በላይ በድንቁርና ላይ በተመሰረተ ድፍረት መጻፋቸው ብቻ ሳይሆን አደገኛነታቸውን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ መጽሐፍ ነው። ይህ የዛሬው ጽሑፌ “በራራ”ን የተመለከተ የመጽሐፍ ግምገማ አይደለም። ይህን መጽሐፍ... ተጨማሪ ያንብቡ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ