የውሳኔ_ስሌት
የውሳኔ_ስሌት!
አንድን ውሳኔ በመወሰንና ባለመወሰን መካከል ስትዋዥቁ በአእምሯችሁ ብቅ ጥልቅ የሚሉ ሁለት ሃሳቦች አሉ፡፡ በአንድ በኩል ውሳኔው ትክክል ቢሆን የምታገኙት ጥቅም ሲሆን፣ በሌላ ጎኑ ግን ውሳኔው ስህተት ቢሆን የሚያስከትለው ችግር ነው፡፡ በተለይ እንድትወላውሉ የሚያደርጋችሁ ስሜት ሊያጋጥማችሁ የሚችለውን ችግር ስታስቡ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ከአንዳንድ ውሳኔዎች በኋላ ምንም ጥቅም ባናገኝም እንኳን ሊደርስብን ከሚችል ችግርና ክስረት ተጠብቀን በዜሮ መገላገል የሚመረጥበት ጊዜ እንዳለ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡
ውሳኔያችሁን ከምታገኙት ጥቅም ብቻ አንጻር ማሰብ በአጓጉል ጉጉት እንድትንደረደሩ ያደርጋችሁና ከሚዛናዊነት ሊጋርዳችሁ ስለሚችል ጥቅማችሁን በሚገባ ካሰላችሁ በኋላ ውሳኔያችሁን ለመገምገም መነሳት ያለባችሁ ሊያስከትል ከሚችለው ችግር ወይም መዘዝ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመወሰን የሚረዷችሁን ሶስት ወሳኝ ነጥቦች አስፍሬላችኋለሁ፡-
1. የምትወስኑት ውሳኔ ትክክል ካልሆነ የሚያደርስባቸችሁ ጉዳት ከምክንያታዊነትና ከተጨባጭ ሁኔታ አንጻር እውን ከሆነ …
2. የሚደርስባችሁ ጉዳት ከአካል ጤንነት፣ ከስነ-ልቦና ቀውስ፣ ከከባድ የገንዘብ ክስረትና ከመሳሰሉት ከባባድ ሁኔታዎች ጋር የሚገናኝ ከሆነ …
3. በተሳሳተው ውሳያኔችሁ ምክንያት ከሚደረስባቸሁ ችግርና መዘዝ ለመውጣት ቢያንስ አንድ አመትና ከዚያ በላይ የሚፈጅባችሁ ከሆነና ከአመታት መባከንና ከእድሜ መበላት ጋር የሚገናኝ ከሆነ፡፡
ካለይ በተዘነዘሩትን የስሌት ሃሳቦች አንጻር ውሳኔያችሁ ተመዝኖ ሚዛን ካልደፋ ስለውሳኔያችሁ በሚገባ እንድታስቡበትና ብትችሉ ከእናንተ ከቀደሙ ብሱል ሰዎች ምክርን እንድትቀበሉ ልምከራችሁ::
ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ