ወያኔ_የቤተ_ሣጥናኤል (Church of Satan)አምላኪዎች ናቸው
#ወያኔ_የቤተ_ሣጥናኤል (Church of Satan)አምላኪዎች ናቸው
The end justifies the means.›
በድምሩ ከአምስት ሚሊዮን ሕዝብ የወጡ ‹ጥቂት›የትግሬ ገዢዎች የ110 ሚሊዮን ሕዝብ ዕጣ ፋንታ ይወስናሉብሎ በሰው ልጅ አእምሮ ማሰብ የሚቻል አይደለም ነበር ፡፡ ነገርግን ይሁን ያለው ከመሆን አይዘልምና እየተገረሙ የዓለምን አካሄድ በትዝብት ከመቃኘት በስተቀር ምንም ማድረግ አይቻለንም፡፡ በብሂልህ “ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራልትል የለም? ወደህ ተሰደድህ ? ወደህ ትራባለህ? ወደህ ሀገር አልባ ትሆናለህ? አብዛኞቹ የዓለም ቢሌነሮች
እነማን ናቸው? የዓለምን ትልቅ ሥልጣን በእጅ አዙርና በቀጥታ የተቆጣጠሩት እነማን ናቸው? ወዴት እየነዱህ ነው?
ወደ ጥፋ ወይንስ ወደ ልዕልና? በኢትዮጵያስ ያንን ዓለም አቀፍ ነፀብራቅ ቁልጭ ብሎ እያየኸው አይደለምን? ዘመኑ የጥቂቶች ነው ወዳጄ ልቤ፡፡ ሁሉን ቢያወሩት ሆድ ባዶይቀራል፡፡እንደውነቱ ውሸት የሚናገር ሰው በሥቃይ ውስጥ ያለ ነው፡፡ እውነትን የሚናገር ሰው ግን በሥቃይ ውስጥ ላለመኖር የቆረጠ ሰው ነው፡፡ እውነትን በመናገር ብዙ ነገር እናጣለን፡፡ከቅርብ ጓደኛና ዘመድ ጀምሮ የምናጣው ብዙ ነገር ነው –
በዓለማዊ አስተሳሰ መብል፣መጠጥ፣ ድሎት፣ሥልጣን፣ፍቅረኛንና የትዳር አጣማሪን ሳይቀር ብዙ ነገሮችን ልናጣ እንችላለን፡፡ ሀሰት መታወቂያዋ በሆነ ዓለም ውስጥ ስንኖር እውነትን ለመናገር
ከቆረጥን እንደዕብድ ልንቆጠርና በውግዘት ከአካባቢናዐከማኅበረሰብም ጭምር ልንገለል እንችላለን – ያኔ ሃይማኖት፣ባህል ወግና ልማድ የተባለው ይበልጡን በውሸት የተቃኘው ማኅበራዊ ሥርዓት ሁሉ ይከዳህና ከሕገ ወጦቹ ጋር ሲወግንብህ መግቢያ ቀዳዳ ታጣለህ – ደግሞም ያኔ የምትኖርባት ዓለም የሀሰት እንጂ የእውነት መገለጫዐእንዳልሆነች ትረዳና አንድም ታብዳለህ አንድም ትመንናለህ አለዚያም በ‹ኩኑ ከማሆሙ› ሥጋዊ መርህ የቆሻሻው ዓለም ባልደረባ ሆነህ አንተም በተራህ እንዳሻህ ትመላለስበታለህ፡፡እከክ የሰጠ ጥፍር አይነሳምና ምርጫዎች አሉህ፡፡
ለሚያምኑበት እውነት መርዝን በድፍረት የጨለጡና የድንጋይ ውርጅብኝ በውዱ ገላቸው ያስተናገዱ እንዲሁም በስቅላት
ያሸለቡ ሞልተዋል – ዕ
ንቁን የላይና የታች ልጅ ክርስቶስን
ጨምሮ፡፡ በጥቃቅን የሃሳብ ልዩነት – ለምሳሌ በመሬት ቅርጽ– ሳይቀር በሞት የተቀጡ አሉ አሁንም ለቆሙለት እውነት
ሲሉ፡፡ ካለመስዋዕትነት ድል እንደሌለ ተገንዘበን በእውነት መንገድ ከተጓዝን በመጨረሻው እውነት ራሷ ትክሰናለች –
አለበለዚያ ትከሰናለች፡፡
ሀሰት የሚናገር ሰው እውነት የሌለው ወይም የሚታወቅን እውነት በመናገሩ ምክንያት አንዳች ነገር አጣለሁ ብሎ
የሚያምን ሰው ነው ማለት ይቻላል፡፡ ወያኔዎችና እበላ ባይ ወይም የዓላማ ደጋፊ ጸሐፊያነ ትዕዛዞቻቸው የይሉኝታን ገመድ በጣጥሰው ጥለው ነጭ ውሸቶችን በመክተብ ሥራ ላይ
የተጠመዱበት ምክንያት ካልዋሹ በስተቀር የያዙትን ቦታ እንደሚለቁ ስለሚያውቁ ነው፡፡ የሚይዙት ካርድ ሁሉ
ያሟልጫል፡- ዴሞክራሲ ቢሉ ንዑሳን በመሆናቸውና
ከጥንትም በደምና በአጥንት ተረማምደው በመምጣታቸው
ምናልባትና በዛ ቢባል ከ6 በመቶ የሀገሪቱ ሕዝብ የበለጠ
የሚመርጣቸው እንደሌለ ያውቃሉና በዚያ ድጋፍ በማይገኝበት የዴሞክራሲ መንገድ ሊጓዙ አልፈለጉም –
ይህንንም እውነት ጃዝ ብለው ያሠማሯቸው ወገኖች ያውቃሉ፣ በተጨባጭም አይተውታል፡፡ ጨቋኝም ሆነው እንደቀደምቱ ነገሥታትና ወታደራዊው መንግሥት ጉልበትንና
ዘዴን ተጠቅመው እንዳይቀጥሉ ከዜጎች ብቻ ሳይሆን ከመሬቱና ከዛፍ ቅጠሉ ተጣልተዋልና ያም አላዋጣ ብሏቸው ቀጠቀጣቸው ብሔርን ከብሔር ፣ ቡድንን ከቡድን፣ ሰውን ከሰው፣ባልን
ከሚስት … እያናከሱ ዕድሜንመቀጠሉም ከአሁን በኋላየሚሠራ አይመስልም ትራፊ ወያኔዎች ትጠፋ ፡፡ ያላቸው ብቸኛ አማራጭ በኃይል መረግጥ ነበር አልሆነም በውሸት ወሬ አደንቁሮ የተቻላቸውን ያህል ርቀት መጓዝ ነው፡፡ ስለወያኔዎች የብዙዎቻችን እውነት ይሄው ይመስለኛል፡፡ይህ ዓለምሰገድ አሰፋ በተባለ ግለሰብ የተጻፈ ጥናታዊ
የተባለ መጽሐፍ የአማርኛ ተናጋሪውን ማኅበረሰብ አፈር ድሜ ለማስጋጥና የሰሜኑን ሕዝብ በተለይም የኤርትራንና ትግራይን የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ማኅበረሰብ በታሪክም በሥነ ልቦናም
በሃይማኖትም ያላቸውን ነባር ትስስር አጉልቶ በማውጣት ከሌሎች የኢትዮጵያ ዜጎች ይልቅ እኚህ ወንድሞቻችንና
እህቶቻችን ጥንት የነበራቸውንና አሁን ሊኖራቸው የሚገባውን የበላይነትና ሥልጣኔያዊ ገናናነት ለማሳየት ያደረገው ጥረት ከፍተኛ ነው(በእርሱ ጥናት መሠረት ከድላቸው በኋላ ጥብቅ
የነበረው የግንኙነት ፈትል በመላላቱ ሳቢያ ትግራይ በኢትዮጵያዊነት ስትጸና ከመረብ ማዶ ያለው ግዛት በኤርትራነቱ እንደፀና በፀፀት መሰል ቃና ይገልጻል)፡፡ ቀጣዩን እንይ፡-
Once in the seat of power in Addis Ababa, the ethnic card is being aborted at a fast rate to
such an extent that even the Tigrayan features of the regime are fading almost completely. A
new national army with no ethnic character has been created. Except for the premiership and foreign ministry, all cabinet posts are held by non-Tigrayans. Even key posts such asdefense, judiciary, and police are held by non-
Tigrayans. In other words, the rational political actors led a costly ethnic nationalist war in
Tigray without being ethnic nationalists themselves. For the Tigrayan rational actors,
therefore, Marxism was their raison d’etre and ethnic rationalism their means to an end. And ethnic nationalism was a politics of power.
ተዛማጅ ትርጉም፡- [ሕወሓቶች] አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ ከ1983ዓ.ም በኋላ በትግሉ ዘመን ይጠቀሙበት የነበረው
የጠባብ ብሔርተኝነት የትግል ሥልት በኅብረ ብሔራዊየአንዲት ሀገር ሉዓላዊ ስሜት ወዲያው በፍጥነት በመተካቱ
በመንግሥት መዋቅሩ ውስጥ ‹ለመሆኑ በዚህ መንግሥት ውስጥ ትግሬ ሥልጣን ላይ አለ እንዴ?› እስኪባል ድረስ
የኢትዮጵያ መንግሥት ከትግሬዎች ተፅዕኖ ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጣ (ከ1983ዓ.ም በኋላ!)፡፡ ዘውገኝነት ያልተንፀባረቀበት ብሔራዊ የመከላከያ ጦርም በጎሣ ተዋፅዖ ሣይሆን በብቃት
መለኪያ መሥፈርት መሠረት ተመሠረተ፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትርና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታዎች በስተቀር ሁሉም የካቢኔ ሚኒስትሮች ቦታዎች ትግሬ ባልሆኑ ዜጎች ተያዙ፡፡ [Please feel free to laugh, guys!] ሌላው
ቀርቶ አሸናፊ አማፂ ማንንም አምኖ የማይሰጣቸው የመከላከያ፣ የፍትህና የፖሊስ ዕዞች በሙሉ ትግሬ ያልሆኑ
ዜጎች እንዲይዟቸው ተደረጉ፡፡ በሌላ አባባል ሕወሓቶች በተፈጥሯቸው የሌለባቸውን የጎሠኝነት ወይም የጠባብ
ብሔርተኝነት ባሕርይ እንደጊዜያዊ ሥልት በመጠቀም ትግላቸውን በከፍተኛ መስዋዕትነት ከግብ ካደረሱ በኋላ
ሥልጣኑን ላልታገሉ ዜጎች አስረከቡ(ና እነሱ ባዶኣቸውን ቀሩ
– ሣቅ/ሣቂ ፤ ዛሬና አሁን ያልሣቅን መቼ ልንስቅ ጎበዝ?)፡፡ ስለዚህም ለትግራውያኑ ተጋዳላዮች ለእውነተኛ የትግላቸው ጅማሮ ዋና አመክንዮ ማርክሲዝም ሆኖ እንደመታገያ ሥልት
ግን ጠባብ ብሔርተኝነትን ወይም ዘውገኝነትን ተጠቀሙበት(እንጂ እነሱማ ኧረ ንሽ እቴ! ዘውገኛነት በሉት ጎጠኝነት
አሊያም ነፍጠኝነት ሲያልፉ አይነኳቸውም፡፡) እናም ሕወሓቶች
ጠባብ ብሔርተኝነትን ለሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ የሥልጣን ማረጋገጫነት ተገለገሉበት እንጂ በተፈጥሯዊ ባሕርያቸው ዴሞክራቶች ናቸው፡፡
መንግሥቱ ኃ/ማርያምን በሁለት ውሸቶቹ ዘወትር አስታውሰዋለሁ – “እውን አሁን ደርግ አለ?” አንድ በሉ፤ “እኔ እንኳንስ ሰው ትንኝ አልገደልኩም!” ሁለት በሉ ( በነገራችን ላይ ከደቂቃዎች በፊት ‘Talk to Aljazeera’ ላይ
በእንግድነት የቀረበ ኑር ሚሷሪ የተባለ አንድ ፊሊፒናዊ የቀድሞ አማፂ ቡድን መሪ ጋዜጠኛዋ ‹ራስህ ሰው ገድለህ
ታውቃለህ ወይ?› ብላ ስትጠይቀው ‹እንኳን ሰው ጉንዳንም ገድዬ አላውቅ› ብሎ ሲመልስላት መንግሥቱ ፊቴ ላይ ድቅን አለብኝ – ሰውዬው ውሸታም ነው ለማለት ፈልጌ ግን አይደለም – ስለማላውቀው፡፡) መንግሥቱንና ወያኔን መሰል አምባገነኖች በአደባባይ የሚያደርጉትን ሁሉ ‹ዐይኔን ግምባር
ያ’ርገው› ብለው ሽምጥጥ ማድረግ የባህርይ ስጦታቸው ነው፡ኢትዮጵያ ባላት የተመናመነ ኢኮኖሚ ያስተማረችው
በእናቱ የጭንቅ ቀንም በፈለገችው ጊዜ የደረሰላት ይህ‹ምሁር› የሚለውን እንቶ ፈንቶ ‹እውነት ነው፤ ውሸት ነው›ብሎ መከራከር ጉንጭን ማልፋትና በጊዜም መቀለድ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ‹በሀሰት አትመስክር፤ የባልንጀራህን የጎረቤትህንም ገንዘብና ሚስቱንም አትመኝ፤አትስረቅ፣ጓደኛህን እንደራስህ ውደድ፣ … › ይላል፡፡
በእስልምናም ‹ዋሽ› የሚል ቁርኣናዊ ጥቅስ ይኖራል ብዬ ስለማልገምት ሙስሊም አይሆንም ባይ ነኝ፡፡
በአይሁድ ሃይማኖትም እንዲሁ ውሸትን የሚያበረታታ የታልሙድም ይሁን የታናክ ወይም የቶራ ጥቅስ ይኖራልየሚል ሃሳብ የለኝም ምናልባት በማንኛውም መንገድ በ‹የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው›ም በሉት በ‹The end justifies the means.› የሥጋ ፍላጎቶቻቸውን ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ ከማይሉት የቤተ ሣጥናኤል (Church of Satan)አምላኪዎች ጋር የሚመሳሰል ወይም የሚነባበር መሆን አለበት – ሊያውም ከነሱም መካከል የ‹አትድረሱብን አንደርስባችሁም› ዓይነት የመከባበር መርህ የሚከተሉ‹ጨዋዎች› አሉ፡፡ አንድ ኢአማኒ(ኤቲይስት) ጓደኛ አለኝ –እንዲያውም ከአንድ በላይ፡፡ በሞራሉና በማኅበራዊ ግንኙነቱ በጣም ጨዋና ሰውን በቸገረው የሚረዳ ደግ ነው –altruist፡፡ ሃይማኖት የለኝም ብሎ አይዋሽም አይቀጥፍም፡፡ጽድቅና ኩነኔ የሉም ብሎ ማመኑ ልክ እንደዚህ ሰውዬ
ቆርጠህ ቀጥል የሆነ ውሸታም እንዲሆን አላደረገውም፡፡
ልክ እንደ‹ፕሮፌሰር› ክንፈ አብርሃም የትግራዩ ገዢ መደብ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያሳረፈውንና እያሣረፈ ያለውን
የማይፋቅ ጠባሳ በዓይጥ ምሥክር ድንቢጥ የሀሰት ምሥክርነት ጽድቅና ለማሰጠት ነው፡፡ እውነቱን ከፈጣሪ
ቀጥሎ ዓለምና የኢትዮጵያ ሕዝብ እያወቀው ለመዋሸት ይህን ያህል ርቀት መጓዝ ከትዝብት ሌላ እንደማይኖር እነዚህ ሀሰተኛ የዲያብሎስ አሽከሮች ሊረዱት በተገባቸው ነበር፡፡ ግንያሳዝናል ኅሊናቸው በዘረኝነት ልክፍት የታወረ በመሆኑ እውነት ታጥበረብራቸዋለችና የሚሠሩት ህፀፅ ሊታያቸው አልቻለም፡፡ ዛሬ የነጻነት ጎሕ ሲቀድ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻው ሲያፍሩበት በአሳቻ ቦታ ተጥሎ ውሻና እሪያ የሚሸናት አፅማቸው እንደሚታዘባቸው መገንዘብ ነበረባቸው፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ