ልጥፎች

ነገሩ ሁሉ እንደ ጥርስ ነው መሰል እህል ያላመጠበትን የመጀመሪያ ቀን የሚያስታውስ የለም።

ነገሩ ሁሉ እንደ ጥርስ ነው መሰል እህል ያላመጠበትን የመጀመሪያ ቀን የሚያስታውስ የለም። ለነገሩ እህል ከማላመጣችን በፊት የፈረደባትን የ'ናታችንን ጡት ነክሰናል.. በሁለት የፊት ጥርስ እና ድድ የጡት ጫፍን ቅርጭው ይዘን.. ሁሉም እናቶች እሰይ ልጄ ጥርስ አበቀለች ብለው እንዳልተደሰቱ በምስራቻቸው ተነክሰዋል... ያውም እስከሚደሙ **************************************** ይህ የራሴ ያገለገለኝ ንብረቴ ፡ ለሆነ አመት አፌ ሲከፈት ነጫጭ ሆኖ ተደርድሮ፡ ግጥም ብሎ አፌን ሞልቶ የልጅነት ቆንጆ ሳቅ አልፈጠረልኝም? ቆሎ ... ከቆሎም ሳይንገረገብ በደረቁ ጣ ጣ ጣ እያለ የተቆላ ሽንብራ አልከካሁበትም? መለልታ ከአንጓ ሳለይ ሸንኮራ አልመጠጥኩበትም? ይባስ ብዬ ተደብቄ እየሰረኩ ስኳር ቅሜ እየቆረጫጨምኩበት ይህ ጥርሴ እስኪቦረቦር ድረስ አንጀቴን በወለላ ጣዕም አላራስኩበትም? ይህ የልጅነት ጥርሴ ለምን ከእኔ ኖሮ ፡ ከእኔ እንዳልተፈጠረ በአመታት ውስጥ ነቅነቅ አለ? ለምን መነቃነቁ አሰጋኝ? ለምን ... ለምን ያ ቆሎም ቆንጥሮ ያቀበለ፡ ሸንኮራም ሸንሽኖ ያጎረሰ የገንዛ እጄ፡ የእጄ ጣቶች ከድዴ የተሰካን ጥርስ አነቃንቆ ለመንቀል ታገለ? እኔ በ እኔ አልተጣላንም? ያውም በልጅነቴ? ብተወዉ በስብሶ በሽታ፡ ብነቅለው - ክብር አሳጥቼ - ከቤቴም ደጃፍ አፈር ምሼ ሳልቀብረው፡ ደብቄ በትንሽ ብልቃጥ ሳላስቀምጠው... ይባስ ብዬ ወደ ጣርያ፡ ያውም አሻግሬ ለወፍ እና ለአይጥ ዘምሬ 'ያንቺን ለኔ የኔን ላንቺ' እያልኩ መወርወሬ.. ተሻግሮ ወይ በእኛ ቤት፡ ወይ በእነ አሹ ቤት ጣሪያ ቋ ብሎ መውደቁን፡ መጣሉን ሲያረጋግጥልኝ፡ አልያም አጥር ዘሎ በጎረቤት ተክል ወድቆ ፀ...ጥ። በመዳፌ አስቀምጬ ቢያሻኝ በሰው መሀል ጮክ ብዬ፡ ወይ በኔና በጥ

ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? “

ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? “ የጋራ አብሮነት ውጤት ነው!” በምን ይገለፃል? “በአደዋ!”  “ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው?  “ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? በምን ይገለፃል?”  ኢትዮጵያዊነት ዜግነት ነው፡፡ ዜግነት ደግሞ በአንድ የተወሰነ ሀገር ውስጥ የጋራ አብሮነትን የሚያሳይ ነው፡፡ አንድ ጆሴ ኦርቴጋ የሚባል ፖርቹጋላዊ ፀሐፊ አለ፡፡ ይህ ጸሐፊ፤ ሀገር የሚመሰረተው በምን ላይ ነው? ሲል ይጠይቃል፡፡ ሀገር የሚመሰረተው በእሱ አተያይ፣ በጋራ አብሮነት (common future) ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነትም የጋራ አብሮነት ውጤት ነው፡፡ የጋራ መሰረት ያለን፣ የጋራ ጉዳይ ያለን፣ ለወደፊትም የጋራ እድል ያለን ሰዎች ነን፤ በኢትዮጵያዊነት ስር ነው የተሰባሰብነው፡፡፡ ይሄ ማለት ዛሬ እና ትናንት ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ነገና ለወደፊትም አብሮ ለመኖር የጋራ ስምምነት ያለን ህዝቦች ነን፡፡  የአሁኗ ኢትዮጵያ እንዴት ተመሰረተች? የሚል ጥያቄ ከተነሳ ደግሞ የአሁኗ የቆመችው በአፄ ምኒልክ ዘመን ነው፡፡ አሁን ላይ ላለው የአንድነት ክፍፍልና የእርስ በእርስ መጠላለፍ መሰረት የሆነውም ያንን የኢትዮጵያ አመሰራረት የምንረዳበት መንገድ ለየቅል መሆኑ ነው፡፡ ግማሹ በቅኝ ግዛት (ወረራ) አይነት የተፈጠረች ነች ይላል፤ ግማሹ ደግሞ ቀድሞ የነበረችውና ኋላ ላይ በታሪክ አጋጣሚ የተበታተነች ኢትዮጵያን መልሶ አንድነቷን ማስጠበቅ ነው ይላል። በዚህ መሃል ግን የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች፣ ወደ ምስራቅ አፍሪካ መስፋፋት ሲጀምሩ፣ በወቅቱ ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ትግሬ በተባሉት አምስት ግዛቶች ላይ ብቻ ተወስና የቆየችው ኢትዮጵያ፣ ሀገራዊ ኃይልና አንድነት ለማጠናከር፣ ወደ ደቡብ፣ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫ መስፋፋት ጀመረች፡፡  አፄ ምኒልክ፤ በሉአላዊነት ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመመከት፣ ሁሉም በጋ

ጥናትና ፅናት የእድገት እርሾ ነው!

ጥናትና ፅናት የእድገት እርሾ ነው! ከዕለታት አንድ ቀን፣ አንድ ለምድር ለሰማይ የከበደ የንጉሥ ልጅ፣ ያማረ ሠረገላውን አሳጥቦ፣ አስወልውሎ  ታጭታልሃለች የተባለችውን ቆንጆ ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያይ፤ አሽከር አስከትሎ ወደ ሩቅ  አገር ሊሄድ ተነሳ። አባቱ የተከበሩ አንቱ የተባሉ ስመ-ጥር ጀግና፣ ከትውልድ ትውልድ ከሚከታተለው ሥርወ-መንግስት የመነጩ፣ የተከበሩ ሰው ናቸው። ልዑሉም ሊሰናበታቸው ወደ ዙፋናቸው ቀረበና፤ ልዑሉ- “ንጉሥ ሆይ! እንግዲህ ወደ ሩቅ አገር መጓዜ ነውና ፈቃድ ይሰጠኝ?” ንጉሡም- “ወደ የት ልትሄድ ተነሳህ?” ልዑል- “ወደ ሩቅ አገር ነው የምሄደው።” ንጉሥ- “እሺ መሄዱንስ ሄድክ፣ ምን ልታደርግ ነው የምትሄደው?” ልዑሉ “ንጉሥ ሆይ! ታጭታልሃለች የተባልኳትን ቆንጆ ልዕልት፣ ቁንጅናዋንና ሰብዕናዋን ሳላይና ሳላውቅ ላገባ አልሻምና ሄጄ ማረጋገጥ ይኖርብኛል”። ንጉሥ- “እኛ ለልጃችን ክፉና የማይሆን ነገር እንመኛለን?” ልዑል- “አይደለም ንጉሥ ሆይ! የእናንተን ደግነት ከቶም ተጠራጥሬ አላውቅም። ሆኖም በእናንተ ውሳኔ ላይ የእኔም አስተያየት ቢታከልበት፣ ነገሩን ያጠነክረዋል እንጂ አያላላውም! ዞሮ ዞሮ ከእናንተ ፍቃድ አልወጣም።” ንጉሥ- “ደህና፣ ሂድ። ለማንኛውም አንድ አሽከር በቅሎ ይዞ ይከተልህ። ደህና ግባ።” ልዑሉ ምስጋና አቅርቦ የተመደበለትን አሽከር ይዞ መንገዱን ቀጠለ። ከከተማው ወጣ እንዳሉ አንድ መንገደኛ ያገኛሉ፤  መንገደኛውም - “እባክህ ጌታዬ አፈናጠኝና ጥቂት መንገድ አብረን እንግፋ” አለው። ልዑሉም ደግ ሰው ነበርና፤ “ና ውጣ” አለው። አሽከርየው ግን፣ “እኔ ይህ ሰው ከእርስዎ ጋር መሄዱ ቅር ብሎኛል። ደረጃው አይፈቅድም “ አለው። ልዑሉም- “ግዴለም። ይሄ ሰውና እኔ በሰውነታችን አንድ ነን። ምናልባትም የጊዜና የቦታ ጉዳ

#አንተ_ሞኝ

#አንተ_ሞኝ ! Knowing the self (ራስን ማወቅ) እንደ ሳትራ እምነት፣ ሁሉም ግለሰብ ራሱን ለመሆን የራስ ንቃተ ህሊና አለው፡፡ እንደርሱ ሀሳብ ሰዎች አስፈላጊ የሚባል ተፈጥሮ የላቸውም፤ ይልቁንም “ንቃተ ህሊና” እና “የራስ ንቃተ ህሊና” ነው ያላቸው፡፡ እነዚህም ሊለዋወጡ የሚችሉ ናቸው ይላል፡፡ አንድ ሰው በማህበረሰቡ ውስጥ ያለው ቦታ እኔን ይገልጻል ብሎ ካሰበ ወይም ማንነቴን መቀየር አልችልም ብሎ ካለ፣ ራሱን እየሸነገለ አልያም እየዋሸ ነው፡፡ ለሌላኛው ሰው “ያ ማለት እኔ ነኝ” ብሎ መንገርም ራስን ማሳት ነው፡፡ እንደ ሳትራ እሳቤ “self-actualization” ለራስ ያለ ነፃ ዕውቀት ሂደት ሲሆን፣ አንድ ነገር ሌላ አንድ ሰው ከተሰራበት እሳቤ ተነስቶ መበየን ሁልጊዜም የሚቻል ነው፡፡ ይህን ለማድረግ አንድ ሰው ሳትራ “facticity” እያለ የሚጠራውን እውነት መገንዘብ ግድ ይሆንበታል፡፡ ይህም ማለት እውነታ ላይ የተመሠረቱ ሀቆችን መረዳት ሲሆን፣ ከግለሰቡ ውስጠት ውጭ ሆነው በእርሱ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳርፉ ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም አንድ ሰው በነፃነት የቆመ ንቃት እና ከማህበረሰቡ የተገነጠለ ንቃት እንዳለው ሊያውቅ ይገባል። (ለምሳሌ ማህበረሰቡ በለካህ ልክ አንተን ‘ሞኝ’ ብሎ ሊገልጽህ ይችላል። ሆኖም ሞኝ የመሆንም፣ ያለመሆንም ምርጫው ባንተ እጅ ላይ ነው) እንደ ሳትራ እምነት እውነተኛውና ብቸኛው ምልከታ አንድ ግለሰብ ለራሱ ንቃተ ህሊና ተጠያቂ መሆኑን ማወቅ እና ለራስ ያለ ንቃተ ህሊና ከልከኛው ንቃተ ህሊና ተመሳስሎሽ እንደሌለውም መረዳት ያስፈልጋል ባይ ነው፡፡ ሳትራ ሁለት አይነት “መሆን” አለ ይላል፡፡ (Being in itself እና Being for itself)፡፡ • Ensoi (being in itself) በራስ መሆን፡- ነገሮች እውን ሲ

የዘመኑ_እርግማን

የዘመኑ_እርግማን #ጭንቅላትህን_አጽዳ መጽሐፍ ብዙ አማራጮች የተሻለ ነገር እንድታገኝ ሊያደርጉህ ይችላል፤ ግን እመነኝ ደስተኛ አያደርጉህም። ወደ አንድ ሱፐር ማርኬት ልውሰድህ፤ ተከተለኝ። በ Food Marketing Institute በ2014 በተደረገ ጥናት መሰረት፣ በአንድ መካከለኛ ሱፐር ማርኬት ውስጥ 42,214 ሸቀጦች ይገኛሉ። እንደ ድሮው በአስር ደቂቃ ውስጥ የምታነሳውን አንስተህ የምትወጣበት ሁኔታ ላይ አይደለህም። ከአንደኛው እርጎ ሌላኛውን እና የተሻለ የምትለውን እርጎ ታማርጣለህ፣ ወይም የቅባት መጠኑ አነስተኛ የሆነውን የዘይት አይነት ፍለጋ ትዳክራለህ። እስኪ አንድ ጅንስ ሱሪ ለመግዛት አስብ፤ ገበያውን ታካልለዋለህ። ፓትሌቱ አጭር ፓትሌቱ ረዥም፤ ፋሽን ያለፈበት ያላለፈበት፤ ጥቁር ከጥቁር መለስ ያለ፤ ጠባብ ሰፊ፤ ባለዚፕ፣ ባለ ቁልፍ፤ ስትረች የሚያደርግ የማያደርግ። አንድ ጅንስ ለመምረጥ ሰዓታትን ታሳልፋለህ። ልብስ የማይመርጡ ሰዎች እነማን እንደሆኑ ታውቃለህ? ስቲቭ ጆፕስ፣ ማርክ ዙከርበርግ እና ኦባማን ጨምሮ ልብስ አይመርጡም። ልብስ ለመምረጥ ጭንቅላታቸውን ማጣበብ እና ጭንቀት ውስጥ መግባት አይፈልጉም። የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ኦባማ፤ እንዲህ ይለናል - “እንደምታየው ግራጫ ወይም ሰማያዊ ሱፎችን ብቻ ነው የምለብሰው።” አለኝ ኦባማ ፈገግታን እንደተላበሰ፤ “በተቻለኝ አቅም የአማራጮቼን ቁጥር ለመቀነስ እሞክራለሁ። ምን እንደምለብስ እና ምን አይነት ምግብ እንደምመገብ መወሰን አልፈልግም። ሌላ ብዙ የእኔን ውሳኔ የሚጠብቁ ጉዳዮች አሉኝ” በአንተም አኗኗር ውስጥ ብዙ ምርጫዎች ይኖራሉ፤ የትኛው መቅደም … የትኛው መቅረት እንዳለበት ለመመርጥ እስክትቸገር ድረስ ግራ ትጋባለህ… እናም ከምርጫዎች ውዥንብር እንዴት ነጻ መሆን ይቻላል? #ጭንቅላትህን_አጽዳ

የውሳኔ_ስሌት

የውሳኔ_ስሌት ! አንድን ውሳኔ በመወሰንና ባለመወሰን መካከል ስትዋዥቁ በአእምሯችሁ ብቅ ጥልቅ የሚሉ ሁለት ሃሳቦች አሉ፡፡ በአንድ በኩል ውሳኔው ትክክል ቢሆን የምታገኙት ጥቅም ሲሆን፣ በሌላ ጎኑ ግን ውሳኔው ስህተት ቢሆን የሚያስከትለው ችግር ነው፡፡ በተለይ እንድትወላውሉ የሚያደርጋችሁ ስሜት ሊያጋጥማችሁ የሚችለውን ችግር ስታስቡ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ከአንዳንድ ውሳኔዎች በኋላ ምንም ጥቅም ባናገኝም እንኳን ሊደርስብን ከሚችል ችግርና ክስረት ተጠብቀን በዜሮ መገላገል የሚመረጥበት ጊዜ እንዳለ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ ውሳኔያችሁን ከምታገኙት ጥቅም ብቻ አንጻር ማሰብ በአጓጉል ጉጉት እንድትንደረደሩ ያደርጋችሁና ከሚዛናዊነት ሊጋርዳችሁ ስለሚችል ጥቅማችሁን በሚገባ ካሰላችሁ በኋላ ውሳኔያችሁን ለመገምገም መነሳት ያለባችሁ ሊያስከትል ከሚችለው ችግር ወይም መዘዝ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመወሰን የሚረዷችሁን ሶስት ወሳኝ ነጥቦች አስፍሬላችኋለሁ፡- 1. የምትወስኑት ውሳኔ ትክክል ካልሆነ የሚያደርስባቸችሁ ጉዳት ከምክንያታዊነትና ከተጨባጭ ሁኔታ አንጻር እውን ከሆነ … 2. የሚደርስባችሁ ጉዳት ከአካል ጤንነት፣ ከስነ-ልቦና ቀውስ፣ ከከባድ የገንዘብ ክስረትና ከመሳሰሉት ከባባድ ሁኔታዎች ጋር የሚገናኝ ከሆነ … 3. በተሳሳተው ውሳያኔችሁ ምክንያት ከሚደረስባቸሁ ችግርና መዘዝ ለመውጣት ቢያንስ አንድ አመትና ከዚያ በላይ የሚፈጅባችሁ ከሆነና ከአመታት መባከንና ከእድሜ መበላት ጋር የሚገናኝ ከሆነ፡፡ ካለይ በተዘነዘሩትን የስሌት ሃሳቦች አንጻር ውሳኔያችሁ ተመዝኖ ሚዛን ካልደፋ ስለውሳኔያችሁ በሚገባ እንድታስቡበትና ብትችሉ ከእናንተ ከቀደሙ ብሱል ሰዎች ምክርን እንድትቀበሉ ልምከራችሁ:: ዶ/ር ኢዮብ ማሞ

Background Information on Ethiopia

ምስል
Background Information on Ethiopia Ethiopia has many diverse topographical, climatic, linguistic, and religious  features. Geographically, Ethiopia is located within the hot zone. Its southern tip is only  30 degrees north of the equator. However, due to its high altitude, the country has a  predominantly moderate climate with an average temperature in its vast central highland  plateaus no more than 20°C (68°F). The Great East African Rift Valley traverses the  central highland plateau into the north-west and south-east highlands. The majority of  the population lives in scattered villages in the highlands as farmers and pastoralists. The  three popular indigenous foodstuff plants, teff (Eragrostis teff), nug (Guizotia  abyssinica), and enset (Edulis edule) have been cultivated since at least the 5th  millennium BC (Pankhurst, 2005, p. 13).The highlands are surrounded by lowlands, the  largest part of which lies on the south-eastern side adjacent to Somalia. The Ethiopian  Rift Valley