30 የ ICT ቴክኒካዊ ስያሜዎች

30 የ ICT ቴክኒካዊ ስያሜዎች
1. #ጥቁር_መዝገብ (Blacklist) - በገዳቢ የክልከላ ፖሊሰ የታገዱ ድረ ገጾች እና ሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶች ዝርዝር ነው።
2. #ብሉቱዝ (Bluetooth) -ገመድ አልባ ከሞባይል እና ከባለመስመር ስልኮች በአጭር ርቀት ዳታ ለመላላክ የሚያስችል ገመድ የግንኙነት ደረጃ ነው። ቡሉቱዝ ዳታ ለመለዋወጥ አጭር ሞገዶችን ይጠቀማል
3. #ቡቲንግ (Booting) - ኮምፒውተርን ሥራ
ማስጀመር ወይም ማስነሳት ነው።
4. #አቫስት (Avast) - ጸረ ቫይረስ መሣሪያ
5. #መሠረታዊ _የግብአት/ውጤት ሲስተም ሶፍትዌር (Basic Input/Output System-BIOS) -የኮምፒውተር ሶፍትዌር የመጀመሪያው እና መሠረታዊው ደረጃ ነው። ባዮስ የኮምፒውተራችንን ሐርድዌር ደኅንነት
ለማረጋገጥ የሚረዱ የተለያዩ አማራጮችን ይሰጠናል፤ኮምፒውተራችን ሲከፈት በይለፍ ቃል ብቻ እንዲገባ ማድረግ ከእነዚህ አንዱ ነው።
6. #ሲክሊነር (CCleaner) - በነጻ የሚገኝ ሶፍትዌር ነው። በቅርብ በተጠቀምንባቸው ፕሮግራሞችና በዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲሰተም አማካኝነት በሐርድዌራችን ላይ የተተዉ ጊዜያዊ ፋይሎችን ዱካ የሚያሳዩ መረጃዎችን የሚያጸዳ ሶፍትዌር ነው።
7. #ሲዲ_በርነር (CD Burner) - በባዶ ሲዲዎች ላይ መረጃ ለመጻፍ የሚችል የኮምፒውተር ድራይቭ ነው።ዲቪዲ በርነር (DVD burners) በተመሳሳይ መንገድ በባዶ ዲቪዲዎች ላይ ይጽፋል።ሲዲ-አርደብሊው (CD-RW ) እና ዲቪዲ-አርደብሊውድራይቮች (DVD-RW drives) ደግሞ በሲዲ/ ዲቪዲ ላይ የተጻፈውን አጥፍተው ከአንድ ጊዜ በላይ መልሰው መጻፍ ይችላሉ።
8. #ሰርከምቬንሽን (Circumvention) - በኢንተርኔት አፈና የታገዱ ድረ ገጾችን እና
የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለማግኘት እገዳውን ማለፍ።
9. #ክሌም_ዊን (Clam Win) - ለዊንዶውስ
የተሠራየኤፍኦኤስኤስ ጸረ ቫይረስ
10. #ኮቢያን_ባክአፕ (Cobian Backup) -
የኤፍኦኤስኤስ የመጠባበቂያ ማከማቻ መሣሪያ ነው።የቅርብ ጊዜዎቹ የኮቢያን አይነቶች ምንጫቸው የማይገለጽ ነገር ግን በነጻ የሚገኙ ናቸው፤የቀድሞዎቹ ግን በኤፍኦኤስኤስ ብቻ የሚለቀቁ ነበሩ።
11. #ኮሞዶ_ፋየርዎል (Comodo Firewall) -
ምንጩ (ውስጣዊ መዋቅሩ) ለምርመራ ክፍት የሆነ፣በነጻ የሚገኝ የፋየርዎል መሣሪያ ነው።
12. #ኩኪ (Cookie) - የኢንተርኔት ማሰሻ
(browser) በኮምፒውተር ላይ የሚተዋቸው የጎበኘነውን ድረ ገጽ እና ተያያዥ መረጃዎችን መዝግቦ የሚይዝ አነስተኛ ፋይል ነው።
13. #ዲጂታል_ፊርማ (Digital signature) -
ኢንክሪፕሽንን በመጠቀም አንድ ፋይል ወይም መልእክት ከትክክለኛው ሰው የተላከ መሆኑን
የማረጋገጫ መንገድ
14. #የዶሜይን_ስም (Domain name) - በቃላት የሚገለጽ የድረ ገጽ ወይም የኢንተርኔት አገልግሎት አድራሻ
15. #ኢንክሪፕሽን (Encryption) - የተራቀቀ ሒሳባዊ ስሌትን በመጠቀም ኢንክሪፕት (encrypt) ማድረግ፤ትክከለኛው መረጃ ማለትም ያለው የይለፍ ቃል ወይም የኢንክሪፕሽን ቁልፍ (encryption key) ሰው ብቻ ኢንክሪፕት የተደረገውን መረጃ ዲክሪፕት ማድረግ/
መክፈት (decrypted) እንዲችል የሚያደርግ
16. #ኢንጂሜይል (Enigmail) - የታንደርበርድ
የኢሜይል ፕሮግራም አጋዥ መሣሪያ (add-on) ነው፤ተጠቃሚዎቹ ኢንክሪፕት የተደረገ ወይም
በዲጂታል ፊርማ የታተመ መልእክት ለመላክና ለመቀበል የሚያስችል
17. #ኢሬዘር /መደምሰሻ (Eraser) ከኮምፒውተር ወይም ከሌሎች ተንቀሳቃሽ የመረጃ ማከማቻዎች ላይ የሚገኝ መረጃን በአስተማማኝ እና በዘላቂነት ከነጭራሹ
ለማጥፋት (delete) የሚያከማይክሮሶፍት
18. #ፋየርፎክስ (Firefox) - የታወቀ የኤፍኦኤስኤስ ማሰሻ (FOSS Web browser) ነው፤ ከማይክሮሶፍት ማሰሻ “ከኢንተርኔት ኤክስፕሎረር” የተለየ አማራጭ ነው።
19. #ፋየርዎል (Firewall) - ኮምፒውተርን
አስተማማኝ ካልሆኑ የኢንተርኔት እና የቤትውስጥ መረቦች ግንኙነት የሚጠብቅ መሣሪያ ነው።
20. ነጻና_ቀመሩ የሚታይ ሶፍትዌር ኤፍኦኤስኤስ
(Free and Open Source Software-FOSS) -ያለክፍያ በነጻ የሚገኙ እንዲሁም ተጠቃሚዎች የሶፍትዌሮቹን አሠራር እንዲመረምሩ፣ እንዲፈትሹ፣እንዲያሻሽሉና ለሌሎች አሳልፈው እንዲሰጡ የሚፈቅዱ
ሶፍትዌሮች ምድብ
21. #ፍሪዌር (Freeware) - በነጻ የሚገኙ፣ ነገር ግን ተጠቃሚዎች መሠረታዊ የፈጠራ አወቃቀሩን (sourcecode) እንዳያገኙ ሕጋዊና ቴክኒካዊ ክልከላዎችን የሚያደርጉ ሶፍትዌሮች
22. #ጂኤንዩ /ሊኑክስ (GNU/Linux) -
የኤፍኦኤስኤስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ነው፤
ለማይክሮሶፍት ዊንዶውስ አማራጭ ሲስተም ነው።
23. #ጂፒኤስ (Global Positioning System -GPያደረገ በስፔስ/ምህዋር ላይ መሠረት ያደረገ በሳተላይት በመታገዝ ቦታንና ጊዜን ለመለየት የሚያስችል፤በማንኛውም የአየር ሁኔታ፣ በየትኛውም የምድራችን ወይም በአቅራቢያዋ ባሉ ቦታዎች የሚሠራ፤ ከሞላ ጎደል በምንም ነገር የማያደናቀፍ ከሰማይ ከፍታ ለመመልከት የሚያስችል የሳተላይት መመልከቻ ነው።
24. #ሐከር /ሰባሪ (Hacker) በዚህ አገባቡ፣ ከርቀት ኮምፒውተራችንን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ወይም ስስ መረጃዎቻችንን ለመስረቅ አይፒ የሚሞክር ወንጀለኛ
25. #የኢንተርኔት_ፕሮቶኮል_አድራሻ -(
አድራሻ) (Internet Protocol address -IP
address) - ማንኛውምሰጪ ኮምፒውተር ከኢንተርኔት ጋራ ሲገናኝ የሚሰጠው ልዩ መለያ
26. #ኢንተርኔት_አገልግሎት (አይኤስፒ)
(Internet Service Provider-ISP) - የኢንተርኔት ወይም ግንኙነት መስመር አገልግሎት የሚሰጥ ኩባንያ ወይም ድርጅት። የብዙ አገሮች መንግሥታት ኢንተርኔትን በጣም
ይቆጣጠራሉ፤ እነዚህን አገልግሎት ሰጪዎች (አይኤስፒ) በመጠቀምም የኢንተርኔት አሶሲዬሽን ክልከላ፣ ስለላ እና እገዳ ያደርጋሉ።
27. #ኢንፍራሬድ_ዳታ (Infrared Data
Association) (ኢርዳ/IrDAአልባ በአጭር ርቀት የኢንፍራሬድ ስፔክተረም ጨረሮችን በመጠቀምመረጃ/ዳታ ለመለዋወጥ የሚያስችል ገመድ አልባ የግንኙነት መንገድ ነው። በዘመናዊ መገልገያዎች ውስጥ ኢርዳ/IrDA በብሉቱዝ ተተክቷል።
28. #ጃቫ_አፕሊኬሽንስ (Java Applications) (አፕልትስ/Applets) - በብዙ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ላይ የሚሠሩ አነስተኛ ፕሮግራሞች ናቸው። ብዙውን ጊዜ በድረ ገጾች ውስጥ የተሻሻሉ አገልግሎቶችን (functionalities) ለመስጠት ጥቅም ላይ ይውላሉ።
29. #ኪይሎገር (Keylogger) - ለስለላ ተግባር
የሚውል የስፓይዌር አይነት ነው፤ በኮምፒውተሩ
የመተየቢያ ገበታ (keyboard) ላይ የነካናቸውን/ የተጫንናቸውን ቁልፎች/ፊደሎች በሙሉ መዝግቦ ለሦስተኛ ወገን ይልካል። ኪይሎገሮች የኢሜይሎችን እና የይለፍ ቃሎችን ለመስረቅ በብዛት ጥቅም ላይ ይውላሉ።
30. #ኪፓስ (KeePass) - የአስተማማኝ የይለፍ ቃል ማከማቻ (database) ፍሪዌር ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ)