ብላቴናው ቴዎድሮስ ካሳሁን

ብላቴናው ቴዎድሮስ ካሳሁን
እኔ በሠው ነገር አልጠቁር አልከሳ
የሠዉ መዉደድ ይስጥህ እንደ ቴዲ ካሣ።
#እድለኛው_ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ!!!
ቴዎድሮስ ካሳሁን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት እንደማተቡ የሰረጸው፣ኢትዮጵያን እልቡ ላይ የተነቀሳት፣የሀገር ፍቅርና መውደድ ሞልቶት ጢም ያለው፣በሙያ ቅቡልነቱም ሀገሩን ተሻግሮ አህጉር አቋርጦ በዓለም ላይ የናኜ ጠረፍ አጥ ድካ አልባ ሙያተኛ ነው፡፡
ብላቴናው ቴዎድሮስ ካሳሁን በሀገር ፍቅሩ በሙያ ክብሩ በሀገሬው ልብና ልቦና ዘልቆ ጠልቆ የገባ ጠቢብ ጥበበኛም ነው፡፡
ምኑም የሚሰምርለት ሙዓዘ ዜማ ሣልሳዊው ቴዎድሮስ ሙዚቀኛ ብቻ ሣይሆን እሱ እራሱ ሙዚቃ ነው፣የደረበው የጥበብ ካባ የደፋው የተሰጥዖ አክሊልም ሞገስ አጎናጽፎታል፤ይህነቱን ለመመስከርም ሳር ቅጠሉ ድንጋይ አፈሩ ተፈጥሮ ሙሉ አንደበት አላቸው፡፡
ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ልዑል የጥበብ ራስነቱ ብቻ አይደለም የሚስደንቀው፤ይለቁንም በወጀብ የማያናወጽ ብርቱ፤ግፊቱም የማያንገዳግደው ጽኑ መሆኑም እንጂ፡፡የሠብዕና ልዕልናውም ከከፍታው እንዳይወርድ አድርጎታል፤ይህም ለጥበብ አንቱነቱ በወል እንድንስማማ አድርጎናል፡፡
ቴዎድሮስ ካሳሁን እሱ ስለፍቅር በፍቅር አቀንቅኗል፣ስለተፈትሮ ተቃኝቷል፣ታሪክን ከምሩ ዘክሯል፣በተልይም ስለሀገር አንድነት በአያሌው ሰብኳል፣ስለዕምነት በጥበብ አዚሟል በዚህም ምንቀረሹ ቴዎድሮስ ሙዚቃ ጥበብን አልዕሏታልም፤፤
ልጁ ከጥበብ ጋር በክብር የተጋባ ጉድኝቱም የሠመረለት አክብሯት ያስከበራት ክብር የሚገባው ክቡር ሰው ነው፡፡
ይህንን ሰው ያከበረ እንደምን አይከበር፤እናም ለእኔ ጎንድር ዩኒቨርሲቲ ዕድለኛ ነው
ከብዙ ሳይንስ ተመራምረው ማህበረሰብን አጥንተው ዶክትሬት ካገኙ ግን ቡዙ ህይወታቸውን ጥላቻ እና ቂምን ከሚዘሩ የፍቅር ጠላቶች ይልቅ የቴዲ የክብር ዶክትሬት እጅግ ዋጋ አለው። ቴዲ ስለ ፍቅር ፣ ስለ ይቅርታ እያወራ ሀገር ሊሰራ ሲደክም የኖረ ሰው ነው። "ተዋደዱ" እንጂ "እኛን ብቻ ውደዱ" ሲል ያልተደመጠ ፤ ከማንም ቀድሞ ያን ክፉ አገዛዝ በተግባር የታገለ ነውና ይገባዋል!! 
ብቻውን ሀገር የሆነ ሰው!! እንደውም ሌሎቹ ዩኒቨርስቲዎች በመቀደማቸው ሊቆጩበት ይገባል።
ቢዘገይም ሹመት መርፈዱን ሳናውቀው ፣
በሚዛን ሳንለካ በፍቅር መትረን አንተን አገኘን ሰው 
በትንሳኤው ማግስት በድል መንሻው ቦታ ፣
ሀገር አፍሮ'ን ሰጠን ለፍቅር እኩሌታ። 💚💛❤️
#አንተ አምሳለ ያሬድ - የሙዚቃው ንጉስ 
ከኢትዮጵያ በታች - የማትልከሰከስ
ብትባል ያንስሃል - ሳልሳዊ ቴዎድሮስ !!
በአስራ ሰባት መርፌ በያስተሰርያል
በድምፅህ ነጎድጓድ እኩያን አፍረዋል
በአንደበትህ ለዛ በፍቅር ያሸንፋል
ስንት ለስንት 'ሚለው ፌዘኛው ተማርኳል !!
ኢትዮጵያ ብሎ ሲዘምር የማይቆም እምባን ከልብ ቤተመቅደስ እንድታመነጭ ያስገድድሀል።
በሰዓታት ለጀግኖቹ የዘላለም የድል ስንቅ ፣ ለኢትዮጵያውያን የጀግኖቻቸውን መታሰቢያ፣ የኦሎምፒክ ትንቅንቅን፣ የአንድ ክንድ ትብብርና ቁርኝትን፣ ሀገራዊ ስሜትንና አሸናፊነት በቅኝት ገልፆ ሲያዜመው እጅ ባፍ አስይዞናል። አንገት ላንገት አቆላልፎ አስለቅሶናል፤ይቀጥላልም" ቀነኒከኛ ልዩ ዜማ ነው።አንበሳ! ቀነኒሳ" በተለይ ለጀግኖቹ የህዝባቸውን የጀግና ማበረታቻ ሲዘምረው አንበሳውም የሚያገሳ ይመስለኛል። "አልሆንልህ አለኝ ሀይሌ አንተን ጥሎ መግባት ለኔ" የ ሀይሌ ገብረስላሴ ቀነኒሳና ስለሽ የአሸናፊነት ብቻ ሳይሆን የመጠባበቅ የመከባበርና የአንድ እናት የአንድ መንፈስ ስሜት አለምን ያስደመመ ትዕይንት! ገልፆታል ብቻ ገልፆታል! በቃ ሰውየው እሱነዋ!
 
   አንተ ማለት ለእኔ አንተ ማለት ለእኛ 
የፍቅር አርማ ነህ የፍቅር አርበኛ ።
ሚኒሊክ በኖረ ቀና ብሎ ባየህ
በጥቁር ዜማ ዶክትሬት በሠጠህ።
ቴዎድሮስ በኖረ ቀና ብሎ ባየህ 
ትላንት ከጎንደር ላይ ሊሻን በሸለመህ።
በላይ የለም እንጂ ያ ኩሩ ቀብራራ
ባነገሰክ ነበር ኢትዮጵያን ስትጠራ ።
የትላንቱ ክብር የስራህ ውጤት ነው።
ቲዎድረስም ቢኖር የሚለው ይህን ነው።
ጀግና የጀግና ዘር የጥቁሮች መለያ 
የሚኒሊክ አምሳል የፍቅር ማሳያ 
የኢትዮጵያ ኩራት ልክ እንደ አድዋ ።
አርማችን አንተ ነህ እንደ ባንድራዋ
ከመጣው ከሄደው ጋር.... ያላሸረገደ
እውነትን በፍቅር... ይዞ የተራመደ
በአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ..አቅፎ እየገመደ
ከኑሮ በላይ ሆኖ ..ኖሯል እንደተወደደ።

#ብቸኛው_ኢትዮጵያዊ!
👉መንግስት እንደአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ የሚቆጥረው ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ቴዲ አፍሮ ነው።
👉ሀገሩ ላይ ሰርቶ ለመብላት ከመንግስት ፈቃድ የሚጠይቅ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ቴዲ አፍሮ ነው።
👉ሀገር ውስጥ ባይኖርም የጎዳና ተዳዳሪ ገጭቶ የሚታሰር ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ቴዲ አፍሮ ነው።
👉“አበበ በሶ በላ” ብሎ ቢዘፍን የስፖርት ተንታኞች አበበ ግደይን ለመተቸት ነው ብለው ዘፈኑን የሚተነትኑለት ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ቴዲ አፍሮ ነው።
👉በአማርኛ ቋንቋ የዘፈነውን ዘፈን ኬንያ ለማስመረቅ የሚገደድ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ቴዲ አፍሮ ነው።
👉ሀይለማርያም ስልጣን ሳይለቅ ፣ አብይ አህመድ ሳይታወቅ ፣ ጌታቸው አሰፋ ሳይደበቅ ፣ ህወሃት ሳይገረሰስ ፣ ዘረኝነት እንዲህ ሳይነግስ ፣ አክቲቪስቶች እንደ አሸን በሀገሪቱ ሳይፈሉ ፣ ታጥቀው የሸሹ ታጋዮች ትጥቅ አንፈታም ሳይሉ ፣ ቄሮዎች ሳይፀነሱ ፋኖ ዘርማና ኤጀቶ ለትግል ሳይነሳሱ እንደካህን ፍቅርን ሰብኮ "ፍቅር ያሸንፋል" ያለ ለትውልዱ ጭቆናን በአንደበቱ የታገለ. . .ይህ ሰው ነበር!!! 🙏
የጥበቡ ንጉስ.... የጥበቡ መሪ
አንድ ሆና ለእናቱ... እንደ ሀገር ተጠሪ
ቴዲ የህዝብ ነው.. ኢትዮጵያን አፍቃሪ
ማንገስ ያውቃል ጎንደር ...እናቱን አክባሪ።
ይገባዋል የሚል... ከእውነት ጋር አባሪ?
ሰው ማለት እሱ ነው...የፍቅር ተባባሪ
ሰላምን የሚሻ... የሰላም ዘማሪ 
አቡጊዳ ብሎ... የፍቅር ጀማሪ
በህይዋን እንደዋዛ ...ፅናት አስተማሪ
በሼመንደፈር ክታብ... አፍቅሮ አፋቃሪ
በጥቁር ሰው ሃዲድ... ዘመን ተሻጋሪ
ቴዲ መፅሐፍ ነው.... ብቻውን አናጋጋሪ
በሁሉም ገፆች ላይ...#ኢትዮጵያን አፍቃሪ።
ግን ግርም እያለኝ ያለው፥ 

በጭራሽ አይደለም ቴዲመሸለሙ እሱማግድነው  
ይገባዋልና ከፍ ብሎ ይታይልን የምንወደው ስሙ፤ ቴዲ ቴዲ አፍሮ... ቴዎድሮስ ካሳሁን፣
በስምህ ዝነኛ በስራህማማር ብቃት መነጋገሪያ ሁን፤የተባለልህ እየተወራልህ የሚነገረው
ከጥንትም ስናውቅ... ከሁሉ ይበልጣል..ፍቅር ያሰረው በፍቅር መታሰር እንጂ ፍቅርን ማሰር... እንዴት ይቻላል
ያለእርሱ ህይወት...አይሆንም ቀላል።
ሩቅ ሄዶ ማያድር ....አይወድም ጉዞ
አይለቅምና.... እናቱን ይዞ
ጭፍን የሆነችን... ጨለማ ዓለም
በላምባዲና ...አርጓታል ለምለም
እጅግ ደስ ይላል.... የቴዲ መሸለም!
ቴዲ አፍሮ የታላቋ ኢትዮጵያ የረጅም አመታት ታሪክ አቀንቃኝ የብሔር ብሔረሰቦች የአንድነት መሰረት ድልድይ የእምነት ተቋማት የክብር እና የመቻቻል መሰላል የኢትዮጵያ ህዝቦች የነፃነት ነጋሪት ጎሳሚ የታላቋ ኢትዮጵያ የታሪክ መዝገበ ቃላት የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ድምፅ የአፍሪካዉያን ኩራት የእምዬ ሚኒሊክ የድል ታሪክ ምስክር የአንድነታችን አቀንቃኝ የኢትዮጵያዊነት ምርኩዝ ዋልታና ማገር ምንም ቢደረግለት አይበዛበትም ያንስበታል ቴዲ የኢትዮጵያዉያንን ዝምታ ሰባሪ የነፃነት ድምፅ ነው ጎንደር ዩኒቨርስቲም ታላቁን ሰው ለዚህ ክብር በመጋበዙ ሊመሰገን ይገባል ሌሎችም ዩኒቨርስቲዎችም ልክ እንደ ጎንደር ዩኒቭርስቲ የሀገር የወገን ድምፅ ተምሳሌት የሆኑ ዜጎቻችንን በየስራ መስካቸው ለትውልድ አርአያነታቸውን እንዲያስተላልፉ የጎንደር ዩኒቨርስቲን አርአያን እንድትከተሉ 
እኔም እንደ ሮፍናን.. ልጠይቅ #ጥያቄ?
አውቄ ካልኖርኩኝ... አልባልም ነቄ
ካሳ ሁን ለሀገር.... ለወገን ደርሰህ
በቴዲ ልጅህ ...ይኸው ቀን ካሰህ
አሁንም ደገምኩ.... ሌላ ጥያቄ?
ሀገሬን እንደ ዓይን... ልያዝ አጥብቄ
በቃ ልሰልስ... በዚህ ጥያቄ?
እናት ናት ለኔ... የምንግዜም ወርቄ፣
በእርሷ(በራዬ) ደስታ ነው.... የምኖረው ስቄ፤

#አፍሮ ይህን ሁሉ ታሪክ... ላገሩ ከሰራ?
#ደፍሮ ያሳየን አምላክ ግዙፍ ሆኖ በልጦ ከትልቅ ተራራ
የትም የሚሰማ ቋንቋችን ይሆናል ሁሌም የሚወራ !!!

መትረየስ ሳይኖርህ፣ በቃል ተኩሰሀል
ለኢትዮጵያዊነት፣ ክፉን ተጋፍጠሀል
ሽጉጡ ሳይኖርህ፣ ምስጢር ጠጥተሀል።
የታሪክ አጥፊዎች፣ አዝማሪ ይሉሀል
ሰብዓዊ ክብርህን፣ መቸ አውቀውልሀል?
ውስጥህ የገባቸው፣የካሳ ያልሀቸው።
ዶክተር ብለውሀል፣ ቢያንስም ይገባሀል።
ቦታ ባይኖርህም፣ ለክብር ለዝና፣ 
ለአንተ ቢያንስብህም፣ ዶክትሬት ዕውቅና
ክብሩን ተቀብለህ፣ ለኢትዮጵያ ቅና
ዳግማዊ ቴዎድሮስ፣ የህዝብ ልቅና።
 
በፍቅር ዜማው ምስጥርን ታሪክ አላብሶ ሲዘፍን ዜማውን ትመስጥና ግጥሙ እያደረ እንደ ወይን ይጣፍጣል እያደረ ቅኔው ይገለጣል ደግሞ እያደረ ሌላ ቅኔ ይሰጣል ግን ምን ያጃጅለኛል ብለህ ካልተውከው ቅኔው ቅኔን እየወለደ የልጅልጅ ልጅ ታወጣለታለህ። 
ሰውየው ራሱ ቅኔ ነዋ!
የኢትዮጵያን ጭንቅና መከራ ቀድሞ የታገለው አደባባይ ላይ
" ጃ! ያስተሰርያል" ሲል ነበር።
"በአስራ ሰባት መድፌ በጠቀመው ቁምጣ"

" አዲስ ንጉስ እንጅ ለውጥ መቼ መጣ"!

ይህን ስታነብ ከነ ስርቅርቅ ለጋ ድምፁ አስታውሰህ የጎደለውን ሞልተህ

" አንድ አርገን መልሰህ" እያልክ ልብህ ቁጭ ብድግ ታሰራሀለች። ሰውየው ገና የልጅ አርበኛ ነዋ!
በወቅቱ ጦርሜዳም አብሮህ በዚህ ዜማ ይዋጋል ድል አለ ከፊትህ!

ሲበዛ ቀና መንፈሳዊ እና ለወገኑ ፈጥኖ ደራሽ ነው። በተለይ በሳውዲ የሞት ፍርድ የተፈረደባትን ሴት እንዴት እንዳተረፋት ትዝ አይላችሁም ብየ ባስብ ሰውየውን የማያቀው ገና ያልተፀነሰ መሆን አለበት። ከተፀነሰማ ፍቅርም የሚጀምሩት አንሶላም የሚጋሩት በማን ዜማ ሆነና! ፊዮሪና፣ ሳማት ሳማት አለኝ፣ ወዘተ
ኧረ ቆንጆዋ ፍቅረኛህ ተሽቀርቅራ ስትወጣም አላምን አላምን አላምን እያልክ እየተሸበርክ አዚመሀል። ታዲያ ተፀንሶ አያውቀውም አትበለኛ። ንጉሱ ሙሽራ ነውና!
የፍቅርን ብራና የደግነት ዳዊት
ሊቁን ጥበበኛ የሰማዩን ውቅርት
የሰንበትን ቀዳሽ ዉዳሴ ኣድራሹን
ኣነገሱት በክብር ሰተው ዶከትሬትን
መረቁት መፅሀፉን የጥበብን ታዛ
የካሳሁንን ልጅ በፍቅር ቢወዛ
ተዉ ድሮስ ውበት ነው ከዛሬ ያልመሰለ
ኣትከራከረኝ ከእድሜው ቀድሞ የዋለ
ምንኣልሽ እማዉ ራዬ
ደስታሽ እንባ አየ ወይ
ምትክ ኣልባዉ ልጅሽ
ሲነግስ በኣደባባይ
ኤሚ የዉበት ንግስት 
ምን ተሰማዉ ልብሽ
ለክብር ኣስኬማ
ሲታጭ ንጉስ ባልሽ
ፍቅርን ያስተማርከኝ ታላቄ ኣባቴ
ከእድሜዬ ቀንሶ ይሰጥህ ቁመቴ
አርቲስት ማለት ለጥቅሙ የሚያጎበድድ ሳይሆን ስለሃገሩ ያለውን እውነታ በተሰጠው ጥበብ የሚገልፅ ይህም ማለት መልካሙን መልካምነቱን ክፉውንም ደግሞ በይቅርታ እንዲታደስ የመከርክ እና ስለ እናት ሃገርም በሚገባው በላይ ፊትለፊት ቆመህ አልሄድ አለኝ እግሬ አልሄድ አለኝ እስከማለት በስቃይ ላይ ሆነህ በእናት ሃገርህ ተስፉ አለመቁረጥህን እና ፉቅር ያሸንፉል በማለት ለአለህ ቆራጥ አቋም ፉቅር አሸንፎ የኃላው ከሌለ የለም የፊቱ ብለህ አያቶቻችንን ባከበርክበት የጥበብ ሙያ አንተንም የሚያከብር ትውልድ ስላገኘን ደስታው ያንተ ብቻ ሳይሆን ለእኛም ጭምር ነው ምክንያቱም ሰው ለሃገሩ ባለው ፉቅር እና ክብር መስዕዋትነትን እስከመቀበል ድረስ ለሄደ ጀግና በሃገሩ ሲከበር እንደማየት የሚያስደስት ነገር አለ???
አርቲስቱ በገናን ይዞ አምላኩን ያስባል። እንዲያውም ማሪያምን ካለ በቃ ሰውየው ቃል ገብቷል። የሁለተኛ ልጁም ስም ማሪያማዊት ነች። ማሪያምን በፍፁም ልቡ ይወዳታል። ያከበራትን ታቃለች የክርስቶስ እናት ህይወትን ከልብህ ኑር ያለችው ይመስላል። ጣፋጭ ህይወት ይኖራል።
ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል...ህይወት በምድር ላይ አጭር ናት፣ ለሌሎች ፍቅርን፣ ተስፋን፣ መልካምነትን፣ መተሳሰብን፣ መረዳዳትን፣ አክብሮትን፣ ትህትናን፣ ቀናነትን ዝራበት። ይገባሃል, የኢትዮጰያ ብርቅዬ ልጅ።
ልባም በጠፋበት መብራት ጨለመና
ምድር አፈለቀች ትንሽ ብላቴና
በሳቱ መርዝ ላይ ውሃ ያፈሰሰ
በድምጽ አልባ ቃላት ፍቅር ያነገሰ
በለጋነት እድሜው ዘፈን መረጠና
ፍቅር አጠመቀን አንድ አደረገና
በሰሜን በደቡብ ምእራብና ምስራቅ 
ቋጥሮ የሰደደ ያንድነትንም ስንቅ
ከፊት ያስቀደመ ያገርን ባንዲራ
ባለም እሱ ብቻ በሰላም የመራ
እናም ቀኑ ደርሶ ብድር መመለሻው
ይኸው ተዘመረ በጎንደር ላይ ባሻው
ባለም የከሰመው ፍቅራችን ሊመለስ 
ባንድነቱ ቃላት ባዝማሪው ሊታደስ
መርከቧ ሳትሰምጥ ክብር ተንሳፈፈ
ባገሬ ምድር ላይ ፍቅር አሸነፈ ።
ሰውየው ሁሉም ይወደዋል። ብዙወቹ በንጉሱ ፍቅር የናወዙ ያለሱ ዜማ የማይሰሙ የሱን ፎቶ በሁሉነገራቸው የሚያስቀምጡም አሉ። በቃ ተወደድ ካለህ ሁሉን ትሰጣለህ ልክ እንደ እሱ ምክንያቱም በፍቅር የሚያንበረክክ ለፍቅር በቃል ሳይሆን በተግባር የሚንበረከክ ሰው ነው።
ለሀገሩ ልዩ ፍቅር አለው በጣም ጣሪያ የነካ ይመስላል ፍቅሩ። ወደር የለውም። ስለሀገሩ ብዙ ዘፍኗል በዙ ግን "ኢትዮጵያ" የሚለው ስራው እምባችንን እየጠረግን የምናዳምጠው ዜማ ነው። ሰውየው ያሳብድሀላ በቃ ይችላል።

"በሰማዩ ላይ ቢታይ ቀለም፣
የእርሷ ነው እንጂ ሌላ አይደለም"።
ሀገሬ
ባንቺ አይደል ወይ ክብሬ!

አድዋ፣ አባይ፣ ሚኒሊክ ጥቁርሰው የቱን ልጥቀስ የቱስ ይባላል ቢጨንቀኝ እንጂ ሰውየው ቡዳ እንደበላው ያስወሸክትሀል።ያለህ አማራጭ አፍህን በ እጅህ መያዝ ነው። ምክንያቱም ሰውየው ያለምርጫ የምታነግሰው እሱ ነው።

በተለይ
ጎንደር ጎንደር
የታሪክ ሀገር
የቴድሮስ ሀገር
ያንዲት ኢትዮጵያ ዋልታና ማገር። እየጮህክ እየዘለልክ አብረኸው ትዘፍናለህ ላብህ ልብስህን ያስወልቅሀል። ውስጥህን በወኔ አናውጦ ያስጮህሀል። የሀገር ፍቅር አከናንቦሀልና። ሰውየው ጀግና ነው።

ዛሬ ባከበራት ሙሽራዋ ጎንደር የክብር ዶክትሬቱን ተጎናፅፏል!

ሰውየው
ክቡር ዶክተር አርቲስት ቴወድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

ሸማ ለጥለቱ
ጉንጉን ለአንገቱ
እርሱ ነው አርቲስቱ
ቅኔ ቱርፋቱ
ፍቅር ምልክቱ!
#አንተ_ራስህ_ጥቁር_ሰው
ክፉ አባዜን የሰረዘ የጽልመትን ጨርቅ ያስጣለ
ገዳዮችን ከሟች አምባ ባንዲት ጥበብ የነጠለ
ሩቅ መስላን የናፈቅናት ከቅርብ ሀገር ላለች እውነት መሬት ወድቃ ክብራችንን የመለሳት ከሰገነት ታሪክ ማወቅ እውነት ማውራት በሚያስኮንን ሰነፍ ጊዜ በጉብዝና ያበረታን ያነቃንም ከፍዛዜ በክያኔው ጀግንነትን ሰውንትን በመሰለው የኔ ዘመን የኛ ዘመን እሱ ራሱ ነው #ጥቁር_ሰው!
#ኪራአቢጋሮ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ከክፉ አይኖች ይሰውራት

" ጃህ ያስተሰርያል"

ዝም ብለህ ተቀምጠህ እንኳ "ምን እያሰብክ ነው?" ብሎ መንግስት ዘሎ በሚያንቅበት በዚያ አስፈሪ ጊዜ እንዲህ ብሎ ላንተና ለሀገርህ በድፍረትና በጥበብ የጮኸ ሰው ነውና ላስታውስህ ብዬ ነው👇🇪🇹❤
ክቡር ዶክተር ቴዎድሮስ ካሳሁን🙏

" ጃህ ያስተሰርያል"
ግርማዊነታቸው ከዚህ ሰረገላ
ወደ ዋገን ወርደው ሲተኩ በሌላ
በአዛውንቶች ራስ ስልሳ ጉድጓድ ምሳ
አብዮት ሞላችሁ የተማሪ ሬሳ
ጃህ ያስተሰርያል...

በአስራ ሰባት መርፌ በጠበቀው ቁምጣ
ለለውጥ ያጎፈረው ዙፋን ላይ ሲወጣ
እንዳምናው ባለ ቀን ያምናውን ከቀጣ
አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ
ይቅር በለውና የበደለን ወቅሰህ
ምህረት አስተምረን አንድ አርገን መልሰህ❤
ጃህ ያስተሰርያል...
ሳባዊ እስራኤል እማማ
ኢትዮጲያዬ ስሚ እማማ
አቢሲንያ እማማ

ቂም በቀል ክፉነው - እማማ- ከአምላክ ያለያያል
ተዋዶ መትጋት ከቅጣት ያስተሰርያል
ኦኦሆ ያስተሰርያል...
ጃህ ያስተሰርያል...
ዘፀአት ለኢትዮጲያ ወደ ተስፋ ጉዞ
ባህሩን ሚያሻግር አንድሙሴ ይዞ❤
ቅርብ ነው አይርቅም የኢትዮጲያ ትንሳዔ
ባንድነት ከገባን የፍቅርሱባኤ❤

ጃህ ያስተሰርያል...
ፍቅር አተን እንጂ በረሃብ የተቀጣን
አፈሩ ገራገር ምድሩመች አሳጣን😢
ኦሲሳ ኦሲሳ ኦሲሳ አማዴላ
ይቅር አባብሎ እንዳስጣለ ቢላ
በተስፋዋ መሬት እንዲፈፀም ቃሉ
ሞፈሩን ያዙና ይቅር ተባባሉ
ጃህ ያስተሰርያል...
እማማ ኢትዮጲያዬ - እማማ
ሳባዊ እስራኤል - እማማ... 
ኢትዮጲያ ስሚ - እማማ 

ይህን በክፉ ቃል - እማማ
አቢሲንያ
ይህንን ሲወቅሰው 
ይሄም በጥላቻ ይህንን ሲወቅሰው 
ለመለየት አቃተን የሚበጀንንሰው
ኦ…

ያስተሰርያል...
እማማ ኦሎሄ ኤሎሄ - እማማ ላማሰበቅታኒ
እማማ - ኢትዮጲያዬ እማማ - አትሰማኝም ወይ በይ
እማማ - ማማዬ
እማማ ጃህ ማለት ፈጣሪ እማማ መሰርይ ይቅርታ
አኛ ስንዋደድ እማማ - ይሰማሻል ጌታ

እማማ - ኦሎሄ ኤሎሄ እማማ ማማዬ...

እማማ እስቲ ተዋደዱ ይያያዝ እጃችሁ
አለበለዚያማ
በምን ያስታውቃል እኛን መውደዳችሁ
እማማ አቤት ስቃይ አቤት ጠኔ
ሰማይ ጨክኖ በወገኔ
ስንት አሳልፈን አልቅሰን ሳናባራ ብለን ወይኔ
እዚህ ጋር ደሞ ሌላ ትኩሳት
ወገኔ አለቀ በወሲብ እሳት እሳት... እሳት..
ኸረ አይነጋም ወይ አይነጋም ወይ
አይነጋም ወይ ሌቱ ኢትዮጲያዬ
እማማ ማማዬ ሳባዊ እስራኤል እማማ..
ለሁሉም ሰው ምሳሌ ነህ የሰውም የሃገር ፍቅርብ ያለብህ ለሄደ ለመጣ የማታሺቃብጥ የጥበብ ሰው እንኳን ደስ ያለህ የጎንደር ህዝብ ሳላደንቅህ አላልፍም ሁሌም ክብር ለሚገባው ክብርይሰጣል በህይወት እያለ ሞራል ይሆናል ሲሞትምመልካም ዝናው እዳይረሳ የሚጥር ምርጥ ህዝብ ነው የየትም ክልል ይሁን አንድ ታሪክ መስራት የቻለ ጀግና ጎንደር ላይ ይወደሳል ጀግና ጀግናን ያበረታታል እጅ አያናንቅም እደ ቴዲ አፍሮ 
ቴዎድሮስ ካሣሁን በዚህ ሰዓት ስፍር ቑጥር የሌለው አድናቂ አለው።ስብዕናውን፣ ተሰጥዖውን፣ ልባምነቱን፣ሩህሩህነቱን አሥተዋይነቱን...ወዘተ... ምክንያት ያደረገ አድናቆት ሲቸረው ቆይቷል፤ ይገኛልም።ሰው ሲያደነቀው ተመልክተው እያደነቁ ያሉ ቅኖችም ይኖራሉ፤ሰው ስለምን ይህን ያህል ርቀት ሄዶ እንደወደደው ለማወቅ በጣሩ ጊዜ አድናቆታቸው ከከንቱ አድናቂነት ተላቆ እውነተኛ አድናቂው ይሆናሉ።መጀመሪያውም የዋሃን ቅኖች እንጅ 'ጭፍኖች' አልነበሩምና።
ለመሆኑ ሰውን በጭፍን መውደድ ይቻላልን?
ብላቴናውን (ማን እንዲህ እንዳለው ባላውቅም) ግን በጭፍን ሳይሆን እርሱን ለመውደድ ከበቂ በላይ ምክንያት ስላለን ውድድ እናደርገዋለን። በጭፍን መውደድም መጥላትም ሚዛናዊ አያደርግም።
በጨለማው ዘመን ለወያኔ ያልተንበረከክ ምርጥ ኢትዮጲያዊ
-ኢትዮጲያ
-ቦብ ማርሌ
-ጡር ሠርተሽ በፍቅር
-ማራኪዬ
-ሸመንደፈር
-አድዋ
-ፀባየ ሠናይ
-ሄዋን እንደዋዛ
-ሌቦ
-ግርማዊነቶ
እነዚህንና ሌሎችምርጥ ስራዎች ያበረከትክልን የጥበብ ሠው ያንስብሀል መባል ዶክተር የጥበብ ሙዳየ ታላቅ እዉቀት አለ በአይምሮህ ምግባረ ሰናይ ፍቅር ያሸንፋል ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር💚💛
ብላቴናውን በጭፍን ሳይሆን በምክንያት የሚጠሉ ምክንያታቸው ምን እንደሆነ በዚህ ሰዓት ህቡዕ አይደለም።የፍቅር ሰባኪን የሚጠላ ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል?
ሙሉ ጃማይካ በቴዲ አፍሮ ዘፈን እየተናጠች ነው !!! የቦብ ማርሊ ቤተሰቦች በአንድነት << Respect Teddy afro 🙏 >> እያሉ ይገኛሉ፡፡

ቴዲ አፍሮ #ደሞ_በአባይ ሲል የተጫወተው ሙዚቃ ሙሉ መልዕክቱ በጃማይካ ቋንቋ ተተርጉሞም ቀርቧል ፡፡ የሙዚቃው ስልተ ምት በሬጌ ተወዳጅ ዘፋኞች ዘንድ እጅግ የተወደደለት ሲሆን "ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያ 14ኛው ወር ነው " ሲሉ ለብቻው ቀን ይሰጠው በማለት አሞካሽተውታል ፡፡

#ክሮኒክስ የተሰኘው ታዋቂ የሬጌ አቀንቃኝ " ገና በአፍላ እድሜዬ ንጉሳችን ቦብ ማርሊ ሲሞት ያቀነቀነውን በሰማሁ ጊዜ ነበር ቆይቶም ቢሆን እንዲህ ያለውን የጣፈጠ ስራ እንደሚሰራ የገባኝ" ብሏል፡፡ 

በእናቱ ጣልያናዊ የሆነው ባንድ ወቅት ኮንሰርቱን አዲስ አበባ ላይ ያከናወነው የቦብ ልጅ Damian marley " በተባረከችዋ ፅዮን ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ላይ የበቀለ ድንቅ ገፀ በረከት " ሲል አወድሶታል፡፡

Tanya Stephens,Rita Marley,Kelissa ... በመሳሰሉ ሴት የሬጌ አቀንቃኞች የተመሰረተው reggae for women ማህበር በበኩሉ በኢትዮጵያ የራስታዎች መንደር በሆነችው የሻሸመኔ ከተማ ላይ የተፈፀመውን ድርጊት አውግዞ "በራስታዎቹ መንደር የማስታወሻ ሃውልት በክብር እንዲቆም እናደርጋለን" ቃል ገብተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ መንግስት ለቴዲ አፍሮ የነፃነት ታጋይ የህዝብ ልብ ትርታ መሆኑን አምኖ አንዳች ካባ ሲያለብሰው ማየትን እናፍቃለሁ ፡፡
ዕድለኛ ሆኜ በህፃንነት እድሜዬ መስቀል አደባባይ(አብዮት_ኤግዚቢሽን ማዕከል) አዳራሽ ውስጥ በተከናወነ ኮንሰርት 30ብር ተከፍሎልኝ ቴዎድሮስ ካሳሁንን በቅርበት ለማየት መድረኩ ላይ ለመውጣትም እድሉን አግኝቼ ነበር ምንም እንኳ ቴዲ አፍሮ "ግርማዊነቶ" እያለ ሲያንጎራጉር ጆኒ ራጋ በመሀል እየዘለለ "እናትን ልብ**" ሲል ደንግጬ ሮጬ ብወጣም 🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂😀
እድሜ ይስጠን እንጂ ብላቴናው በአለም መድረክ ላይ ሳንጃውን ይዞ እንደሚሸልል እናምናለን፡፡ ኢትዮጵያ ከፍ ከፍ ትላለች ፡፡
ከሁሉ ከሁሉ ግን ንግስቲቱ እጅግአየሁ ሽባባው እና ንጉሱ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮን) በአንድ መድረክ ላይ የምናይበት ቀን ይመጣ ዘንድ እመኛለሁ፡፡ 💚💛❤️ 
መቼም ያገኛት ቀን ጎንበስ ብሎ ምን እንደሚያበረክትላት ሳስብ ለመገመት እቸገራለሁ ፡፡ ያዜምላት ይሆን? ወይስ ለገጣሚ ይልማ ገብረዓብ የወርቅ ብዕር እንደሰጠው ሁሉ ለሷም የወርቅ ድምፅ ማጉያ ይሰጣታል? እንጃ ብቻ 
አመክኖኒዮኣዊ ፋይዳውስ ምን ሊሆን ይችላል?መልሱ ቀላል ነው። በሌላ በኩል ብላቴናውን በጭፍን ሣይሆን በምክንያት የምንወድ እኛ፣ ምክንያታችን ምን እንደሆነ አንዴ ሳይሆን በተደጋጋሚ በአስረጅ ገልፀናል።የብላቴናውን ስራ መውደድ በዚህ ሰዓት ጥበብን የመውደድ ያለመውደድ ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ እንዲህ የምንለው ደግሞ ስራውን የምንመዝንበት ሚዛን ሲንሻፈፍ ስለምንመለከት ነው። ዘፈኖቹ(መዝሙሮቹ)እንከን የለሽ መሆናቸውን ብናውቅ እንኳን እውነታውን ለመደበቅ ጥረት ስናደርግ እንስተዋላለን።
በጥበብ ሚዛን ከተመዘኑ የብላቴናው ስራዎች ሁሌም ቅድምናውን ይወስዳሉ።ይህንንም እኔ ሣይሆን የሙዚቃ ጠበብት፣የታሪክ ጠበብት በተለያያዬ አጋጣሚ እማኝነታቸውን የሰጡት ሀቅ ነው።ስራውን ከጥበብ ሚዛን በተለዬ ሌላ መመዘኛ ከመዘነው፣ከመሰረቱ መመዘኛችን ሚዛናዊነት ያልጎደለው መሆኑን እርግጠኛ እንሁን።ይህንን ካደረግን ማን ከፊት ተሰላፊ እንደሆነ ያኔ እናያለን። የአድናቂ ድርቅ በበዛበት በዚህ ቀውጢ ሰዓት ድምፁን የምንሰማበትን፣ ዘፈኑ የሚወጣበትን፣ ኮነሠርት የሚያቀርብበትን ዕለት ... ወዘተ...ልክ እንደ ልደታችን ዕለት በጉጉት የምንናፍቅለት ምርጥ የጥበብ ሰው የገርማሞ የልጅ ልጅ አይደለምን?
የጥበብ ስራው ከመውጫው መባቻ ጀምሮ ልክ እንደ ዳቦ(ዳቦ ይሻል ይሆን?) በሠልፍና በግፊያ እንደሸመትነውና እየሸመትነው እንዳለን ሁላችንም እያየነው ያለነው ጉዳይ ነው።
ሰሞኑን ደግሞ ብላቴናው ቴዲ አፍሮ በዓለም መድረክ እየተወደሰ ይገኛል።
አወድሱኝ የማይል፣ስራው ስለ ራሱ እንጅ፤ራሱ ስለ ስራው የማያወራ ጨዋ!!!
ውዳሴ ሲያንሰው ነው።ታላላቅና ተፅዕኖ ፈጣሪ የአለማችን መገናኛ ብዙሃን...እንደ CcTv የመሣሠሉ ሚዲያዎች አድናቆትና ውዳሤ እየቸሩትና ሽፋን እየሰጡት ይገኛል።
አማርኛችንን ቢሰሙ ውዳሴያቸዉን አስቡት!!
የአለማችንን የጥበብ ከዋከብት(stars) ስራ እያወዳደረ ለአሸናፊዎች እውቅና እየሰጠ የሚገኘው(world album bill board) ቴዲ አፍሮን የሰንጠረዡ አናት ላይ የማስቀመጡትስ ምስጢር ምን ይሆን?
ምን አልባት 'የድሮ ስርዓት ናፋቂ' ፣ትምክህተኛ አሊያም ጠባብ የ "bill board" ሰዎች አጋዥነት ይሆን?የፍቅር ሰባኪው መቼም የትም እንዳሸነፈ ይኑርልን።ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከመጨረሻው (ኢትዮጵያ) አልበሙ ድረስ ቴዲ አፍሮ ስለፍቅር ያልሰበከበትን ማግኘት በጣም ያስቸግራል።
ቴዎድሮስ ካሳሁን(የአፄ ቴዎድሮሥ ወይም ካሣ (ምትክ)) ምርጥ ምሳሊያችን ነህ።ክፉ አይንካህ። ፍቅር ያሸንፋልና አንድ ቀን ታሸንፋለህ፤ፍቅርነህና
መሰረቱ ፍቅር 
ሰብዕናው ፍቅር
ሁለንተናው ፍቅር 
ቴዲ አለ የፍቅር ሰው በሀገሬ ሰማይ ስር 
በግጥም ተራቆ በዜማ የሚመሰጥር"
በአቋም ፅናቱ ትውልድ ሲናገር
ዘመን ሲመሰክር!!"
����
... የሀገር ሀብት የሆነን ብላቴና!የሀገርን ትርጉም ጠንቅቆ የተረዳ፣የህዝብ ብሶትና ህመም የሚያንገበግበው፣ በማይቀየር አቋሙ ዘመናትን በሚሻገር የሀሳብ ልዕልናው በድፍረት ብሶታችንን ሲጮህልን የነበረ ፣ የዕምነትን ፅናት፡ የተስፋን ጉልበት፡የፍቅርን ሀይል፡ ከፈጣሪ በተቸረው በጥበብ ልሳኑ ደግሞ ደጋግሞ አዜመልን!አዜመልን!!የሚያአዜመልን!!!...ቴዲ የሀገርን ጥልቅ ፍቅር አዳምጠን በማንሰለቸው ውብ ስራዎቹ ሰብኮናል፡፡ ትናት ላይ ቆሞ በላቀው የአስተሳሰብ አድማሱ ጊዜን ቀድሞ ስለ ዛሬው እውነት ተንቢት ተናግሯል፡፡ 
ማነህማ ዲጄ ጃ ያስተሰርያልን ክፈተው!!!
ጃ!..ያስተሰርያል!!!!
......አዲስ ንጉስ እንጅ ለውጥ መቼ መጣ!!!
...
በጎጥ እና በመንደር ሳይታጠር፣ በስሜት ሳይነዳ፣ በጭብጨባ ሳይኮፈስ፣በነፈሰበት ሳይነፍስ፣ሁሌም በአቋም በመፅናት ሀገርን ከፊት አስቀድሞ ለህዝብ የሚታገል የክፍለ ዘመናችን እውነተኛ የጥበብ "ሰው" ቴዲ እድሜና ጤና ፈጣሪ አብዝቶ ይስጥህ፡፡
ቀሪው የህይወት ዘመንህን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክልህ።
�����
"በአንደበቱ የታገለ፣ የጭቆናን ግዙፍ ቀንበር
በጥበብ ልሳኑ ዛሬ ላይ ቆሞ ነገን የሚናገር
ብላቴናው ንጉስ የጥበብ ዋርካ አድባር
ይወደስ ይሸለም እክሊል ይጫን ይከበር
የክቡር ዶ/ር ቴዲ አፍሮ "ፍቅር ያሸንፋል!" የሚላት የሁልጊዜም አባባሉና የዛሬው የንግግሩ መቋጫ የነበረችውን በርዝመቷ አጭር የሆነችውን በይዘቷ ግን እምቅ የሆነችዋን አረፍተ ነገሩን ነው። በእኔ እይታ "ፍቅር ያሸንፋል" የሚለውን የክቡር ዶ/ር ቴዲ አፍሮ ከታላቁ መፅሐፍ ከመፅሐፍ ቅዱስ የብርሀነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ከሆነው መልእክታት ውስጥ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ 13 ላይ ያለውን መሰረት አድርጌ እግዚአብሔር ባሳወቀኝ መጠን ልገልፀው ወደድኩኝ።

1፤ በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። 
2፤ ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
3፤ ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።((ከ ቁጥር 1-3 ያለው ፍቅር ሳይኖረን ሁሉ ቢኖረን ከንቱ ነን። በሚለው የሚጠቃለል ሀሳብ ነው። ከንቱ ሰው ደግሞ አይደለም ሊያሸንፍ አቻ እንኳን አይወጣም። ሁልጊዜ ተሸናፊ ነው!))
4፤ ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤
5፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤
6፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤
7፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።
8፤ ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም((ከቁጥር 4-8 ያለው ደግሞ የፍቅርን ባህርያት ያብራራሉ። 'ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም' የምትለዋ ቃል አንድም ሁሌ ፀንቶ የሚኖርና የማይሻር ነው፤ አንድም ደግሞ 'ፍቅር ሁልጊዜ አሸናፊ ነው!' እንደማለት ነው።)) ፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።
9፤ ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና፤
10፤ ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል።
11፤ ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ።
12፤ ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።((ከቁጥር 8-12 ያለው ደግሞ ከፍቅር ውጪ ሁሉም የተጠቀሱት ነገሮች እንደሚያልፉና እንደሚሻሩ ይነግረናል።))
13፤ እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።((ቁጥር 13 ደግሞ የፍቅርን የበላይነት ከሌሎች ጥሩ ነገሮች እንኳን አንደኛ እንደሆነ ነው የሚነግረን: "እምነት":- እስከ በዚህ አለም በህይወት እስካለን የሚቆይ ነው። ከዚህ አለም በሞት ስንለይ እንደእምነታችንና እንደ ስራችን ዋጋችንን ስናገኝ ያልፋል። "ተስፋ" ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ቸርነት 'ተስፋ መንግስተ ሰማያት፤ ሰማያዊት ኢየሩሳሌምን' ስናገኝ ከዛ የዘለለ ሌላ ተስፋ አይኖረንም። ምክንያቱም የሰው ልጅ የተፈጠረበት አላማ እግዚአብሔርን ስሙን ለመቀደስ፤ ክብሩንም ለመውረስ ስለሆነ። ስሙን ቀድስን አመስግነን ክብሩን(መንግስተ ሰማያትን) መውረስ የመጨረሻ ተስፋችን ነው። በእርግጥ መንግስተ ሰማያት እንደአለማዊ ኑሮ አይሰለቸንም። ዘወትር ዕለት ዕለት የእግዚአብሔር ጸጋ ስለሚጨመር ይበልጥ ተድላ ደስታ የምናደርግበት የመጨረሻ አላማችን (ultimate goal) የሚባል ለሁላችንም የሚበቃ እግዚአብሔር ያዘጋጀልን ቦታ ነው። ተስፋችን ያበቃል ሲባል አንዴ መንግስተ ሰማያትን ከወረስናት በኋላ ተስፋችን ተሳክቷል። አለቀ ደቀቀ እንደማለት ነው። "ፍቅር" ግን ከተስፋም ይበልጣል። እንዴት ትለኝ እንደሆነ ተስፋ መንግስተ ሰማያትን ወርሰንም ሆነ ፍቅር ለዘለዓለም ትቀጥላለችና። በዚያ የምንኖረው በፍቅር እንጂ እንደዚህች አለም በጥላቻና በክርክር አይደለም። አንድም ያለፍቅር ተስፋ መንግስተ ሰማያት አንወርስም።)) 
#ስለዚህ ፍቅር ያሸንፋል ማለት በእኔ እይታ ለሁልጊዜም ያሸንፋል። ከምንም፣ከማንም፣ከጥሩ ነገር ጋር ቢወዳደር ራሱ ያሸንፋል። እግዚአብሔር ራሱ ታላቁ መፅሐፍ እንደሚለን ፍቅር ነውና! እመቤታችን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ራሷ የፍቅር እናት ነችና! ቅዱሳን መላእክታን፣ ፃድቃን ሰማዕታት የኖሩት በፍቅር ነውና!)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለወላዲቱ ድንግል፤ ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)