የዘመኑ_እርግማን

የዘመኑ_እርግማን
#ጭንቅላትህን_አጽዳ መጽሐፍ
ብዙ አማራጮች የተሻለ ነገር እንድታገኝ ሊያደርጉህ ይችላል፤ ግን እመነኝ ደስተኛ አያደርጉህም።
ወደ አንድ ሱፐር ማርኬት ልውሰድህ፤ ተከተለኝ። በ Food Marketing Institute በ2014 በተደረገ ጥናት መሰረት፣ በአንድ መካከለኛ ሱፐር ማርኬት ውስጥ 42,214 ሸቀጦች ይገኛሉ። እንደ ድሮው በአስር ደቂቃ ውስጥ የምታነሳውን አንስተህ የምትወጣበት ሁኔታ ላይ አይደለህም። ከአንደኛው እርጎ ሌላኛውን እና የተሻለ የምትለውን እርጎ ታማርጣለህ፣ ወይም የቅባት መጠኑ አነስተኛ የሆነውን የዘይት አይነት ፍለጋ ትዳክራለህ።
እስኪ አንድ ጅንስ ሱሪ ለመግዛት አስብ፤ ገበያውን ታካልለዋለህ። ፓትሌቱ አጭር ፓትሌቱ ረዥም፤ ፋሽን ያለፈበት ያላለፈበት፤ ጥቁር ከጥቁር መለስ ያለ፤ ጠባብ ሰፊ፤ ባለዚፕ፣ ባለ ቁልፍ፤ ስትረች የሚያደርግ የማያደርግ። አንድ ጅንስ ለመምረጥ ሰዓታትን ታሳልፋለህ።
ልብስ የማይመርጡ ሰዎች እነማን እንደሆኑ ታውቃለህ?
ስቲቭ ጆፕስ፣ ማርክ ዙከርበርግ እና ኦባማን ጨምሮ ልብስ አይመርጡም። ልብስ ለመምረጥ ጭንቅላታቸውን ማጣበብ እና ጭንቀት ውስጥ መግባት አይፈልጉም። የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ኦባማ፤ እንዲህ ይለናል -
“እንደምታየው ግራጫ ወይም ሰማያዊ ሱፎችን ብቻ ነው የምለብሰው።” አለኝ ኦባማ ፈገግታን እንደተላበሰ፤ “በተቻለኝ አቅም የአማራጮቼን ቁጥር ለመቀነስ እሞክራለሁ። ምን እንደምለብስ እና ምን አይነት ምግብ እንደምመገብ መወሰን አልፈልግም። ሌላ ብዙ የእኔን ውሳኔ የሚጠብቁ ጉዳዮች አሉኝ”
በአንተም አኗኗር ውስጥ ብዙ ምርጫዎች ይኖራሉ፤ የትኛው መቅደም … የትኛው መቅረት እንዳለበት ለመመርጥ እስክትቸገር ድረስ ግራ ትጋባለህ… እናም ከምርጫዎች ውዥንብር እንዴት ነጻ መሆን ይቻላል?
#ጭንቅላትህን_አጽዳ መጽሐፍ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)