#አንተ_ሞኝ

#አንተ_ሞኝ!
Knowing the self (ራስን ማወቅ)
እንደ ሳትራ እምነት፣ ሁሉም ግለሰብ ራሱን ለመሆን የራስ ንቃተ ህሊና አለው፡፡ እንደርሱ ሀሳብ ሰዎች አስፈላጊ የሚባል ተፈጥሮ የላቸውም፤ ይልቁንም “ንቃተ ህሊና” እና “የራስ ንቃተ ህሊና” ነው ያላቸው፡፡
እነዚህም ሊለዋወጡ የሚችሉ ናቸው ይላል፡፡ አንድ ሰው በማህበረሰቡ ውስጥ ያለው ቦታ እኔን ይገልጻል ብሎ ካሰበ ወይም ማንነቴን መቀየር አልችልም ብሎ ካለ፣ ራሱን እየሸነገለ አልያም እየዋሸ ነው፡፡ ለሌላኛው ሰው “ያ ማለት እኔ ነኝ” ብሎ መንገርም ራስን ማሳት ነው፡፡
እንደ ሳትራ እሳቤ “self-actualization” ለራስ ያለ ነፃ ዕውቀት ሂደት ሲሆን፣ አንድ ነገር ሌላ አንድ ሰው ከተሰራበት እሳቤ ተነስቶ መበየን ሁልጊዜም የሚቻል ነው፡፡ ይህን ለማድረግ አንድ ሰው ሳትራ “facticity” እያለ የሚጠራውን እውነት መገንዘብ ግድ ይሆንበታል፡፡ ይህም ማለት እውነታ ላይ የተመሠረቱ ሀቆችን መረዳት ሲሆን፣ ከግለሰቡ ውስጠት ውጭ ሆነው በእርሱ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳርፉ ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም አንድ ሰው በነፃነት የቆመ ንቃት እና ከማህበረሰቡ የተገነጠለ ንቃት እንዳለው ሊያውቅ ይገባል። (ለምሳሌ ማህበረሰቡ በለካህ ልክ አንተን ‘ሞኝ’ ብሎ ሊገልጽህ ይችላል። ሆኖም ሞኝ የመሆንም፣ ያለመሆንም ምርጫው ባንተ እጅ ላይ ነው)
እንደ ሳትራ እምነት እውነተኛውና ብቸኛው ምልከታ አንድ ግለሰብ ለራሱ ንቃተ ህሊና ተጠያቂ መሆኑን ማወቅ እና ለራስ ያለ ንቃተ ህሊና ከልከኛው ንቃተ ህሊና ተመሳስሎሽ እንደሌለውም መረዳት ያስፈልጋል ባይ ነው፡፡
ሳትራ ሁለት አይነት “መሆን” አለ ይላል፡፡ (Being in itself እና Being for itself)፡፡
• Ensoi (being in itself) በራስ መሆን፡- ነገሮች እውን ሲሆኑ የሚተረጎሙና ምሉዕ ናቸው፤ ሆኖም ስለራሳቸው ምሉዕ ጣዕምና ምልከታ ፈፅሞ አያውቁም፡፡ ለምሳሌ ድንጋዮች፣ አእዋፍ እና ዛፎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
• Paur sai (being for itself) እነዚህ ሊፈረጁና ሊተረጎሙ፣ በሃቅ ሊታወቁ የሚችሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ንቃተ ህሊናና ህላዊነትን ያውቃሉ (ሰዎችን መጥቀስ ይቻላል)

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ)