ፖርኖግራፊ

#ፖርኖግራፊ
ፖርኖግራፊ የሞራል ችግር ውድቀት ተብሎ
በአብዛኛው ቢታይም ከዛ
ባለፈ በዋነኝነት ከአዕምሮ ጋር የተያያዘ ችግር ነው።
ስለ ፖርኖግራፊ
ስንነጋገር ከላይ እንደተጠቀሰው አይምሮአችን እንዴት
እንደሚሰራ
መረዳቱ አስፋላጊ ነው።
ለምሳሌ አንዲት እናት ልጅዋን በደረትዋ አስደግፋ
በምታጠባበት ጊዜ
አይምሮዋ ‘ኦክሲቶሲን’ የሚል ‘ኒውሮኬሚካል’
ይፈጥራል። ይህም
ኬሚካል አንዲት እናት በውስጣዊ ስሜትዋ ከልጅዋ
ጋር እንድትተሳሰር
የሚያደርግ ሲሆን፤ በወሲብ ጊዜ ሰውነታችን
የሚኖረው የኬሚካል
ሁደትም ይህን ይመስላል። ፈጣሪ በሰውነታችን
የሚለቀቀውን ይህን
የኬሚካል ሁደት በባለትዳሮች መካከል የሚደረግ
ወሲብን ተከትሎ
ስሜታዊ ትስስር የመፍጠር አላማ ቢኖረውም፤ ከትዳር
ውጭ በሆነ
በተለያየ ወሲባዊ ድርጊት ውስጥ አሉታዊ ተፅዕኖ
ይኖረዋል ።
ሰዎች ፖርኖግራፊ በሚጠቀሙበት ጊዜ የሚለቀቁት
እነዚሁ
የ’ኦክሲቶሲን’ ‘ኬሚካሎች’ ተመልካቹ ከሚመለከተው
ምስል ጋር
ስሜታዊ ትስስር እንዲኖረው ያደርጋል። በግለ ወሲብ
ሱስም ውስጥ ያሉ
ሰዎችም በእነዚህ ኬሚካሎች ከራሳቸው ጋር ትስስር
ይፈጥራሉ።
በተደጋጋሚ
የሚደረግ ማናቸውም ነገር በአይምሮ ላይ እንዳላቸው
ተፅህኖ ሁሉ
ፖርኖግራፊም የአይምሮአችንን ቅርፅ በመቀየር
በፖርኖግራፊ እስራት
ውስጥ መውደቅ ያስከትላል።
ስለዚህ ስለፖርኖግራፊ እስራት መውጫ መንገዶች
ስናወራ ወደ ሱሱ
ሊመሩ የሚችሉ ነገሮችን፤ ተያያዥ ባህሪዎችን እና
አመለካከቶችን
አብረን ማንሳት ይኖርብናል። ከሁሉ ቀዳሚው ነገር
ከላይ እንደጠቀስነው
ችግሩ እንዳለ ማመን ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ)