ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? “

ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? “የጋራ አብሮነት ውጤት ነው!” በምን ይገለፃል? “በአደዋ!”  “ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? 
“ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? በምን ይገለፃል?” 
ኢትዮጵያዊነት ዜግነት ነው፡፡ ዜግነት ደግሞ በአንድ የተወሰነ ሀገር ውስጥ የጋራ አብሮነትን የሚያሳይ ነው፡፡ አንድ ጆሴ ኦርቴጋ የሚባል ፖርቹጋላዊ ፀሐፊ አለ፡፡ ይህ ጸሐፊ፤ ሀገር የሚመሰረተው በምን ላይ ነው? ሲል ይጠይቃል፡፡ ሀገር የሚመሰረተው በእሱ አተያይ፣ በጋራ አብሮነት (common future) ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነትም የጋራ አብሮነት ውጤት ነው፡፡ የጋራ መሰረት ያለን፣ የጋራ ጉዳይ ያለን፣ ለወደፊትም የጋራ እድል ያለን ሰዎች ነን፤ በኢትዮጵያዊነት ስር ነው የተሰባሰብነው፡፡፡ ይሄ ማለት ዛሬ እና ትናንት ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ነገና ለወደፊትም አብሮ ለመኖር የጋራ ስምምነት ያለን ህዝቦች ነን፡፡ 

የአሁኗ ኢትዮጵያ እንዴት ተመሰረተች? የሚል ጥያቄ ከተነሳ ደግሞ የአሁኗ የቆመችው በአፄ ምኒልክ ዘመን ነው፡፡ አሁን ላይ ላለው የአንድነት ክፍፍልና የእርስ በእርስ መጠላለፍ መሰረት የሆነውም ያንን የኢትዮጵያ አመሰራረት የምንረዳበት መንገድ ለየቅል መሆኑ ነው፡፡ ግማሹ በቅኝ ግዛት (ወረራ) አይነት የተፈጠረች ነች ይላል፤ ግማሹ ደግሞ ቀድሞ የነበረችውና ኋላ ላይ በታሪክ አጋጣሚ የተበታተነች ኢትዮጵያን መልሶ አንድነቷን ማስጠበቅ ነው ይላል። በዚህ መሃል ግን የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች፣ ወደ ምስራቅ አፍሪካ መስፋፋት ሲጀምሩ፣ በወቅቱ ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ትግሬ በተባሉት አምስት ግዛቶች ላይ ብቻ ተወስና የቆየችው ኢትዮጵያ፣ ሀገራዊ ኃይልና አንድነት ለማጠናከር፣ ወደ ደቡብ፣ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫ መስፋፋት ጀመረች፡፡ 
አፄ ምኒልክ፤ በሉአላዊነት ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመመከት፣ ሁሉም በጋራ መቆም አለባቸው ከሚል መነሻ ነው መስፋፋትን ያደረጉት፡፡ በዚህ መሃል ግጭት ተፈጥሮ የብዙ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል፡፡ ይሄ ክስተት ነው፡፡ ዛሬ አንድ ሆኖ የሚታየው አብዛኛው ሀገር፣ አሁን ላይ የያዘው ቅርፅ በእንዲህ አይነት ክስተቶች አልፎ የመጣ ነው፡፡ የዚህ አይነት የማሰባሰብ ውጤት የታየው በአድዋ ጦርነት ላይ ነው፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በግልፅ ለአንዲት የጋራ ሉአላዊ ሀገር ተዋድቀዋል፡፡ ስለዚህ አድዋ የኢትዮጵያዊነት ታሪክ ነው፡፡ አድዋ ላይ የምናየው ኢትዮጵያዊነትን ነው፡፡ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች፣ በጋራ የሉአላዊነት አደጋን የቀለበሱበትና አብሮነታቸውን ያጠናከሩበት፣ ወደፊትም በነፃነት ለመኖር የተስማሙበትና መስዋዕትነት የከፈሉበት፣ ሁሉም ለወደፊት አብሮነታቸው አሻራቸውን ያሳረፉበት ነው አድዋ ማለት፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዊነት ለኔ አድዋ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊነት ማለት በአብሮነት፣የወደፊት ነፃነትን አስከብሮ፣ በጋራ ለማደግ የመስማማት ውጤት ነው፡፡ በዚህ መንፈስ ነው ነፃነታችንን አስከብረን ዛሬ ላይ የደረስነው፡፡ ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ቅኝ ግዛት ውስጥ የወደቁበት ሚስጥሩ፣ ይሄን አብሮነት ማጣታቸው ነው፡፡ ስለዚህ ለኔ ኢትዮጵያዊነት ማለት በወደፊት አብሮነት ላይ የተመሰረተ አንድነት ነው፡፡ በኢትዮጵያዊነት ነው ከቅኝ ግዛት ነፃ የሆንነውና ራሳችንን አስከብረን የኖርነው፡፡ 

የኢትዮጵያ አንድነትን ለማምጣት ብዙ ዋጋ ተከፍሏል፡፡ ብዙ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል፡፡ ይሄ ግን እኛ ብቻ ሳንሆን  ሰልጥነዋል የተባሉ ሀገሮችም የዛሬ አንድነታቸውን ያገኙት፣ በእንዲህ ያለውና ከዚህም በከፋ ሂደት ነው፡፡ አኖሌ ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ፣ የኢትዮጵያ አንድነት በሚመሰረትበት ሂደት ውስጥ የተፈጠረ ነው፡፡ አኖሌ ላይ ወገኖቻቸው የተጨፈጨፉባቸው ሰዎች ናቸው፣ አድዋ ላይ ለጋራ ነፃነት የተዋጉት፡፡ አድዋን ያለ ኦሮሞ ብሔር ተሳትፎ ማሰብ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም አብዛኛው የአፄ ምኒልክ ወታደር ኦሮሞ ነው፡፡ 

አሁን የሚንጸባረቀው  የመበደል ስሜትና የብሔርተኝነት ስሜትም ሂደት የፈጠረው ነው። በየትኛውም ተመሳሳይ የታሪክ አጋጣሚ ውስጥ ባለፈ ሀገር ይሄ ይፈጠራል፡፡ ለምሳሌ ፈረንሳይን ማንሳት እንችላለን፡፡ ይሄ የመበደል (ብሔርተኝት) ስሜትና የአንድነት ስሜትን የማራመድ ጉዳይ አዲስ ክስተት ሳይሆን ሊፈጠር የሚችል መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ልሂቃን እንደሚሉት፤የሀገር አብሮነትን ለማስጠበቅ፣ ይሄን አይነቱን የበደለኝነት ስሜት መዘንጋት ያስፈልጋል፡፡ አሰቃቂ ክስተቶችን መዘንጋትና አስተማሪ ወይም በጎ የሆኑትን መሰብሰብ ያስፈልጋል፡፡ እኛ ሀገር ያለው የብሔርተኝነት ስሜት መሰረቱ የበደለኝነት ስሜት ነው፡፡ ስለዚህ ይሄን መዘንጋት ያስፈልጋል፡፡ በአንድነት ጎራ ደግሞ የግድ ኢትዮጵያዊ አንድነትን መቀበል አለብን ብሎ መጫን አያስፈልግም፡፡ ኢትዮጵያዊነትን ከእንግዲህ ወዲህ፣ ፈቅደን መርጠን የምንወስደው እንጂ በግድ የሚጫንብን መሆን እንደሌለበት ማስተዋል አለብን። 

የብሔርተኝነቱና የአንድነቱ ጎራ ግጭት በዚህ መንገድ መታረቅና የጋራ የወደፊት አብሮነት መታሰብ ይኖርበታል። የበደለኝነት ስሜትን ትቶ አንድነትን ለማሰብ የአኖሌን ጭፍጨፋ ዘወትር ማንሳቱን ትተን፣ አንድ ያደረገንን አድዋን መዘከር አለብን፡፡ በጎ የታሪክ ገፅታችንን ማጉላት ይገባናል። የቀድሞ ታሪካችን ላይ ቆዝመን አንድነታችንን መሸርሸር ትተን፣ በወደፊት አብሮነታችንና የጋራ ራዕይ ላይ የተመሰረተ የጋራ አንድነትን ለመፍጠር መጣር አለብን፡፡ የፖለቲካ ሃይሎችም አቅጣጫቸው፣በወደፊት የጋራ አብሮነት ላይ የሚያጠነጥን መሆን አለበት፡፡ አሁን ልዩነቶችን ማጉላት ላይ ነው ያተኮርነው፡፡ 

ዛሬ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሲዳማ፣ ትግሬ እያልን እርስ በእርስ የምንከራከረው፣ የጋራ ጉዳይ፣ የጋራ አገር ስላለን ነው፡፡ ክርክሩ ራሱ የተመሰረተው በጋራ ጉዳያችን ላይ ነው፡፡ አሁን ማተኮር ያለብን “ለወደፊት በጋራ እንዴት እንኑር” በሚለው ጉዳይ ላይ ነው፡፡ በዚህ መንገድ እየከረረ የመጣውን ልዩነታችንን ማስታረቅ እንችላለን

#የዝንጀሮ_መንገድ እና የእኛ ሕገ-መንግስት አንድ ናቸው! 
 
ሀገራችን ውስብስብ በሆኑ ማህበራዊ፥ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንዳሉባት እርግጥ ነው። እነዚህ ውስብስብና እርስ-በእርስ የተጠላለፉ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት በጥናትና ዕውቀት ላይ የተመሰረተ መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ያለው የፖለቲካ አመራር ሊኖር ይገባል። ችግሩ ሲፈጠር በነበረው ወይም ችግሩን በፈጠረው የፖለቲካ አስተዳደርና አመራር፤ የመንግስትን አስተዳደርና የተቋማት አሰራር ማሻሻል፥ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ማስፈን፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ፣ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት፥ የብዙሃኑን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣… በአጠቃላይ የሀገሪቱን ማህበራዊ፥ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በዘላቂነት መቅረፍ አይቻልም። 

በዚህ መሰረት፣ ሀገራችን ከገባችበት ፖለቲካዊ ቀውስና አለመረጋጋት እንድትወጣ፣ በዜጎች ሕይወት፥ አካልና ንብረት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃትና ጉዳት ለማስቀረትና የሁሉም መብት፥ ነፃነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማስከበር በፖለቲካዊ ስርዓቱ ላይ ስር-ነቀል ለውጥ መደረግ አለበት። ይህን እውን ለማድረግ ደግሞ በቅድሚያ በፖለቲካ ስርዓቱ ውስጥ የሚስተዋሉ መዋቅራዊ ችግሮችን (structural problems) በግልፅ መለየት ያስፈልጋል። ስለዚህ የሀገራችን ፖለቲካዊ ስርዓት ያሉበት መዋቅራዊ ችግሮች ምንድን ናቸው? 

በሕገ-መንግስቱ አተገባበር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተለያዩ ፅሁፎች ለማቅረብ ሞክሬያለሁ። የዚህ ፅሁፍ ትኩረት በሕገ-መንግስቱ የተሳሳቱ መርሆች፥ ድንጋጌዎች እና የመንግስት አወቃቀር ላይ ነው። በዚህ መሰረት፣ ሦስት አንቀፆችን መነሻ በማድረግ ሕገ-መንግስቱ፤ ለዜጎች ፀረ-እኩልነት እና ፀረ-ነፃነት፣    

1ኛ) ሕገ-መንግስቱ ለዜጎች “ፀረ-እኩልነት” ነው!

ሕገ-መንግስቱ በአምስት መሰረታዊ መርሆች ላይ የተመሰረተ ነው። ከአምስቱ መሰረታዊ መርሆች ውስጥ የመጀመሪያው አንቀፅ 8 ላይ የተጠቀሰው “የሕዝብ ሉዓላዊነት” የሚለው መርህ ነው። በዚህ አንቀፅ መሰረት “የኢትዮጲያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች የኢትዮጲያ ሉዓላዊ ስልጣን ባለቤቶች ናቸው” ይላል። በዚህ መሰረት፣ የሀገሪቱ ዜጎች የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤትነት የላቸውም። በመሆኑም በሕገ-መንግስቱ የተደነገጉ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችና ነፃነቶችን የመጠየቅ፥ የማስከበር፥ የማሻሻል፥ የመቀየር፥… ሉዓላዊ ስልጣን የላቸውም። ስለዚህ ዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲየዊ መብቶችና ነፃነቶችን መጠየቅ ሆነ መጠቀም አይችሉም። 

በተቃራኒው የኢትዮጲያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤቶች ቢሆኑም በሕገ-መንግስቱ የተደነገጉ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለመጠየቅ፥ ለመጣስ፥ ለማክበር፥ ለማስከበር፥ ለማሻሻል፥ ለመቀየር፥… የሚያስችል ተፈጥሯዊ አቅም የላቸውም። ስለዚህ ሉዓላዊነታቸውን፥ የስልጣን የበላይነታቸውን ተግባራዊ ማድረግ ሆነ መጠቀም አይችሉም። 

በሕገ-መንግስቱ መሰረት፣ የኢትዮጲያ ዜጎች በሀገራቸውና መንግስታቸው ላይ ሉዓላዊ መብትና ስልጣን፣ የሰልጣን ባለቤትነትና የበላይነት የላቸውም። በአንፃሩ የኢትዮጲያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች በሕገ-መንግስቱ በተሰጣቸው ሉዓላዊ ስልጣን መሰረት በራሳቸው ምንም ማድረግ አይችሉም፤ የራሳቸውን ሆነ የዜጎችን መብት አይጥሱም፥ አያከብሩም፥ አያስከብሩም፥…ወዘተ። ኢትዮጲያዊያን በሀገራቸውና መንግስታቸው ላይ ሉዓላዊ መብትና ስልጣን (sovereign power) የላቸውም። የአንድ ሀገር ዜጎች ሉዓላዊ መብትና ስልጣን ከሌላቸው በሀገሪቱ ላይ ባለቤትነት፣ በመንግስት ላይ የበላይነት ሊኖራቸው አይችልም። ስለዚህ ሕገ-መንግስቱ ለዜጎች ፀረ-እኩልነት ነው!

2ኛ) ሕገ-መንግስቱ ለሀገር “ፀረ-አንድነት” ነው!

ሀገርና መንግስት የሚመሰረተው በወደፊት አብሮነት እና አንድነት ነው። በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 39 መሰረት አሁን ያለው መንግስታዊ ስርዓት ከወደፊት አብሮነት ይልቅ መለያየትን፣ ከአንድነት ይልቅ ልዩነትን በማስፋትና ማስረፅ ላይ የተመሰረተ ነው። በመሆኑም ሀገር ከሚመሰረትበት ፅንሰ-ሃሳብ ፍፁም ተቃራኒ ከመሆኑም በላይ በተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል ያለመተማመንና ጥርጣሬ መንፈስ የሚያሰርፅ ነው። 

ለምሳሌ በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 39(1) መሰረት፣ ነገ የትኛውም ብሔር፥ ብሔረሰብ፥ ሕዝብ ከተቀሩት የኢትዮጲያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የመገንጠል መብቱ በማናቸውም መልኩ ያለ ገደብ የተጠበቀ ነው። ይህ አንቀፅ “ትላንት ላይ አንድነት አልነበረንም፣ ዛሬ ላይ በልዩነት አለን፣ ነገ ላይ መለያየት እንችላለን” በሚል እሳቤ ላይ የተመሰረተ ነው። በመሆኑም ዛሬ ላይ አብረን እያለን ነገ ላይ ለመለያየት መንገድ ቀይሰናል።  

በመሰረቱ በመለያየት መርህ ላይ የተመሰረተ መንግስታዊ ስርዓት ለሀገር አንድነትና ሉዓላዊነት ከፍተኛ ስጋት (threat) ነው። ምክንያቱም ከትላንቱ ታሪክ ጥሩውን እያደበዘዘ መጥፎውን የሚያጎላ፣ ዛሬ ላይ ከሀገራዊ አንድነት ይልቅ የብሔር ልዩነትን የሚያቀነቅን፣ ነገ ላይ ከአብሮነት ይልቅ የመለያየት መንገድ የቀየሰ የፖለቲካ ስርዓት የሀገር ፍቅርና ክብር ከዜጎች ውስጥ ተሟጥጦ እንዲጠፋ ያደርጋል። 

የትላንቱን መጥፎ ታሪክ እየሰበክን፣ ዛሬ ላይ ልዩነትን እያጎላን፣ ነገ ላይ ለመለያየት መንገዱን ቀይሰን የወደፊት አብሮነት ሊኖረን አይቻለንም። የወደፊት አብሮነት ከሌለን ዛሬ ላይ አንድነት የለንም። ዛሬ ላይ አንድነት ከሌለን ነገ ላይ አብሮነት አይኖረንም። ዜጎች ለሀገራቸው ፍቅርና ክብር አይኖራቸውም። ይህ የአብሮነት መንፈስን በመሸርሸር የሀገር አንድነት፥ ፍቅርና የዜግነት ክብር ከዜጎች ልብ ውስጥ ተፍቆ እንዲጠፋ ያደርጋል። ስለዚህ ሕገ-መንግስቱ ለሀገር ፀረ-አንድነት ነው!

3ኛ) ሕገ-መንግስቱ ለሕዝብ “ፀረ-ሰላም” ነው!  

በዚህ ረገድ የመንግስትን አወቃቀር የሚደነግገውን የሕገ-መንግስቱን አንቀፅ 49 እንደ ማሳያ መጥቀስ ይቻላል። በንዑስ አንቀፅ 2 ላይ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ስልጣን እንዳለው ይጠቅሳል። ቀጥሎ ባለው ንዕስ አንቀፅ 3 ግን “የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ተጠሪነቱ ለፌደራሉ መንግስት ይሆናል” ይላል። የአዲስ አበባ ከተማ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ስልጣን ካለው የከተማው መስተዳደር ተጠሪነቱ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መሆን አለበት። ከዚህ በተጨማሪ፣ አዲስ አበባ ከተማ የፌደራል መንግስት እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት “ርዕሰ ከተማ” ናት። በመሆኑም የፌደራሉ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተለየ መብትና ስልጣን ሊኖረው አይችልም። ስለዚህ የከተማ መስተዳደሩ ተጠሪነት ለፌደራል መንግስት ብቻ የሚሆንበት አግባብ የለም። 

ከዚያ ይልቅ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ በሕገ-መንግስቱ መሰረት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የራሱ መቀመጫ አለው። ከዚህ በተጨማሪ፣ እንደ ማንኛውም ክልል የራሱ የሆነ ምክር ቤት አለው። ስለዚህ የከተማ መስተዳደሩ ተጠሪነቱ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ራስን በራስ የማስተዳደር መብታቸውን ተጠቅመው ለመረጡት የከተማ ምክር ቤት መሆን አለበት። የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር ተጠሪነቱ ለኦሮሚያ ምክር ቤት (ጨፌ) ነው። የአማራ ክልል መስተዳደር ተጠሪነቱ ለአማራ ክልል ምክር ቤት ነው። የፌደራሉ መንግስት ተጠሪነቱ ለፌደራሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ተጠሪነቱ በከተማ ነዋሪዎች ለተመረጠ የከተማው ምክር ቤት መሆን አለበት።   

ይህ ባለመሆኑ ምክንያት፤ አንደኛ፡- የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ራስን በራስ የማስተዳደር መብትና ስልጣን ተገፍፏል፣ ሁለተኛ፡- የፌደራሉ መንግስት በከተማዋ ላይ የማይገባውን ስልጣን ተሰጥቶታል፣ ሦስተኛ፡- ይህን የማይገባ ስልጣን በመጠቀም፣ በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ መስተዳደር መካከል የተቀናጀ የአገልግሎት አቅርቦት፣ የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም እና አስተዳደራዊ ግንኙነት እንዳይኖር አድርጓል፣ በአንቀፅ 49(5) መሰረት የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም እንዳይከበር እንቅፋት ሆኗል። በዚህ መሰረት፣ የከተማዋ ነዋሪዎች እና የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ ጥቅምና ተጠቃሚነት እንዳይረጋገጥ አድርጓል። የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ አገልግሎቶች አቅርቦትን አስተጓጉሏል፣  በመኖሪያ ቤትና በትራንስፖርት አገልግሎት እጥረት ተንገላተዋል። ለግንባታ በሚል ሰበብ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው መንገድ ላይ ወድቀዋል፣ ለጤና መታወክና ለውሃ ወለድ ወረርሽኝ በሽታ ተጋልጠዋል። 

በመሰረቱ መሬት፤ አንደኛ፡- በሀገራችን ዋንኛ የሃብት ምንጭ የብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጫ ነው። ሁለተኛ፡- በሀገራችን ሁኔታ መሬት ከማንነት ጋር የተያያዘ ስለሆነ ብሔር ብሄረሰቦች የማንነት መገለጫዎቻቸውን ማሳደግ የሚችሉት ከመሬት ያለመነቀል ዋስትና ሲያገኙ ነው። ሆኖም ግን፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሞ አርሶ አደሮች ያለ በቂ ካሳ ክፍያ ከመሬታቸው በግፍ ተፈናቅለዋል። 

ከዚህ በተጨማሪ፣ ከተማዋ በሚወጣው የተበከለ አየርና ፍሳሽ፣ እንዲሁም ደረቅ ቆሻሻ ምክንያት በማህብረሰቡ ጤንነትና የአከባቢ ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ይህ ሁሉ የሆነው በፌደራሉ መንግስት ጣልቃ-ገብነት ምክንያት ነው። ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል የተነሳው አመፅና ተቃውሞ፣ በንፁሃን ሕይወትና ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት በሙሉ በፌደራሉ መንግስት ጣልቃ ገብነት ነው። ለጣልቃ ገብነቱ መንስዔ ደግሞ ሕገ-መንግስቱ ነው። ስለዚህ ሕገ-መንግስቱ ለሕዝብ ፀረ-ሰላም ነው!  

በአጠቃላይ ሕገ-መንግስቱ የተመሰረተው፤ ለዜጎች ፀረ-እኩልነት፣ ለሀገር ፀረ-አንድነት፣ ለሕዝቦች ፀረ-ሰላም በሆነ ፅንሰ-ሃሳብ ላይ ነው። በዚህ ሕገ-መንግስት መሰረት ላለፉት አመታት የዜጎች መብት፥ የሀገር አንድነት፥ የሕዝብ ሰላም አልተከበረም። ይህን ሕገ-መንግስት ይዞ ስለ ዜጎች መብትና ነፃነት፣ ስለ ሀገር አንድነትና ሉዓላዊነት፣ ስለ ሕዝብ ሰላምና ደህንነት ማውራት፥ መናገር፥ መደስኮር፥ … ከቶ እንዴት ይቻላል? ይህን ሕገ-መንግስት ይዞ ጉዞ “የዘንጀሮ መንገድ ቢከተሉት ገደል” የሚሉት ዓይነት ነው

🐬🐬እጅግ በጣም የሳትነው ብዙ ነገር አለ። 
እነዛ የሶሻሊዝምን ጽንሰ-ሃሳብ በውል ያልተረዱ፣ ጺማቸውንና ጠጉራቸውን የሚያሳድጉ የ60'ዎቹ ተማሪዎች "ማርክስ እንዳለው …፣ ኤንግልስ እንዳለው…፣ ሌኒን እንዳለው …፣ ማኦ እንዳለው …፣ ቼጉቬራ እንዳለው…፣ ሆቺሚኒ እንዳለው…፣ እስታሊን 

 እንዳለው…፣ " ወዘተ እያሉ ታሪካችና እሴቶቻችን እንዲጠለሽ አድርገዋል።

የ60'ዎቹ ትውልድ ባህሉን፣ ወጉን፣ ሥርዓቱን፣ ሥነ-ጽሑፉን፣ ታሪኩን ጭምር ነቅፎ በባዶ እጁ 
ነው የሸፈተው። ከቆዳ ቀለማቸው በስተቀር የኢትዮጵያዊነትን ነባር እሴት፣ ባህል፣ ወግ፣ ታሪክ... ፍቀው የነማርክስንና የነስታሊን ፍልስፍና ይዘው ነው የሸፈቱት።

መፍትሔው እግዚአብሔርን መካድ የመሰለው ማርክሲዝምን ርዕዮተ ዓለም አድርጎ የተነሣው የሶሻሊስት አቀንቃኝና የብሔር ፖለቲካን ቀይጦ የያዘው ወጣት የኢትዮጵያዊነት አስኳል ከውስጣቸው አውጥተው ጣሉት። በአጉል ማርክሳዊ-ሌኒናዊነት እግዚአብሔር-አልባ አደረጋቸው።

ትውልዱንም ሳይቀራረብ የሚተያይ፣ በማያውቀው ታሪክ ተተብትቦ ወደኋላ እንጂ ወደፊት መራመድ የማይችል፣ ባዕድን እንደ ዘመድ፤ ዘመድን እንደ ባዕድ የሚመለከት ሽባ ትውልድ አደረጉት።
እንጥፍጣፊ ሳያስቀር የኩራቱንና የክብሩን ካባ አውልቆ ጣለው፣ ኢትዮጵያዊነትን በአፍጢሙ ደፋው፣ የመንፈስ ኃይሉ ደቀቀ፣ በመጨረሻም አንገቱን ደፋ፣ ችግሩንም ሁሉ ለመፍታት የፈረንጆችን እርዳታ የሚፈልግ ትውልድ ተፈጠረ።

ቀጥሎስ.....ቀጥሎ ደግሞ የኢትዮጵያ እደ ጥበብ ሠራተኞችን፦ ለምሳሌ ብረት ሰሪዎችን "ቀጥቃጭ"፣ ልብስ ሰሪዎችን "ሸማኔ"፣ ቆዳ ሰሪዎችን "ፋቂ" በማለት እንዲጠፉና ከማኅበረሰቡ እንዲገለሉ አደረገ። ይህ ቅስቀሳ በሚሲዮናውያን የተጀመረ ቢሆንም በዚህኛው ትውልድም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

እንዲያው ለመሆኑ ብረት ሰሪዎች ባይኖሩ ኖሮ ገበሬው በምን ያርስ ነበር? በምንስ ታጭዶ ይገባ ነበር? የኢትዮጵያ ነፃነትስ ተጠብቆ የቆየው በጦርና በጉራዴ አይደለምን? ሸማኔዎች ልብስ ባይሸምኑ፣ ሴቶች ጥጥ ባይፈትሉ፣ ገበሬው ጥጥ ባይዘራ ኖሮ ምን እንለብስ ነበር? ቆዳ ሠራተኞች ባይኖሩ ኖሩ አርበኞቻችን በጦርነት ጊዜ የሚለብሱት ጋሻ ከዬት ይመጣ ነበር። ይህን ጋሻ የሠራ ሰው እንደምን ይናቃል?
አሁን ይሄን የሚያስተካክል የተፍታታ፣ የነቃ፣ የበቃ ትውልድ ያስፈልገናል። መንቃትና መነሳት አለብን። በጣም የሚያስገርመው ያለፈው ትውልድ የመሬት ልብ እየሰነጠቀ ሐውልት ገንብቷን፤ ቤተ መቅደስ አንጿል፤ ሀገር ከነነፃንቱ አስረክቧል፤ ነገርግን 
ጥንት ከነበረው ትውልድ ተከታታይ ትውልዶች አንድ እርከን ወደላይ አላሳደገውም። ሌላው ቀርቶ
ከአንድ ዓለት ተፈልፍሎ የተሠራው የላሊበላ ኪነ-ሕንፃ ግማሹ ወድቆ ተሰባብሯል የሚጠግነው ትውልድ ገና አልመጣም?

#ህወሐት_ገንዳ_ውስጥ_እንደሚኖር_ዓሳ ናት። 
ዓሳ ከገንዳው ውስጥ ቢወጣ መተንፈስ እንደማይችል ሁሉ ሕወሐትም ከገንዳዋ ብትወጣ መኖር አትችልም።
ታዲያ የኛው ሐገር አረመኔና ቀማኛ የሆነችው ህወሐት ከናዚዎች በምን ተለየች?
ህወሐት መቼም አትማርም፡፡ ምክንያቱም የተዋቀረችው አዲስ ዕውቀት ለመማር ወይም አዲስ ዕውቀት ለመፍጠር ሳይሆን ከውስጡ በፊውዳላዊ ቂምና ቁርሾ የተለወሰ ከላይ ደግሞ በዴሞክራሲያዊ አምባገነንነት የተለበጠ ርዕዮተ ዓለም ለማስፋፋት ነው። የዕውቀቷ መጠን ፈጣሪዎቿ ተብትበው የሰጧትን ዴሞክራሲያዊ አምባገነንነት እንደመዝሙረ ዳዊት መሸምደድ ነው። ከዚያ ውጭ እንድታውቅ አይፈቀድላትም። አዲስ ዕውቀት መቅሰም ዓይኖቿ እውነታን እንዲያዩና ጆሮቿ እውነትን እንዲሰሙ ስለሚያደርግና ይህም ደግሞ በተራው በመተግበር ላይ ያለችውን የተሳሳተ ርዕዮት የትም እንደማያደርሳት ስለሚያሳያት እንደ ዓላማዋ እንቅፋት ታየዋለች። ለምሳሌ ሕዝቡን የሚያስቀድም እና መብታቸውን የሚያከብር እውነተኛ ዴሞክራሲ ሲነሳባት ያቅለሸልሻታል።

በተምሳሌት ስናየው ህወሐት ገንዳ ውስጥ እንደሚኖር ዓሳ ናት። ዓሳ ከገንዳው ውስጥ ቢወጣ መተንፈስ እንደማይችል ሁሉ ሕወሐትም ከገንዳዋ ብትወጣ መኖር አትችልም። የምታውቀው እዚያው ገንዳዋ ውስጥ በራሷ የቆሸሸ ፍሳሽ በተጨማለቀው ውኃና በተበከለው አየር መተራመስን ብቻ ነው። አዲስ ውኃና ንፅህ አየር አይስማማትም። ከሚከረፋው ገንዳዋ ውስጥ ሊያወጧት የሚሞክሩትን ሁሉ ጠላቶቿ ታደርጋቸዋለች። እንዲያውም ውኃውን ለመቀየርና አየሩንም ለማስተካከል ቢሞከር ታኮርፋለች፣ እንዳበደ ውሻ መናከስ ትጀምራለች፣ የፈሪ በትሯን ታምዘገዝጋለች። ያለችበት የከረፋ የገንዳ ሥርዓት ስለተዋሃዳትና ባሕሏም ስላደረገችው ክርፋቱም ተስማምቷታል። ሁለመናዋ ለበሰበሰው ውኃና ለከረፋው አየር ተስተካክሏል። አንዳንዴ ገንዳው በጣም ሲደፈርስና ሲጨልምባት “ተሐድሶ” በማለት ድፍርሱን ያጠራች እየመሰላት ባስመሳይ እርምጃዎች ትውገረገራለች። “ውኃ ቢወቅጡት እምቦጭ” እንዲሉ ከማይፀዳ የበሰበሰ ገንዳ ውስጥ ተሰብስባ መታደስ ያለፈውን መድገም እንጂ አዲስ ነገር እንደማያመጣ ማወቅ ተስኗት ነው የኖረቸው። ከዚያ ገንዳ ለመውጣት ከፈለገች የትም የማያደርሳትን የጠባቦች ራዕዮቷን መተውና አእምሮዋን ለአዲስ አውነታዎች መክፈት ይኖርባታል። ነገር ግን የራሷን የገንዳ ባሕል የፈጠረች የመንደርተኛ ጥርቅም ስለሆነች አዲስ ለውጥ ከመቀበል ይልቅ መጥፋቷን ትመርጣለች። መለወጥ ብትፈልግ ኖሮ ገንዳዋን ከነወጀለኞቿ ጠቅልላ እንደልማዷ ወደመንደሯ ባልሸሸችና አሁን በመካሄድ ላይ ያለውን ለውጥ ለመቀልበስ ባልተፍጨረጨረች ነበር።
አሸባሪዎቹ የህወሓት መሪዎች በከረፋው ዴምክራሲያዊ ማዕከላዊ አምባገነንነት ገንዳቸው ውስጥ ተለውሰው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈፀሙዋቸው ፋሺስታዊና ትዕቢታዊ ግፎች በታሪክ ተመዝግበው የሚኖሩ ጥቁር ነጥቦች ናቸው። ሕዝቡን ሳያማክሩት በራቸውን ዘግተው በአፓርታይድ ፖሊሲ ከፋፍለውት በድንበርና በሌሎች ዘረኛ ምክንያቶች እርስ በርስ አንዲጫረስ አድርገዋል፣ እያደረጉም ናቸው። ሕዝቡንም መከፋፈላቸው የሐገሪቷን ሃብቶች ያላንዳች ሐፍረት ለመዝረፍ አስችሏቸዋል። የኢትዮጵያውያንን ሰብዓዊ መብቶች ያላንዳች ቅሬታ ጥሰዋል። በጅምላ ገድለው በጅምላ ቀብረዋል። መግደል ያልቻሉትን ወንዶች አኮላሽተዋል፤ ሴቶችች ደፍረዋል፤ ግብረ ሰዶም ፈፀመዋል፣ እስረኞች ላይ ሽንታቸውን ሸንተዋል፤ ጥፍሮች ነቅለዋል፤ በኤሌክትሪክ አቃጥለዋል፤ የተቃዋሚ እስረኞችን ገላ እንደ ሲጋራ መተርኮሻ ተጠቅመውበታል፤ እግሮችና እጆች ቆርጠዋል፤ ዘቅዝቀው ገርፈዋል። በአጠቃላይ በዓለም አቀፍ ሕግ የሚያስጠይቃቸውን ሰቆቃ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ፈፅመዋል። በገሐድ የተሠሩት እሥር ቤቶች አልበቃ ብሏቸው በድብቅ እሥር ቤቶች ውስጥ ብዙውን አሰቃይተዋል። ሜዳ ተወልደው ሜዳ አድገው የአንድን ሕዝብ አንድ ክፍል ብቻ “ነፃ ለማውጣት” የተዋጉና ሌላውን የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደጠላት ወይም እንደ መጠቀሚያ እንጂ እንደሐገራቸው አይተውት የማያውቁ የጫካ ልጆች ስለኢትዮጵያ ደሕነንትና ብልፅግና የማሰብ ውስጣዊ ልቦና የላቸውም። ስለዚህም የወረሩን ለኛ ለኢትዮጵያውያን አስበው አይደለም፤ የወረሩን ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ነው። ይህን ሁሉ ነውር እና አሰቃቂ የወንጀል ተግባር ሲፈፅሙ፤ ሰብዓዊ መብትን ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ሲጥሱ፤ ራሳቸው የፈተሉትን ሕገ መንግሥት አንቀጾች 18-24ን እየጣሱ ነው። ከሁሉም በላይ የሚያሰቅቀውና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ስሜት እንደሌላቸው የሚያሳየው፤ ይህ ሁሉ ኢሰብዓዊ ድርጊት ይፋ ሲወጣና የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲያዝን፤ እነሱና ደጋፊዎቻቸው ግን ኢሰብዓዊ የግፍ ስቃይ የደረሰባቸውን ወገኖች “እሰይ! እንኳን ለጥፋታቸው ተመጣጣኝ ቅጣት አገኙ” በማለት አረመኔነትን ሲደግፉ በሚዲያ አዘውትረው ተሰምተዋል፡ የትምክህተኛና የገዳይ ባህርያቸውን እያጋነኑ ደረት መንፋቱ የሕዝቡን ሰቆቃ ከመገንዘብ በልጦባቸው።

እነዚህ አረመኔዎች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈፀሙት ግፍ የጀርመን ናዚዎች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በይሁዶችና በሌሎች ሕዝቦች ላይ ከፈፀሙት ግፍ የማያንስ ነው። ለምሳሌ በጀርመን አገር ውስጥ ቫይማር ሪፐብሊክ በሚባል ክፍል ቡከንቫልድ በሚባል ትልቁ ኮንሰንትሬሽን ካምፕ ውስጥ የታጨቁት ከአሥር ሺህ የማያንሱ ይሁዶችን፣ የጦር ምርከኞችን፣ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን፣ አካለ ስንኩላንን፣ የሐይማኖት ሰዎችን፣ ተራ ወንጀለኞችን፣ ሌሎችንም በመርዝ ጋዝ ከመፍጀታቸውም አልፎ በሕይወት እያሉ አካላታቸውን በመቆራረጥ የተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶችን (ኤክስፐሪመንቶችን) ካደረጉባቸው በኋላ በእሳት አጋይተዋቸዋል። ብዙዎቹንም በተለያዩ አረመኔያዊ ዘይቤዎች በመጠቀም ጥፍሮቻቸውን መንቀል፣ የአካላቸውን ክፍሎች መቁረጥ፣ ቆዳቸውን በሕይወት እያሉ መግፈፍ ዕለታዊ ተግባራቸው አድርገውት ነበር። እነዚህኑ ግፎች በሌሎች የኮንሰንትሬሽን ካምፖችም የሚሊዮን ሕዝብ ሕይወትን አጥፍቷል። ናዚዎች ይህን ሁሉ አረመኔያዊ ግፍ ሲፈፀሙ የአርያን ዘር በላይነት መብት እንዳላቸው በማመነን ያን መብት የማስከበር ግዴታ እንዳለብቸው በማሰብም ጭምር ነው
ታዲያ የኛው ሐገር አረመኔና ቀማኛ የሆነችው ህወሐት ከናዚዎች በምን ተለየች?
ወደፊት ለመራመድ መፍትሄው ፀሐይዋ የጠለቀችባትን ህወሐት ከነበሰበሰ ገንዳዋ ከትግራይ አገዛዝ አስወግዶ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ ነው። 
«ኧረ ባባጃሌው! ሴት ደሞ ልትሾም? አንተስ ጉደኛ እየሆንክ ሔደሃል። አባትህ ይሄን ጉድ 
አላዩ» አሉ ወይዘሮ ደብሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ከልብ የተኮሳተሩ መስለው። ግን ይህም በሙሉ 
አልተዋጣላቸውም። ቁጣችው ከልባቸው አለመሆኑ የሚያሳጣቸው ከዐይን አገላለጣቸው፣ ከከንፈር መሥመራቸው አንድ ልዩ ምልክት ያለ ይመስላል። 
«ለምን አትሾምም ይኸው ተዋበች ተሹማ የለ?» አለ ጋረድ በመጠጡ ኃይል ርግጥ አድርጎ፤ 
«ያውም የመጨረሻውን!» 
«ኧረ ባባጃሌው፤ ያ ሌላ ይኼ ሌላ» አሉ ወይዘሮ ደብሬ ነገሩን በማቃለል። 
ብዙ ሰው ግን ግራ ተጋብቶ፣ ተገርሞ ዝም አለ። የጋረድ አሽሙር የታንጕትንም እንደ መርፌ 
ጠቅ አደረጋት። አዎ፤ እርሷም በአደባባይ ክብርና ማዕረግ ማግኘቱን ትወደው ነበር። ግና አላገኘውም። 
እርግጥ አባ ታጠቅ እንደልጅ አሳድጎ፤ ከዚያ ባላነሰ ፍቅር እንደሚያመለክታት ይታወቃታል። ከዚህ በተረፈ ግን የፍቅሩ መሠረት ለሰው በግልጽ አይታወቅም። እንዳሳደጋት የቤት በምሥጢር ነው። ዛዲያ ፀሐይ ካላየው ወዳጅና ጠላት ካላወቀው ምን ርባና አለው? ተዋበች ግን ከርሷ በኋላ መጥታ እንሆ ጋረድ እንዳለው በአደባባይ የመጨረሻውን ቀሚስ ለብሳለች። ታንጕት ከዚህ ሐሳብ ላይ ስትደርስ፣ ራሷን ይዛ እግዚኦ ማለት ቃጣት፤ እንደ ትልቅ እህት ትወዳታለች። ለካሣ መንገር የማትደፍረው ግን እንዲሆንላት የምትፈልገውን የምታማክረው ለተዋበች ነበር። ካሣን፣ የአሁኑን ቴዎድሮስ ከራስዋ ይልቅ ተዋበች እንደሚረግፍ አበባ ተንከባክባ እንደምትይዘው ታውቃለች። ‹ታዲያ እኔ በተዋበች ማዕረግ ልቅና?› ስትል ራሷን ጠየቀችና ራሷን በምሬት ለመውቀስ ሞከረች። ወዲያው መልሳ፤ ‹ግና ደግሞስ እኔስ ብሆን› የሚለው ጥያቄ ከጋረድ አነጋገር ጋር አስማማት። ሐሳብዋን ሁሉ ሲማታባት፤ ወደ ጓዳ ገብታ በተደረደረው ምግብና መጠጥ መካከል ዘፍ አለችና፤ አገጭዋን በመዳፎቿ አስደግፋ ዝም ብላ ተቀመጠች። 
በአካልም፤ በሐሳብም ደከማት። ከአዳራሹ የሰው ንግግር ይሰማታል። 
ጥቂት ቆይቶ ቅልል ሲላት፤ በአንዳች ዐይነት ምሥጢር ያውቁ ይመስላል ወይዘሮ ደብሬ 
መጡና፤ «ኧረ ባባጃሌው! ነይ እንጂ እንግዳሽን ሸኝ!» አሏት። የድካም ፈገግታ እያሳየች ተከተለቻቸው። 
ጋረድ ቀደም ሲል በአክሊሉ ተገፋፍቶ ወጥቶ ስለ ነበር አላገኘችውም። «ያ ቋረኛስ እንደሆነ 
እየቀባጠረ ሔዷል» አሏት ወይዘሮ ደብሬ ሐሳቧን የተረዱ ይመስል። ሌሎችም አንዳንዱ፤ ከአንገቱ 
ቀልበስ፤ ሌላው ከትከሻው ሰበር፣ ወይም ከወገቡ አጠፍ እያለ ተሰናብቶ አለቀ። 
«በይ እንግዲህ እንዳሻሽ!» አሉና በመጨረሻው ወይዘሮ ደብሬ ተሰናበቷት። 
«መሔድዎ ነው!»
«ኧረ ባባጃሌው! ዛዲያ ከዚህ ላድርልሽ ነው?» 
እንግዶች ሁሉ ሔደው፤ ሠራተኞች ሁሉ ተሰናብተው ታንጕት ከበለጡ ጋር ብቻቸውን ከቀሩ በኋላ፤ «ጉድ አይደለም?» አለቻት። 
«ኧረ! እሜቴ ደስ የሚል ዓለም ነው!» አለች በለጡ በመቅበጥበጥ። 
ከዚህም ከዚያም ስታሟላና ስታገላብጥ ቀማምሳ ነበር። 
«ዝብርቅርቅ አልሆነብሽም በለጡ?» አለች ታንጕት በአብዛኛው ከራሷ ጋር። የወይዘሮ ደብሬን 
ከጋረድ ጋር፣ ብዙ ከማይናገረው የሎዛ አለቃ እየፎከረ ለያዥ ለገላጋይ አሰግሮ የተሰኘው አንድ ደጅ 
ጠጥቶ --- የገብርዬን አሽከር ሲል እየፎከረ ለያዥ ለገላጋይ አስቸግሮ የተሸኘው አንድ ደጅ ጠጅ መሳይ ጋር ሁሉንም አነጻጸረችው። 
«ኧረ ቢሆንም ውብ ዓለም ነው» አለች በለጡ በድጋሚ። «ምንም አልቀመሱትም እኮ እትዬ!» 
ስትል ብርሌ ጠጅ አመጣችላት። 
በእውነት ጉሮሮዋ ደርቆ ነበር። በአብዛኛው በሐሳብ። ጎንጨት አደረገችና፣ «ምኑን እናውቃለን  ብለሽ። እስቲ መጨረሻውን ያሳምረው» አለች። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ)