ልጥፎች
Ethiopia
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ambachewmu3.blogspot.com> ብዙዎቻችን ትንቢቶችን ተረት ፣ የደብተራ ቅዠት ወዘተ ብለን ስናናቅ ነበር የከረምነው። ትንቢት አትናቁ። የአበውን ቃል አትናቁ። የኢትዮጵያ መፍትሔ ፦ የእግዚአብሔር መንገድ ነው። በእግዚአብሔር መንገድ ውስጥ እውነተኛ ሰላም ፣ ፍትህ ፣ ጥበብ እና ተስፋ አለ። አንዳንዴ በምናየው ልክ ነው የምናስበው። ያላየነው የህይወት ገፅታ ስላላየነው አይሆንም የለም ማለት አይደለም። አንዳንዶች አሻግረው ተመልክተው የተለያዩ ገፅታዎችን ይመለከታሉ። ይህ የብስለት ጉዳይ ነው። የመንፈስ ብስለት አንድም ደግሞ የነፍስ ንቃት እና ትጋት ውጤት ነው። ኢትዮጵያ ትንሳኤ አላት የላትም ንትርክ ውስጥ መግባት አያስፈልግም። ትንሳኤውን አሻግረው ለተመለከቱ ትንሳኤው በፈቃደ እግዚአብሔር ጊዜውን ጠብቆ ይገለጥላቸዋል። ኢትዮጵያ ትንሳኤ እንዳላት ማመን እጅና እግርህን አጥፈህ ተቀምጠህ ጠብቅ ማለትም አይደለም። ሁሉም ነገር የትጋት ውጤት ነው። ነጥቡ እንዴት ነው የምንተጋው ነው። ቅኝ ገዥዎችህ ባስተማሩህና በሰሩልህ የፓለቲካ ርእዮተ ዓለም ነው በጥንቱ የአባቶችህ በነዮቶር ስርአት ነው ለኢትዮጵያ የምትተጋው ??? በኢትዮጵያ ትንሳኤ የምናምነው ስራ ፈት ስለሆንን አይደለም። በቅዱሳት መፃሕፍት ፣ በቅዱሳን አባቶች ትንቢት እና በትውፊት ስለምናምን ነው። የኢትዮጵያን ትንሳኤ መጠበቅህ በእምነትህ ያጠነክርሃል እንጂ አያዝልህም። የዚህ ትንሳኤ መገለጥ ዝቅ የሚያደርጋቸው ስማዝያውያን (ሃያላን መንግሥታት) የኢትዮጵያ ትንሳኤ ሳይገለጥ ለማዳፈን እጅግ የረቀቁ ሴራዎችን አድብተው ሰርተዋል እየሰሩ ነው። ይህ ስልት አገር ውስጥ ባሉ የእናት ጡት ነካሾም የሚደገፍ ነው። አንዳንዶቹ ደግሞ በኢትዮጵያ ትንሳኤ ስም እየማሉ ከተዋህዶ ህዝቡን ሊለዩ የሚዳክሩትም የዛኑ ያህል ብዙ...
አማራ
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
እኔ ሰው ብቻ ነኝ፣ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ እኔ ስልጡን ነኝ፣እኔ ምሁር ነኝ ፣ እኔ ሀይማኖተኛ ነኝ፣ እኔ ፖለቲካ አልወድም፣ እኔ በራሴ ፍልስፍና ነው የምመራው" የሚሉት ባህሪያት እንደአማራ አንድ ላይ ቆመን በአማራነቱ የገጠውን ፈተና አማራዊ መልስ ስጥቶ ነፃ እንዳይወጣ ያደረገው #በአባ_ባህርይ ዘመን የነበረው #የባህሪይ _ውርስ ነው ማነህ የእኛን ያህል የተገፋህ? እኛ ማለት እኮ... ➔አሀዳዊያን ተብለን የምንወዳትን አገር እንጠላ ዘንድ ማለቂያ የለሽ ግፍ የተፈጸመብን፤ ➔ "አማራ የለም" ተብሎ በሚዲያ ሲወራ የሰማን፤ ➔ዜግነትም ሆነ ማንነት የለሽ ሕዝብ መሆናችንን የሚገልጽ መጽሐፍ ተጽፎ ያነበብን፤ ➔"ሕዝብ ሳትሆኑ መንግሥት ናችሁ" በሚል የትግል ማኒፌስቶ ድምጽ የለሽ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የተፈጸመብን፤ ➔አማራን የሚያንቋሽሹና የሚያጠለሹ ሚዲያዎች ሪሲቨራችን ላይ የተጫነብን፤ ➔"አማራ ጠላት ሕዝብ ነው" ብለው የሚያምኑ ድርጅቶች ጥምረት ፈጥረው ጦርነት ያወጁብን፤ ➔ያልያዝነውን ሥልጣን እናስረክብ ዘንዳ "ዳውን ዳውን" የተባልን፤ ➔በእነ አቦይ ስብሐት አንደበት "እንዳያንሰራሩ አድርገን ሰብረናቸዋል" የሚል ጥናት የቀረበብን፤ ➔በቋንቋችን የተሳደድን፣ በማንነታችን የተጠቃን፣ በአገራዊ ፍቅራችን የተጣላን፤ ደስ የሚለው ነገር ታዲያ ይሄን ሁሉ በዴል የፈጸመብንና ጠላት ያደራጀብን አሸባሪ "አማራ ላይ የማወራርደው ሒሳብ አለኝ" በሚል እብሪት ወረራ ፈጽሞ ከእግራችን ስር መውደቁ ነው። በጎጃም፣ በጎንደር፣ በሸዋ ምድር የሚኖረው አማራም ወሎ መሬት ላይ ተሰባስቦ "አንቀጥቅጨዋለሁ" ባለው ተራራ ላይ እንደ ወባ እያንዘፈዘፈው ነው። ታዲያ ይሄን ታሪካዊ ክስ...
30 የ ICT ቴክኒካዊ ስያሜዎች
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
30 የ ICT ቴክኒካዊ ስያሜዎች 1. #ጥቁር_መዝገብ (Blacklist) - በገዳቢ የክልከላ ፖሊሰ የታገዱ ድረ ገጾች እና ሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶች ዝርዝር ነው። 2. #ብሉቱዝ (Bluetooth) -ገመድ አልባ ከሞባይል እና ከባለመስመር ስልኮች በአጭር ርቀት ዳታ ለመላላክ የሚያስችል ገመድ የግንኙነት ደረጃ ነው። ቡሉቱዝ ዳታ ለመለዋወጥ አጭር ሞገዶችን ይጠቀማል 3. #ቡቲንግ (Booting) - ኮምፒውተርን ሥራ ማስጀመር ወይም ማስነሳት ነው። 4. #አቫስት (Avast) - ጸረ ቫይረስ መሣሪያ 5. #መሠረታዊ _የግብአት/ውጤት ሲስተም ሶፍትዌር (Basic Input/Output System-BIOS) -የኮምፒውተር ሶፍትዌር የመጀመሪያው እና መሠረታዊው ደረጃ ነው። ባዮስ የኮምፒውተራችንን ሐርድዌር ደኅንነት ለማረጋገጥ የሚረዱ የተለያዩ አማራጮችን ይሰጠናል፤ኮምፒውተራችን ሲከፈት በይለፍ ቃል ብቻ እንዲገባ ማድረግ ከእነዚህ አንዱ ነው። 6. #ሲክሊነር (CCleaner) - በነጻ የሚገኝ ሶፍትዌር ነው። በቅርብ በተጠቀምንባቸው ፕሮግራሞችና በዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲሰተም አማካኝነት በሐርድዌራችን ላይ የተተዉ ጊዜያዊ ፋይሎችን ዱካ የሚያሳዩ መረጃዎችን የሚያጸዳ ሶፍትዌር ነው። 7. #ሲዲ_በርነር (CD Burner) - በባዶ ሲዲዎች ላይ መረጃ ለመጻፍ የሚችል የኮምፒውተር ድራይቭ ነው።ዲቪዲ በርነር (DVD burners) በተመሳሳይ መንገድ በባዶ ዲቪዲዎች ላይ ይጽፋል።ሲዲ-አርደብሊው (CD-RW ) እና ዲቪዲ-አርደብሊውድራይቮች (DVD-RW drives) ደግሞ በሲዲ/ ዲቪዲ ላይ የተጻፈውን አጥፍተው ከአንድ ጊዜ በላይ መልሰው መጻፍ ይችላሉ። 8. #ሰርከምቬንሽን (Circumvention) - በኢንተርኔት አፈና የታገዱ ድረ ገጾችን እና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለማግኘት እገዳው...
Ethiopia
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ብዙ ዐዋቂዎች በጥቂት ታዋቂዎች በተዋጡባት ምድር ላይ እኖራለሁ፡፡ ብዙ ገንዘብ አልባ የአይምሮ ሐብታሞች በጥቂት የፈረንካ ባለጠጋ መሐይማን በተጋረዱባት ፕላኔት ላይ እገኛለሁ፡፡ ብዕር የጨበጡ፣ መጽሐፍ ያነገቡ ዐዋቂዎች፣ ብረት ባነገቡ፣ ሳንጃ በወደሩ ታዋቂዎች በተደፈጠጡባት ዓለም ላይ እዋኛለሁ፡፡ አደባባዩ በታዋቂዎች ግሪሳ ካፍ እስከገደፉ ተሞልቷል፡፡ ታዋቂዎች ሲያስነጥሱ እልፍኝ አላዋቂዎች “እግዚሐር ይማራችሁ!” ለማለት ወረፋ ይይዛሉ፡፡ ዐዋቂዎች ቢያልፉ ግን ቀባሪ እንኳ የላቸውም፤ የታዋቂዎች የቀትር ጥላ ጋርዷቸዋልና፡፡ መቅረዞቹ ጋን ተደፍቶባቸዋልና ብርሃናቸው ከጋናቸው ሊወጣ አልቻለም፡፡ ዐዋቂዎች ከጋናቸው ከወጡ ጥላቸው በታዋቂዎች ላይ ያርፍና ታዋቂዎችን ይጋርዳቸዋልና፡፡ ታዋቂነት ነግሦ ዐዋቂነት ተዋርዷል፡፡ አንድ ዐዋቂና ሌላ ታዋቂ ከአደባባይ ቢገኙ፤ ብዕርና ደብተር ለታዋቂው ይጎርፉለታል፤ ፊርማውን እንዲያኖርበት፡፡ጥበበኛም ይህን በማየት ሌላ ጥበብ ሌላ ዕውቀት ይጨምራል፣ እንዲህም ሲል ይቀኛል፣ “አላዋቂዎች የታዋቂዎችን ፊርማ ለምን ይሰበስባሉ?፣ ዕውቀት ሊገበዩበት ነው? . . . አይደለም፡፡ ጥበብ ሊገዙበት ነው? . . . አይደለም፡፡ ማስተዋል ሊያተርፉበት ነው? . . . አይደለም፡፡ አላዋቂዎች የታዋቂዎችን ፊርማ የሚሰበስቡት ታዋቂውን ለማወቃቸው በቂ መረጃ እንዲሆናቸው ነው፡፡ ዐላዋቂዎች ከዐዋቂዎች ዕውቀትን ባለመቅሰም ብቻ ሳይሆን፣ ታዋቂዎችንም በማወቅ ታዋቂ መሆን ይፈልጋሉ፡፡ የዚህች ምድር ክበብ በታዋቂዎች ሳይሆን በዐዋቂዎች ተመሥርቷል፡፡ የሚያሳዝነው ግን ዓለምን ዐዋቂዎች ሳይሆኑ ታዋቂዎች ይነዷታል፡፡ በዚህች ዓለም ላይ ከአንድ መሪ ነኝ እመራለሁ ባይ ታዋቂነት እንጂ ዕውቀት አይፈለግበትም፡፡ ቲፎዞ እንጂ ማስተዋል አይጠየቅበትም፡፡ እንዲያማ ባይሆን ...
ነገሩ ሁሉ እንደ ጥርስ ነው መሰል እህል ያላመጠበትን የመጀመሪያ ቀን የሚያስታውስ የለም።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ነገሩ ሁሉ እንደ ጥርስ ነው መሰል እህል ያላመጠበትን የመጀመሪያ ቀን የሚያስታውስ የለም። ለነገሩ እህል ከማላመጣችን በፊት የፈረደባትን የ'ናታችንን ጡት ነክሰናል.. በሁለት የፊት ጥርስ እና ድድ የጡት ጫፍን ቅርጭው ይዘን.. ሁሉም እናቶች እሰይ ልጄ ጥርስ አበቀለች ብለው እንዳልተደሰቱ በምስራቻቸው ተነክሰዋል... ያውም እስከሚደሙ **************************************** ይህ የራሴ ያገለገለኝ ንብረቴ ፡ ለሆነ አመት አፌ ሲከፈት ነጫጭ ሆኖ ተደርድሮ፡ ግጥም ብሎ አፌን ሞልቶ የልጅነት ቆንጆ ሳቅ አልፈጠረልኝም? ቆሎ ... ከቆሎም ሳይንገረገብ በደረቁ ጣ ጣ ጣ እያለ የተቆላ ሽንብራ አልከካሁበትም? መለልታ ከአንጓ ሳለይ ሸንኮራ አልመጠጥኩበትም? ይባስ ብዬ ተደብቄ እየሰረኩ ስኳር ቅሜ እየቆረጫጨምኩበት ይህ ጥርሴ እስኪቦረቦር ድረስ አንጀቴን በወለላ ጣዕም አላራስኩበትም? ይህ የልጅነት ጥርሴ ለምን ከእኔ ኖሮ ፡ ከእኔ እንዳልተፈጠረ በአመታት ውስጥ ነቅነቅ አለ? ለምን መነቃነቁ አሰጋኝ? ለምን ... ለምን ያ ቆሎም ቆንጥሮ ያቀበለ፡ ሸንኮራም ሸንሽኖ ያጎረሰ የገንዛ እጄ፡ የእጄ ጣቶች ከድዴ የተሰካን ጥርስ አነቃንቆ ለመንቀል ታገለ? እኔ በ እኔ አልተጣላንም? ያውም በልጅነቴ? ብተወዉ በስብሶ በሽታ፡ ብነቅለው - ክብር አሳጥቼ - ከቤቴም ደጃፍ አፈር ምሼ ሳልቀብረው፡ ደብቄ በትንሽ ብልቃጥ ሳላስቀምጠው... ይባስ ብዬ ወደ ጣርያ፡ ያውም አሻግሬ ለወፍ እና ለአይጥ ዘምሬ 'ያንቺን ለኔ የኔን ላንቺ' እያልኩ መወርወሬ.. ተሻግሮ ወይ በእኛ ቤት፡ ወይ በእነ አሹ ቤት ጣሪያ ቋ ብሎ መውደቁን፡ መጣሉን ሲያረጋግጥልኝ፡ አልያም አጥር ዘሎ በጎረቤት ተክል ወድቆ ፀ...ጥ። በመዳፌ አስቀምጬ ቢያሻኝ በሰው መሀል ጮክ ብዬ፡ ወይ በኔና በጥ...