እውነትን በግልጥ የማይናገር ሰው ሁከትን ይፈጥራል፣
በግልጥ የሚነቅፍ ግን ሰላም እንዲገኝ ያደርጋል፡፡
የደግ ሰው ንግግር የሕይወት ምንጭ ነው፣
የክፉ ሰው ንግግር ግን የዐመፅ መሸፈኛ ነው፡፡
ጥላቻ ሁከትን ያነሣሣል፣
ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ዐይታ በይቅርታ ታልፋለች፡፡ …
እውነትን በምትናገርበት ጊዜ ቅን ፍርድ ታደርጋለህ፣
ሀሰት ግን ፍርድ እንዲጓደል ያደርጋል፡፡
ያለ ጥንቃቄ የተነገረ ቃል እንደሰይፍ ያቆስላል፣
በጥበብ የተነገረ ቃል ግን ይፈውሳል፡፡
የሀሰት ዕድሜ አጭር ነው፣
እውነት ግን ለዘላለም ትኖራለች፡፡
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕ. 10 (10 – 12) – 12 (17-19)
A lie is an abomination unto the Lord and a
very present help in trouble. Adlai Stevenson
(1900 – 1965)
It is always the best policy to tell the truth,
unless, of course, you are an exceptionally
good liar. Jerome K. Jerome (1859 – 1927)
አንድ የብዕር ወዳጄ ሰሞኑን በድረ ገፆች ያወጣውን ጽሑፍ
በከፍተኛ አግራሞትና የተጻፈውን ለማመን ባለመፈለግ
ስሜትም ጭምር ካነበብኩ በኋላ ኢትዮጵያዊ ምሁር
ያሰናዳው ነው ብዬ መቀበል ስለተሳነኝ ወዳጄ መጣጥፉን
ለመጻፍ የተጠቀመበትን ኦሪጂናል የጥናት ሥራ አግኝቼ
በራሴው ለማንበብ ወሰንኩ – “From the horse’s
mouth” ትሉ የለም እናንተስ? የተባለውን መጽሐፍ ከጥቂት
ድካም በኋላ ከጓደኛ በውሰት አገኘሁ፡፡ ይህን የ230 ምናምን
ገጽ መጽሐፍ በ‹ፍቅር› ለማንበብ ብዙ ጊዜ አልወሰደብኝም –
እንደተባለውም የመጽሐፉ ዋነኛ ዓላማ ከመነሻው
እስከመድረሻው የሚያጠነጥነው በተስኪያን እንደገባች ውሻ
አማራን እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ አድርጎ በተገኘ ምናባዊ
መሣሪያ ሁሉ መቀጥቀጥ ነው – ፍርጃ እኮ ነው እናንተዬ፤
አሁንስ ይሄ አማራ የሚባል ብሔር ባይፈጠር በተሻለው፤
የጠብ ያለሽ በዳቦ ልክፍት የተጠናወተው ሁሉ አፍ ማሟሻና
የጭቃ ጅራፍ ብዕር የስድብ መለማመጃ ሆኖ ይቅር እንዴ?
ባይቆጭ ያንገበግብ ይባላል፡፡ ንባቤን እንደጨረስኩ
የተሰማኝን ስሜት ለመግለጽ ቃላት አጠሩኝ – እንዲህ ባለ
አጋጣሚ የቋንቋ ውሱንነትም ታወሰኝ፤ ለካንስ የከረረ ስሜትን
ለመግለጽ ቋንቋ ራሱም ይሰንፋል? አዎ፣ ሁኔታው አስደንጋጭ
ነው፡፡ በአንድ ሀገር ዜጎች መካከል እንዲህ ዓይነት አሣዛኝ
ሁኔታ መፈጠሩ ለደግ አይደለምና ከአሁኑ ይልቅ የወደፊቱ
እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው፡፡ ከመጠን ባለፈ ከመጨነቄም
የተነሳ “በርግጥ ይሄ ሰውዬ ጤናማ ይሆን? የውሸትን ድካና
ዳር ድንበርስ ያውቅ ይሆን? መጽሐፉን ለደህና ጓደኛ
ቢያሳይና አስተያየት ቢቀበል ኖሮ እኮ እርሱም ሆነ ድርጅቱ
ሕወሓት ከቅሌት ይድኑ ነበር!” በማለት በሰው ልጆች
አጠቃላይ የቁሣዊ ዓለም ግንዛቤና ከእውነት የራቀ አተያይ
ብዙ ተክዤ ቆየሁ፡፡ ያነበብኩት የመጽሐፉ ዕውነትና መሬት
ላይ ያለው ሀገራዊ እውነት አልገናዘብልኝ ብለው በሰዎች
የሁለት ዓለም ባሕርይ ክፉኛ መጠበብና መጨነቅ የያዘው
ሰውነቴ ወደአቅሉ እንዲመለስ ራሴን በራሴው ማጽናናት
ያዝኩ፡፡ ወዳጄ በጻፈው ጽሑፍ ላይ ሊገለጹ የሚገባቸው ነገር
ግን ያላጤናቸው ወይም በይሁንታ ያለፋቸው እጅግ በርካታ
የማያቀባብሩ ነጥቦች እንዳሉ መገንዘቤን ልደብቅ
አልፈልግም – ምናልባት ክፍተትን ይበልጥ ላለማስፋት አስቦ
ሊሆን ይችላል ብዬ ገምቻለሁ፡፡ ይሁንና አንዳንድ ነጥቦች
መገለጽ እንዳለባቸው አመንኩና ይህችን አጠር ያለች
ማስታወሻ ልጽፍ ወደድኩ፡፡
በዚህ አጋጣሚ መግለጽ የምፈልገው ነገር እውነትን
እንዳለች እንድንመለከት እግዚአብሔር ፈጣሪያችን
ሁላችንንም ልቦናና ብርታትን እንዲሰጠን ነው፡፡ እርግጥ ነው
ሕንዳዊው ደራሲ ናራያና እንዳለው እውነት እንደጠራራ ፀሐይ
ዐይንን ታጥበረብራለች፤ ብዙዎቻችን በቀጥታ ልናያት
አይቻለንም፡፡ እውነትን ደፍሮ መጋፈጥ የሚቻለው ሰው ብርቱ
ነው፡፡ የእውነት ጦር ከማንኛውም ሰው ሠራሽ መሣሪያ
የበለጠ ኅሊናን ይወጋል፡፡ ስለዚህም ነው በርካታዎቻችን
ይህችን እውነት አጥብቀን ስንሸሽ የምንስተዋለው፡፡ ሁሉም
ሰው የኅሊናው ባለቤት ቢሆን የምድራችን ቅርጽ ከአሁኑ
እጅግ ባማረ ሁኔታ የተለዬ በሆነ ነበር፡፡ ግን ዕድሜ ለዚህ
በተመሳሳይ ወቅት እየጠገበ ለሚርበው ሆድ ለጥቅም ሲባል
እውነት እንደክርስቶስ አላበሳዋ እየተወገረች፣ ሀሰት
ንግሥናንና ግርማ ሞገስን እያገኘች ዓለማችን ከምንጊዜውም
በላይ በሚያስደነግጥ የጥፋት ማዕበል እየተናጠች ልትገኝ
ችላለች፡፡
እውነትን አለመናገር አንድ ነገር ነው – ዝም ማለት፡፡ እውነትን
ለመደበቅ መጣርም አንድ ነገር ነው – ማስተባበል፡፡
የፈጠጠ እውነትን መካድና በፈጠራ የልቦለድ ሥራ መራር
እውነትን በውሸት ቡልኮ ለመሸፈን መሞከር ግን ሰው
የመሆንን ሥነ ተፈጥሮ የሚፈታተን ታላቅ ሰብኣዊና ሞራላዊ
ኪሣራ ነው፡፡ የዚያን መጽሐፍ ደራሲ ያገኘሁት እንግዲህ
ከሰውነት በታች ወርዶ፣ ከቀሪው የእንስሳት ዓለምም እጅግ
ዘቅጦ በሚያሳዝን የኅልውና ደረጃ ውስጥ ወድቆ በዓሣማ
ጋጣ የዘረኝነት አረንቋ ውስጥ ሲማስን ነው – ስንት ዓመት
ሊኖር? ሕወሓትንስ በዚህ ውሸቱ ጠቅሞ ስንት ዓመት
ሊያኖር? ከንቱነት ነው – እንደመጽሐፉ ንፋስን የመከተል
ያህል የከንቱ ከንቱ ነው የዚያ ሰው ልፋቱ፡፡ ወገኖቼ ናቸው
የሚላቸውን ቢያድላቸው ደግሞ የኛም ወገኖች ሊሆኑ
ይቻላቸው የነበሩ ሳይፈጠሩ ቢቀሩ የሚሻላቸው ወገኖችን
ወንጀልና የግፍ ቁልል ለመሸፈን የሚያደርገው ጥረት ራሱን
አጋልጦ የወንጀላቸው ተባባሪ ሊሆን እንደሚችል
እስክንጠራጠር ድረስ በዘረኝነት የጠባብነት ቁጢት ተተብትቦ
ወያኔዎች ያልሆኑትን እንደሆኑ ለማሳመን ቆላ ደጋ መራወጡን
ስናይ የምናዝነው ለኛ ለግፉኣኑ ብቻ ሳይሆን ለርሱና ለነርሱ
ሳይሞቱ ለሞቱት ወገኖቻችንም ጭምር ነው፡፡ አንዳንዴ
ሟችም ለገዳይ ማዘኑ የነበረና ተገቢም ነው፡፡ የሚገድልና
የሚዋሽ ሰው ወድዶ አይደለምና እውነትም ይበልጥ ማዘን
በሀሰት ሚዛን እየመዘነ፣ በሀሰተኛ ምላስ እየፈረደ ንጹሓንን
ለሚያጠፋ ነው፡፡ ሰው በጤናው ሰውን አይገድልም፤ ሰው
በጤናው አይዋሽም፤ ሰው በጤናው መጥፎ ድርጊት ውስጥ
አይገባም፡፡ አንድ ሰው የሆነ ሥነ አእምሮኣዊ ወይም ሥነ
ልቦናዊ ችግር ውስጥ ካልተዘፈቀ በስተቀር ከመሬት ተነስቶ
ሰው አይዘልፍም ወይም አይገድልም፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰው
ሕክምና እንዲያገኝና ፈጣሪ ከእሥራቱ እንዲፈታው
ቢጸለይለት በረከት ያስገኛል እንጂ ክፋት የለውም፡፡
ስለዚህም ዐውቀውም ይሁን ሳውቁ ለጠፉ ወንድምና
እህቶቻችን በጋራ እንጸልይላቸው፤ ከዚህ ሰው ጽሑፍ ተነስቼ
ልል የምችለው ቀዳሚ ነገር ይህንን ነው፡፡
‹ባልዋሽ፣ባልገድል፣ዝም ብል፣… ይህን ወይ ያን ጥቅምና
ሥልጣን ላጣ እችላለሁ፡፡› ብሎ የሚያስብም የምኞቱ ባሪያ
ሆኖ ወደ ወንጀል ዓለም እየገባ ነውና ሊታዘንለትና ሊጸለይለት
ይገባል፡፡ እንጂ በመሠረቱማ የሰው ልጅ ሁሉ አንድ ነው –
ልዩነታችን ጥፋታችንና ልማታችን፡፡ በጥፋታችን እንጠፋፋለን፤
በልማታችን በሀብት እንበለጽጋለን፤በአስተሳሰብና
በአመለካከትም እናድጋለን፡፡ ይህን ዕድል የሚያሳጡንን
ታዲያን በጋራ እንታገላቸው፡፡ በዘረኝነት መታወር፣ በትምክህት
መወጠር፣በዕብሪት መጀነን፣ በዕውቀት መደኽየት፣ በራስ
ወዳድነት ልክፍት መጠፍነግ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ክርስቶስ “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ያለው
በገንዘብና በሥልጣን ፍቅር ላበዱ ለዚያኛው ዘመን
አይሁዳውያን ወያኔዎች ብቻ አይደለም፡፡ ለተገነዘበው
ለሁሉም ዘመን የሚሠራ ታላቅ አስተምህሮ አለው፡፡ የሞት
ፈጣሪ በፍጡራኑ ሲሰቃይ፣ ሲገረፍ፣ ምራቅ እየተተፋበትና
በእሾህ አክሊል እየተፌዘበት እስከስቅላት ደርሶ የሞትን ጽዋ
ሲጎነጭ እነዚያን ወያኔዎች ቀርቶ ዓለምን ከናካቴው ሊያጠፋ
የሚችል ኃይል አጥቶ አልነበረም፡፡ እንደመጽሐፉ ያ ሁሉ
የሆነው ታዲያ እንዲሆን ግድ ስለነበረ ነው፡፡ ይህም ዘመን
እንዲያልፍ ግድ ነውና በወያኔዎች ዐይን ያወጣ የብልግና
ሥራ ብዙም አንደነቅ፡፡ በቅድመ ትንበያ (predestination)
ለምናምን አንዳንድ ወገኖች ይህ ሁሉ አብራቅዳብራ
እንደሚከሰት – ወቅቱን በትክክል ባናውቅም – የቀደመ
ግንዘቤ ነበረን፡፡ አይሆኑም የሚባሉ ነገሮች የሚሆኑበት
አጋጣሚ ሞልቷል፡፡ በድምሩ ከ18ሚ. የዓለም ሕዝብ የወጡ
በጣ የሚቆጠሩ ፅዮናውያን የሰባት ቢሊዮንን ሕዝብ ዕጣ
ፋንታ፣ በድምሩ ከአምስት ሚሊዮን ሕዝብ የወጡ ‹ጥቂት›
የትግሬ ገዢዎች የ85 ሚሊዮን ሕዝብ ዕጣ ፋንታ ይወስናሉ
ብሎ በሰው ልጅ አእምሮ ማሰብ የሚቻል አይደለም፡፡ ነገር
ግን ይሁን ያለው ከመሆን አይዘልምና እየተገረሙ የዓለምን
አካሄድ በትዝብት ከመቃኘት በስተቀር ምንም ማድረግ
አይቻለንም፡፡ በብሂልህ “ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ
ይሰብራል” ትል የለም? ወደህ ተሰደድህ? ወደህ ትራባለህ?
ወደህ ሀገር አልባ ትሆናለህ? አብዛኞቹ የዓለም ቢሌነሮች
እነማን ናቸው? የዓለምን ትልቅ ሥልጣን በእጅ አዙርና
በቀጥታ የተቆጣጠሩት እነማን ናቸው? ወዴት እየነዱህ ነው?
ወደ ጥፋ ወይንስ ወደ ልዕልና? በኢትዮጵያስ ያንን ዓለም
አቀፍ ነፀብራቅ ቁልጭ ብሎ እያየኸው አይደለምን? ዘመኑ
የጥቂቶች ነው ወዳጄ ልቤ፡፡ ሁሉን ቢያወሩት ሆድ ባዶ
ይቀራል፡፡
እንደውነቱ ውሸት የሚናገር ሰው በሥቃይ ውስጥ ያለ ነው፡፡
እውነትን የሚናገር ሰው ግን በሥቃይ ውስጥ ላለመኖር
የቆረጠ ሰው ነው፡፡ እውነትን በመናገር ብዙ ነገር እናጣለን፡፡
ከቅርብ ጓደኛና ዘመድ ጀምሮ የምናጣው ብዙ ነገር ነው –
በዓለማዊ አስተሳሰብ
መብል፣መጠጥ፣ድሎት፣ሥልጣን፣ፍቅረኛንና የትዳር
አጣማሪን ሳይቀር ብዙ ነገሮችን ልናጣ እንችላለን፡፡ ሀሰት
መታወቂያዋ በሆነ ዓለም ውስጥ ስንኖር እውነትን ለመናገር
ከቆረጥን እንደዕብድ ልንቆጠርና በውግዘት ከአካባቢና
ከማኅበረሰብም ጭምር ልንገለል እንችላለን – ያኔ
ሃይማኖት፣ ባህል፣ ወግና ልማድ የተባለው ይበልጡን
በውሸት የተቃኘው ማኅበራዊ ሥርዓት ሁሉ ይከዳህና ከሕገ
ወጦቹ ጋር ሲወግንብህ መግቢያ ቀዳዳ ታጣለህ – ደግሞም
ያኔ የምትኖርባት ዓለም የሀሰት እንጂ የእውነት መገለጫ
እንዳልሆነች ትረዳና አንድም ታብዳለህ አንድም ትመንናለህ
አለዚያም በ‹ኩኑ ከማሆሙ› ሥጋዊ መርህ የቆሻሻው ዓለም
ባልደረባ ሆነህ አንተም በተራህ እንዳሻህ ትመላለስበታለህ፡፡
እከክ የሰጠ ጥፍር አይነሳምና ምርጫዎች አሉህ፡፡
ለሚያምኑበት እውነት መርዝን በድፍረት የጨለጡና የድንጋይ
ውርጅብኝ በውዱ ገላቸው ያስተናገዱ እንዲሁም በስቅላት
ያሸለቡ ሞልተዋል – ዕንቁን የላይና የታች ልጅ ክርስቶስን
ጨምሮ፡፡ በጥቃቅን የሃሳብ ልዩነት – ለምሳሌ በመሬት ቅርጽ
– ሳይቀር በሞት የተቀጡ አሉ – አሁንም ለቆሙለት እውነት
ሲሉ፡፡ ካለመስዋዕትነት ድል እንደሌለ ተገንዘበን በእውነት
መንገድ ከተጓዝን በመጨረሻው እውነት ራሷ ትክሰናለች –
አለበለዚያ ትከሰናለች፡፡
ሀሰት የሚናገር ሰው እውነት የሌለው ወይም የሚታወቅን
እውነት በመናገሩ ምክንያት አንዳች ነገር አጣለሁ ብሎ
የሚያምን ሰው ነው ማለት ይቻላል፡፡ ወያኔዎችና እበላ ባይ
ወይም የዓላማ ደጋፊ ጸሐፊያነ ትዕዛዞቻቸው የይሉኝታን ገመድ
በጣጥሰው ጥለው ነጭ ውሸቶችን በመክተብ ሥራ ላይ
የተጠመዱበት ምክንያት ካልዋሹ በስተቀር የያዙትን ቦታ
እንደሚለቁ ስለሚያውቁ ነው፡፡ የሚይዙት ካርድ ሁሉ
ያሟልጫል፡- ዴሞክራሲ ቢሉ ንዑሳን በመሆናቸውና
ከጥንትም በደምና በአጥንት ተረማምደው በመምጣታቸው
ምናልባትና በዛ ቢባል ከ6 በመቶ የሀገሪቱ ሕዝብ የበለጠ
የሚመርጣቸው እንደሌለ ያውቃሉና በዚያ ድጋፍ
በማይገኝበት የዴሞክራሲ መንገድ ሊጓዙ አያስቡትም –
ይህንንም እውነት ጃዝ ብለው ያሠማሯቸው ወገኖች
ያውቃሉ፣ በተጨባጭም አይተውታል፡፡ ጨቋኝም ሆነው
እንደቀደምቱ ነገሥታትና ወታደራዊው መንግሥት ጉልበትንና
ዘዴን ተጠቅመው እንዳይቀጥሉ ከዜጎች ብቻ ሳይሆን
ከመሬቱና ከዛፍ ቅጠሉ ተጣልተዋልና ያም አያዋጣም፡፡
ብሔርን ከብሔር ፣ ቡድንን ከቡድን፣ ሰውን ከሰው፣ባልን
ከሚስት … እያናከሱ ዕድሜን መቀጠሉም ከአሁን በኋላ
የሚሠራ አይመስልም፡፡ ያላቸው ብቸኛ አማራጭ በኃይል
ረግጦና በውሸት ወሬ አደንቁሮ የተቻላቸውን ያህል ርቀት
መጓዝ ነው፡፡ ስለወያኔዎች የብዙዎቻችን እውነት ይሄው
ይመስለኛል፡፡
ይህ ዓለምሰገድ አሰፋ በተባለ ግለሰብ የተጻፈ ጥናታዊ
የተባለ መጽሐፍ የአማርኛ ተናጋሪውን ማኅበረሰብ አፈር ድሜ
ለማስጋጥና የሰሜኑን ሕዝብ በተለይም የኤርትራንና ትግራይን
የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ማኅበረሰብ በታሪክም በሥነ ልቦናም
በሃይማኖትም ያላቸውን ነባር ትስስር አጉልቶ በማውጣት
ከሌሎች የኢትዮጵያ ዜጎች ይልቅ እኚህ ወንድሞቻችንና
እህቶቻችን ጥንት የነበራቸውንና አሁን ሊኖራቸው የሚገባውን
የበላይነትና ሥልጣኔያዊ ገናናነት ለማሳየት ያደረገው ጥረት
ከፍተኛ ነው(በእርሱ ጥናት መሠረት ከድላቸው በኋላ ጥብቅ
የነበረው የግንኙነት ፈትል በመላላቱ ሳቢያ ትግራይ
በኢትዮጵያዊነት ስትጸና ከመረብ ማዶ ያለው ግዛት
በኤርትራነቱ እንደፀና በፀፀት መሰል ቃና ይገልጻል)፡፡ ቀጣዩን
እንይ፡-
Once in the seat of power in Addis Ababa, the
ethnic card is being aborted at a fast rate to
such an extent that even the Tigrayan features
of the regime are fading almost completely. A
new national army with no ethnic character has
been created. Except for the premiership and
foreign ministry, all cabinet posts are held by
non-Tigrayans. Even key posts such as
defense, judiciary, and police are held by non-
Tigrayans. In other words, the rational political
actors led a costly ethnic nationalist war in
Tigray without being ethnic nationalists
themselves. For the Tigrayan rational actors,
therefore, Marxism was their raison d’etre and
ethnic rationalism their means to an end. And
ethnic nationalism was a politics of power.
ተዛማጅ ትርጉም፡- [ሕወሓቶች] አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ
ከ1983ዓ.ም በኋላ በትግሉ ዘመን ይጠቀሙበት የነበረው
የጠባብ ብሔርተኝነት የትግል ሥልት በኅብረ ብሔራዊ
የአንዲት ሀገር ሉዓላዊ ስሜት ወዲያው በፍጥነት በመተካቱ
በመንግሥት መዋቅሩ ውስጥ ‹ለመሆኑ በዚህ መንግሥት
ውስጥ ትግሬ ሥልጣን ላይ አለ እንዴ?› እስኪባል ድረስ
የኢትዮጵያ መንግሥት ከትግሬዎች ተፅዕኖ ሙሉ በሙሉ ነጻ
ወጣ (ከ1983ዓ.ም በኋላ!)፡፡ ዘውገኝነት ያልተንፀባረቀበት
ብሔራዊ የመከላከያ ጦርም በጎሣ ተዋፅዖ ሣይሆን በብቃት
መለኪያ መሥፈርት መሠረት ተመሠረተ፡፡ ከጠቅላይ
ሚኒስትርና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታዎች በስተቀር
ሁሉም የካቢኔ ሚኒስትሮች ቦታዎች ትግሬ ባልሆኑ ዜጎች
ተያዙ፡፡ [Please feel free to laugh, guys!] ሌላው
ቀርቶ አሸናፊ አማፂ ማንንም አምኖ የማይሰጣቸው
የመከላከያ፣ የፍትህና የፖሊስ ዕዞች በሙሉ ትግሬ ያልሆኑ
ዜጎች እንዲይዟቸው ተደረጉ፡፡ በሌላ አባባል ሕወሓቶች
በተፈጥሯቸው የሌለባቸውን የጎሠኝነት ወይም የጠባብ
ብሔርተኝነት ባሕርይ እንደጊዜያዊ ሥልት በመጠቀም
ትግላቸውን በከፍተኛ መስዋዕትነት ከግብ ካደረሱ በኋላ
ሥልጣኑን ላልታገሉ ዜጎች አስረከቡ(ና እነሱ ባዶኣቸውን ቀሩ
– ሣቅ/ሣቂ ፤ ዛሬና አሁን ያልሣቅን መቼ ልንስቅ ጎበዝ?)፡፡
ስለዚህም ለትግራውያኑ ተጋዳላዮች ለእውነተኛ የትግላቸው
ጅማሮ ዋና አመክንዮ ማርክሲዝም ሆኖ እንደመታገያ ሥልት
ግን ጠባብ ብሔርተኝነትን ወይም ዘውገኝነትን ተጠቀሙበት
(እንጂ እነሱማ ኧረ ንሽ እቴ! ዘውገኛነት በሉት ጎጠኝነት
አሊያም ነፍጠኝነት ሲያልፉ አይነኳቸውም፡፡) እናም ሕወሓቶች
ጠባብ ብሔርተኝነትን ለሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ የሥልጣን
ማረጋገጫነት ተገለገሉበት እንጂ በተፈጥሯዊ ባሕርያቸው
ዴሞክራቶች ናቸው፡፡
መንግሥቱ ኃ/ማርያምን በሁለት ውሸቶቹ ዘወትር
አስታውሰዋለሁ – “እውን አሁን ደርግ አለ?” አንድ በሉ፤ “እኔ
እንኳንስ ሰው ትንኝ አልገደልኩም!” ሁለት በሉ ( በነገራችን
ላይ ከደቂቃዎች በፊት ‘Talk to Aljazeera’ ላይ
በእንግድነት የቀረበ ኑር ሚሷሪ የተባለ አንድ ፊሊፒናዊ
የቀድሞ አማፂ ቡድን መሪ ጋዜጠኛዋ ‹ራስህ ሰው ገድለህ
ታውቃለህ ወይ?› ብላ ስትጠይቀው ‹እንኳን ሰው ጉንዳንም
ገድዬ አላውቅ› ብሎ ሲመልስላት መንግሥቱ ፊቴ ላይ ድቅን
አለብኝ – ሰውዬው ውሸታም ነው ለማለት ፈልጌ ግን
አይደለም – ስለማላውቀው፡፡) መንግሥቱንና ወያኔን መሰል
አምባገነኖች በአደባባይ የሚያደርጉትን ሁሉ ‹ዐይኔን ግምባር
ያ’ርገው› ብለው ሽምጥጥ ማድረግ የባህርይ ስጦታቸው
ነው፡፡ ኢትዮጵያ ባላት የተመናመነ ኢኮኖሚ ያስተማረችው፣
በእናቱ የጭንቅ ቀንም በፈለገችው ጊዜ የደረሰላት ይህ
‹ምሁር› የሚለውን እንቶ ፈንቶ ‹እውነት ነው፤ ውሸት ነው›
ብሎ መከራከር ጉንጭን ማልፋትና በጊዜም መቀለድ ነው፡፡
ጽሑፉ ራሱ ብዙ ይናገራልና፡፡ እዚህ ላይ ከመጽሐፉ ብዙ
መጥቀስ በተቻለ፤ ግን ይብስ ሆድ ማስባስ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ‹በሀሰት አትመስክር፤ የባልንጀራህን
የጎረቤትህንም ገንዘብና ሚስቱንም አትመኝ፤
አትስረቅ፣ጓደኛህን እንደራስህ ውደድ፣ … › ይላል፡፡
የዓለምሰገድ ሃይማኖት ክርስትና ነው ብዬ ለማመን
እቸገራለሁ፡፡ በእስልምናም ‹ዋሽ› የሚል ቁርኣናዊ ጥቅስ
ይኖራል ብዬ ስለማልገምት ሙስሊም አይሆንም ባይ ነኝ፡፡
በአይሁድ ሃይማኖትም እንዲሁ ውሸትን የሚያበረታታ
የታልሙድም ይሁን የታናክ ወይም የቶራ ጥቅስ ይኖራል
የሚል ሃሳብ የለኝም፡፡ የዚህ ሰውዬ እምነት እንግዲህ –
እርሱ ተቀበለውም አልተቀበለውም – ምናልባት በማንኛውም
መንገድ በ‹የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው›ም በሉት
በ‹The end justifies the means.› የሥጋ
ፍላጎቶቻቸውን ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ
ከማይሉት የቤተ ሣጥናኤል (Church of Satan)
አምላኪዎች ጋር የሚመሳሰል ወይም የሚነባበር መሆን
አለበት – ሊያውም ከነሱም መካከል የ‹አትድረሱብን
አንደርስባችሁም› ዓይነት የመከባበር መርህ የሚከተሉ
‹ጨዋዎች› አሉ፡፡ አንድ ኢአማኒ(ኤቲይስት) ጓደኛ አለኝ –
እንዲያውም ከአንድ በላይ፡፡ በሞራሉና በማኅበራዊ ግንኙነቱ
በጣም ጨዋና ሰውን በቸገረው የሚረዳ ደግ ነው –
altruist፡፡ ሃይማኖት የለኝም ብሎ አይዋሽም አይቀጥፍም፡፡
ጽድቅና ኩነኔ የሉም ብሎ ማመኑ ልክ እንደዚህ ሰውዬ
ቆርጠህ ቀጥል የሆነ ውሸታም እንዲሆን አላደረገውም፡፡
የዚህ ሰውዬ ውሸት ግን የተለዬ ነው፡፡ ፍላጎቱ ግልጽ ነው –
ልክ እንደ‹ፕሮፌሰር› ክንፈ አብርሃም የትግራዩ ገዢ መደብ
በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያሳረፈውንና እያሣረፈ ያለውን
የማይፋቅ ጠባሳ በዓይጥ ምሥክር ድንቢጥ የሀሰት
ምሥክርነት ጽድቅና ለማሰጠት ነው፡፡ እውነቱን ከፈጣሪ
ቀጥሎ ዓለምና የኢትዮጵያ ሕዝብ እያወቀው ለመዋሸት
ይህን ያህል ርቀት መጓዝ ከትዝብት ሌላ እንደማይኖር እነዚህ
ሀሰተኛ የዲያብሎስ አሽከሮች ሊረዱት በተገባቸው ነበር፡፡ ግን
ያሳዝናል ኅሊናቸው በዘረኝነት ልክፍት የታወረ በመሆኑ
እውነት ታጥበረብራቸዋለችና የሚሠሩት ህፀፅ ሊታያቸው
አልቻለም፡፡ ነገ ጧት የነጻነት ጎሕ ሲቀድ ልጆቻቸውና የልጅ
ልጆቻው ሲያፍሩበት በአሳቻ ቦታ ተጥሎ ውሻና እሪያ
የሚሸናት አፅማቸው እንደሚታዘባቸው መገንዘብ ነበረባቸው፡፡
እዘህ ላይ ማለት የምፈልገው ነገር የቀድሞ መንግሥታት
በነዓለምሰገድ ሥሌት ምንም ይባሉ ምን፣ ምንም ይሁኑ ምን
የሠሩት ስህተት አሁን ለሚሠራው ሌላ ስህተት መሠረትና
ድጋፍ ሊሆን እንደማይችል ማወቅ የሚገባን መሆኑን ነው፡፡
ዱሮ ዘመኑ የዕውቀት አልነበረም እንበልና የዱሮውን ስህተት
አምነን እንቀበል፡፡ “Every argument has two sides.”
ከሚለው ማለፊያ ነጥብ አኳያ የታሪክ አጻጻፍ ግነትም
ግድፈትም ሊኖረው መቻሉን በታሳቢነት ይዘን ዓለምሰገድም
ሆነ መሰል ፀረ – አማራና በተያያዥነትም ፀረ-ኢትዮጵያ ጥናት
አጥኚዎች በአማራው ‹ገዢ መደብ› ላይ የሚደፈድፉት
ኃጢያት እውነት እንደሆነ በሙሉ ልብ እንቀበልላቸው፡፡
እንዲያም አመንንላቸውና አማራ ትግሬን ጨቁኗል፤ ትግራይንና
ኤርትራን ዘርፎ ጎንደርንና ሸዋን፣ ጎጃምንና ወሎን ፋብሪካ
በፋብሪካ፣ ትምህርት ቤት በትምህርት ቤት፣ ዩኒቨርስቲ
በዩኒቨርስቲ፣ አስፋልት በአስፋልት፣… አድርጓል – ይሁን ብለን
እንመን – ማመን አይገድም፡፡ በሌላም በኩል በማወቅ
ወይም ባለማወቅ ብዙ የጭካኔና የአረመኔ ተግባር የፈጸሙ
አማሮች ነበሩ፣ አሁንም በአስተሳሰባቸው ከሞቱት በላይ
ከቆሙት በታች የሆኑ ከወያኔዎች የማይሻሉ ከንቱ አማሮች
ሊኖሩ እንደሚችሉ እንመን፤ እናምናለንም፡፡ የሀገር ግንባታና
ልማዳዊ የግዛት አስተዳደር ጉዳይ ሂደታዊ ነውና በተለይ
በዱሮ ዘመን ጥፋት አይኖርም ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው –
እነጋሪባልዲም 38 ብጥስጣሽ የጣሊያን ግዛቶችን
አስተባብረው ነው ታላቅ ሀገር የፈጠሩት፡፡ ይህ ክስተት
ለኢትዮጵያ ሲሆን ነውር ለወያኔና ለሌላው ሲሆን ጽድቅ ሊሆን
አይገባም፤ አይችልምም፡፡ ደርግ የወደቀው በአበባ በታኝ
የሠርግ አጃቢዎች ሣይሆን በሬሣ ላይ እየተረማመዱ
በመጡ፣ በትግርኛ ፕሮግራማቸው ‹ዘራፍ! አማራ ገዳይ! አህያ
ገዳይ! አማራ ፈሪ ነው – እንዳትለቀው› እያሉ በወሎና ሸዋ
የዋህ አማሮች መንገድ አመላካችነት በተመሙ ማይማን
የሀሽሽ ሰለባ ጦረኞችና በሕዝብ ኩርፊያ መሆኑን ልብ
ይሏል፡፡ ሌሎች ተጓዳኝ ሻጥሮችና ዓለም አቀፍ ሤራዎች …
ሳይዘነጉ፡፡ እውነት እንደፀሐይ ስለምታጥበረብር የምለው
ነገር የሚጎመዝዘው ቢኖር ልረዳው አልችልም – (አማርኛ
ተናጋሪ የሆናችሁ – በአማራነት የተፈረጃችሁ ወይም
ራሳችሁን የፈረጃችሁ ወገኖች በምንም መንገድ አትናደዱ –
በቀል የፈጣሪ እንጂ የሰው አይደለችምና ኅሊናችሁን ንጹሕ
አድርጋችሁ ወደላይ ጩኹ፤ ክፉ ብታስቡ ያ ክፋት ወደራሳችሁ
ይዞራልና እንዲያውም ክፉን ለሚያደርጉባችሁ ፍቅራችሁን
አሳዩዋቸው – አደራ)፡፡ እውነትን መናገር ሀሰትን ከመናገር
ቢከብድም ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ በበኩሌ አህያ ጥሩ
አገልጋይ ስለሆነች ይህ ስም ሲበዛብኝ እንጂ አያንሰኝም፤
አይከፋኝምም፡፡ ስለዚህ ዕድሜ ለወያኔዎቹና – የጠቤን
ምህዳር ላስፋው ይሆን? አይ፣ ይቅርብኝ – ለማንኛውም ጥሩ
የዳቦ ስም አለኝ፡፡ ‹አንድ ጣትህን ወደሰው ስትቀስር ሦስቱ
ወዳንተ መዞራቸውን አስተውል› ይባላል፡፡ የኛንም ‹ቁስል›
ማሳየቱ ነውር አይደለም ከሚል የዋህነት ነው አለወትሮየ
እንዲህ የምል – በዚያ ላይ ዓለምሰገድ ብቻውን ‹ስለኛ›
መናገር አይገባውም – እኔም ‹ስለነሱ› ላግዘው፡፡ እርግጥ
ነው – ሁሉም እንደምንጭ ውኃ ኩልል ብሎ የሚጠራበት
ጊዜ ይመጣል – የእስከያኔውና የእስከዛሬው ድፍርስ ነበር፡፡
ከአሁን በኋላ ግን ሁኔታዎች እየከረሩ የሚሄዱበት ወቅት ላይ
የደረስን ይመስለኛል፡፡ ይህችን ሀገር እግዚአብሔር
ባይጠብቃት ኖሮ ይሄኔ ከሦርያም ብሰን ነበር፡፡ ፈጣሪ ጓዙን
ጠቅልሎ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለ ማመን አለብን፡፡
ያልተላለቅነውና ውለን የምንገባው በኪነ ጥበቡ እንጂ
በወያኔ ቸርነትና ጥበቃ አይደለም፡፡ ለነገሩ ሰው በስንቱ
ሊበደል ይችላል?
ለማንኛውም ጥቂት ከፍ ሲል በጀመርነው ተጠየቅ መሠረት
በቀድሞ ዘመን የተሠራው መጥፎ ነገር ሁሉ የታሪክ ስህተት
ነውና ቀጣዩ የታሪክ ተረካቢ ነባሩን ስህተት አስተካክሎ
በፍትህ ይገዛል ብለን በጉጉት እንጠብቅ፡፡ ከ17 ዓመታት
የደርግ የግፍ አገዛዝ በኋላ በቆዬ የቦካ ቂም ክራሩን በአዲስ
የበቀል አንቺሆዬ ቃኝቶ ለሌላ የተነጣጠረ ዕልቂት ያላለመ
መንግሥት ጠበቅን እንበል፡፡ አልቀረም መጣ‹ልን›፡፡
ግንቦት 20 ቀን 1983ዓ.ም፡፡
ቀጣዩ የታሪክ ባቡር በትግሬዎች እጅ ወደቀ፡፡ ምን ተፈጸመ?
የ‹አማሮች› ስህተት ተደገመ ወይንስ ተስተካክሎ ዕንባ ታበሰ፣
የሚፈስ ደምስ ደረቀ? ‹አማራው› ያስለቀሳቸው ወገኖች
ጭቁኑን አማራ ጨምሮ አለፈላቸው? የታወጀላቸው ራስን
በራስ የማስተዳደር ዴሞክራሲያዊ ባህል ሠፈነላቸው? የዚያ
ሁሉ መስዋዕትነት ዋጋ ምን አመጣ? ለሌላ አዙሪት የሚዳርግ
ስህተት እየተሠራ ነው ወይንስ ፍትህ ሰፍኖ ሁሉንም ያማከለ
ልማት ተዘረጋ? ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ተጀመረ
ወይንስ ተሠሩ የተባሉ ስህተቶች ታርመው ፍትህና ርትዕ
ነገሡ? ጥያቄውም መልሱም ከማንም የተሠወረ አይደለም፡፡
‹ተቀልዷል፣ ተቀልዷል፣ተቀልዷል› በሚል አዝማች አንዲት
ዘፋኝ ያቀነቀነችው ሥልት ትዝ አለኝ፡፡…
የሚመለከታችሁ ወገኖች በአስቸኳይ ከአማራ ራስ ውረዱ!!
‹አማራ› አጥፍቷል፤ እውነት ነው፡፡ አጠፉ የተባሉት አማሮች
ግን ብቻቸውን አልነበሩም፤ ዘመኑም እጅግ ሩቅ ነው፡፡
የመንግሥት ሥልጣን ይዛችኋል – ሌላው ወገናችሁ ብዙ
ጊዜ እናንተንና ፈጣሪን አንጋጥጦ ጠበቀ፡፡ በስቃይ እየኖረ
እንደክርስቶስ ኤሎሄ እያለ ነው፡፡ የጸሎቱ ዳፋ ግን ለማንም
ምሕረት የማይኖረው እንደሚሆን እንረዳ፡፡ እውነትን
እንነጋገር፡- የዘረኝነትን አጥር በአመዛዛኝ የዕውቀት ቁልፋቸው
ከፍተው ለጋራ ሕይወት ከሚታገሉ በጥቂት ሺዎች የሚገመቱ
የትግራይ ተወላጆች ውጪ አብዛኛው ትግራዋይ ለወያኔ
የማይራራ ልብ አለው ማለት ስለሚከብድ የሕዝቡ መራቆት
ይሰማንና ነገን ሳንጠብቅ የሚመርም ቢሆን መድሓኒት ገዝተን
ዛሬውኑ እንዋጥና ‹በኛ ይብቃ!› እንበል፤ ለልጆቻችን
መርገምት አናስተላልፍ፡፡ የማስተካከል ወርቃማ ዕድል
በበራችሁ ተኝታ ስትማጸናችሁ እናንተ ሳታስተውሏት ይሄውና
22 ዓመታት ላይመለሱ ነጎዱ፡፡ አታሞ እርግጥ ነው በሰው
እጅ ታምራለች – የማደናገር ዕዳው ሲይዟት ነው፡፡
በኢትዮጵያ ከሞላ ጎደል ሁሉም የሥልጣን ቦታዎች ላይ
አለችሎታቸውና አለዕውቀታቸው – በዘውጋዊ ታማኝነታቸው
ብቻ የተቀመጡ ሌሎችን ግን የሚያባርሩና አልፎ ተርፎም
በአሸባሪነት እየከሰሱ ወህኒ የሚያወርዱ የገዢው መደብ
አባላት ወደየኅሊናቸው በአፋጣኝ ይመለሱ፡፡ ጊዜ የለም፡፡
ፅዋው ሞልቷል፡፡ ከአሁን በኋላ ምርጫው ሁለት ነው፤ አንዱ
አካሄድን ማስተካከልና ልክ እንደደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ዕርቅ
ማውረድ፡፡ ሁለተኛው የእናቴ መቀነት አሰናከለኝን መተውና
ወያኔዎች በድንቁርናቸውና በዕብሪታቸው ያበላሹት – ዐፈር
ላይ ጥለው አለመላው ያርመጠመጡት ዋልጌያዊ
የመንግሥት ሥልጣን አያያዝ የሚያመጣውን የማይቀር ዕዳ
ለመቀበል መዘጋጀት፡፡ ከዚያ በተረፈ “በምኒልክ የደነቆረ፣
‹ምኒልክ ይሙት› እያለ ሲምል ይኖራል” እንደሚባለው
የአማራን ስም እንደውዳሤ ማርያም ቀን ከሌት እየደገሙ
አበሳን ማብዛት የራሷን ምስል በመስትዋት ውስጥ ተመልክታ
‹አምላኬ ሆይ፣ እንኳንስ እንደዚህች ዓይነት አስጠሊታ ፍጡር
አላደረግኸኝ!› ብላ እንደጸለየችው ዝንጀሮ መሆን ነው፡፡ ጀሮ
ያለው ይስማ፤ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ፀጉር ስንጠቃ
አርማጌዴዖንን አያስቀርም፡፡ ጉራና ትዕቢትም ወንዝ ቀርቶ
የደረቀ ፈፋን አያሻግርም – ሲያመጣው፡፡
ይህን የምለው አንዱ ጻዲቅ ሌላው ኃጥዕ ሆኖ አይደለም፡፡
ነገር ግን የእግዚአብሔር ሚዛን እንደሰው ሚዛን
ስለማይቀላምድ በሆነው ነገርና እየሆነ ባለው ነገር መካከል
ያለውን ልዩነት ተመልክተን የመጪውን ጊዜ ይዞታ ስንገምት
በአማራ ላይ የደረሰው ቅጣት ከወይራ ጥብጣብ ወይም
ከለበቅ የሚወዳደር እንጂ በአሁኖቹ ቀብራራ ገዢዎች ሊደርስ
ካለው ጋር በምንም መንገድ እንደማይቀራረብ ለመጠቆም
ነው – የነብርንና የሚዳቋን የ‹አሁን ብበላህ ምን እሆናለሁ?›
ምሣሌያዊ ብሂል አስታውሱ፤ ሁልጊዜ ጌትነትም የለም፤
በፋሲካ የገባች ገረድ ፍልሰታ እንደምትመጣ ካላወቀች ገልቱ
ናት – እርግጥ ነው ፋሲካና ፍልሰታ ርቀት አላቸው –
ቢሆንም … ፡፡ በበኩሌ ሁለት ነገር አስባለሁ – አንድም ያንን
የፍርድ ቀን ፈጣሪየ ባያሳየኝ፣ አንድም ያንን የፍርድ ቀን
ፈጣሪዬ አድርሶ ቢያሳየኝ፡፡ ምርጫው የርሱ ይሁንልኝ፡፡
ከአያያዝ ይቀደዳል፤ ከአነጋገር ይፈረዳል – ቀኑን እዩት ፤ ቀኑ
ደርሷል! የዘመኑን መቅረብ ለመረዳት ደግሞ በግድ ቆዳ
ታጥቆ አንበጣ እየበላ በበረሃ የሚሰብክ ሰው መጠበቅ
አይገባንም፡፡
የዘሩት መብቀሉ፣ የበቀለ መታጨዱና ተወቅቶ ጎተራ መግባቱ
አይቀርም፡፡ ሼክስፒር ‹ትልቅ ደግ ነገር ለመሥራት ትንሽ
መጥፎ ነገር መሥራት ምንም አይደለም› ይል ነበር አሉ፡፡
በኢትዮጵያ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን የስሙኒ ዶሮ
የሚሊዮን ብሩን የወርቅ ገመድ ይዛ እየጠፋች ተቸግረናል፡፡
የአንዲት ክፍለ ሀገር ጥቂት መኳንንትን ሁለንተናዊ ርሀብ
ለማስታገስና የጥቂት ሚሊዮን ዜጎችን ሥነ ልቦናዊ የገዢነት
እርካታ እውን ለማድረግ የተከፈለው መስዋዕትነትና
የወደመው ሀብትና ንብረት አሥራ አራቱንም የቀድሞ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛቶች ሕዝብ ቁጭ አድርጎ ለአሠርት
ዓመታት ይቀልብ ነበር፡፡ ነገር ግን የፊተኞቹም ሞኞች፣
የአሁኖቹም ለከት ያጡ ብልጦች ሆኑና በመካከሉ ሀገርና
ሕዝብ ለማያባራ የሲዖል እሳት ተዳርገው መቅኖ አጥተው
ቀሩ፡፡ ደግነቱ ግን ይህም ያልፋል፡፡
በዚያ ላይ ትልቁ ችግር የሆነብን ኅሊናን የሚሠቀጥጥ ውሸት
እየተለቀቀብን ፈረንጆቹ በ‹MC› (Mind Control)
በሳተላይት የተደገፉ ሥውር የአእምሮ መቆጣጠሪያ
ፕሮጄክቶቻቸው ዜጎቻቸውን በኤሌክትሮኒክስ ጨረሮች
እንደሚያነሆልሏቸው ሁሉ የኛ የገዢው መደብ ምሁራን
ተብዬዎችም እንዳቅሚቱ ያቺን የMC/PR የምትመስል
የሕዝብ ግንኙነት ሥራ መሥራታቸው ነው፡፡ ቂሎች ናቸው፡፡
በእንደዚህ ዓይነት የሞኝነት ሥራ ገብተው ሊዋረዱ
አይገባቸውም ነበር – የውርደትን ምንነት ቢያውቁ፡፡ ዝምታ
ማንን ገደለ? ምንም ሳይናገሩ የታሪክ ባቡር ወስዶ አንዱ
ሥርቻውስጥ እስኪቀረቅራቸው ድረስ ዕድል የሰጠቻቸውን
ሲሳይ ድምጻቸውን አጥፍተው እንደለመዱት እዬዘረፉ
ቢከፋፈሉ ማን ምን ያደርጋቸዋል? ልፉ ብሏቸው እንጂ ዋሹ
አልዋሹ፣ የፈጠራ ድርሰት ጻፉ አልጻፉ ያላሰቧት ዕድል
እንደሆነች በደጃቸው ከትማለችና የመጥፎ ሥራቸው የዞረ
ድምር መቅሰፍቱን እስኪያዘንብባቸው ድረስ አርፈው
መቀመጥ ይችላሉ፡፡ መንቀዥቀዥ ሳያስፈልጋቸው አሁን
እያደረጉ ያሉትን ሁሉ እያደረጉ መኖር ‹ጉልበታቸው›
የሰጣቸው መብታቸው ነው፡፡ ናፖሊዮንንና ሂትለርን የመሰሉ
አባ ጉልቤዎችም ብለዋል:- “Mighty is right”.
አስተዋይ ሰው ከቆመው ብቻ ሣይሆን ከወደቀውና
ከተቀመጠውም ብዙ ይማራል፡፡ ስህተትን በስህተት ቢደግም
ራሱም ቀኑን ጠብቆ እንደሚወድቅ ይገነዘባል፡፡ ትናንትን ከዛሬ፣
ዛሬንም ከነገ በማገናዘብ ለአለውና ለመጪው ትውልድ
መልካም ነገሮችን ቀይሶ ያልፋል፡፡ እናም ወያኔዎች ወድቋል፤
ተቀብሯል ያሉት አማራ እንግዲያውስ ለምን ወደቀ? ብለው
አዙረው ማየት ነበረባቸው እንጂ በ‹ብጥለው ገለበጠኝ›
የመሠሪነት ባሕርይ ታሪክ አፍ አውጥቶ እስኪታዘባቸው ድረስ
እንዲህ ባልተጃጃሉ ነበር፡፡ ሌላውን ሁሉ ትተን ጣልነው
ያሉትን የጣሉት በኢፍትሃዊነት ተፈጥሮው ስለተጓዘ እንደሆነ
አምነው ሳይሆን ለሀብትና ለሥልጣን በነበራቸው ጉጉት
ያስመስልባቸዋል፡፡ ይሄ ሁሉ የስም ማጥፋት ዘመቻም
ስለፍትህ በመጨነቅ ሳይሆን ለግላዊ ጥቅምና ለሥልጣን
ጥም እርካታ መሆኑን ያሳብቅባቸዋል፡፡
ኢፍትሃዊነት እነሱን ወልዶና አሳድጎ ራሱን ኢፍትሃዊነትን
ካጠፋ የነሱ ኢፍትሃዊነት ሌላ አካል ወልዶና አሳድጎ የነሱን
መረን የለቀቀ ኢፍትሃዊ አገዛዝ ሊያጠፋ እንደሚችል እንዴት
ሊገነዘቡ አይችሉም? ምን ዓይነት ተፈጥሯዊ ‹intrinsically
in-built› ድንቁርና ይሆን እነዚህን ወንድሞቻችንን
የተጣባቸው? አፄ ኃ/ሥላሴ ለምን ወደቁ? ደርግ ለምን
ወደቀ? ሂትለር ለምን ተዋርዶ ሞተ? ጋዳፊ ከ42 ዓመታት
በኋላ ከነባረያ ፈንጋይ ሥርዓቱ ለምን ተገረሠሠ? የደቡብ
አፍሪካ የጥቂቶች የአፓርታይድ አገዛዝ ብዙ ጥፋትና ውድመት
ካደረሰ በኋላም ቢሆን ለምን ወደቀ? (ነጮቹ ከጠቅላላው
ሕዝብ 6 በመቶ እንደሆኑ ይነገራል) ሆስኒ ሙባረክ ለምን
ተዋረደ? ጨቋኙ አላዊት ባሽር አላሳድ ለምን ሰሞኑን
ይወድቃል? … እነዚህ የትግሬ ገዢዎች ከዚህ ሁሉ ዓለም
አቀፍ የአሁንና የጥንት ኹነቶች ትምህርት ሊቀስሙ
ያልቻሉበትና በመዥገራዊ የዘረኝነት አባዜ እንደተለከፉ
የማርጀታቸው ምክንያት ምን ሊሆን እንደሚችል ሲታሰብ
በእጅጉ ይገርማል፡፡ ለመሆኑ ‹የክፋት ዕድሜ እስከ ስንት
ሊሆን ይችላል? የዱባ ጥጋብስ ዕድሜው ስንት ነው – ምን
ያህል ዳገቶችንስ ያስወጣል? …› ብለው ጥቂት ማሰላሰል
እንዴት አቃታቸው? ታሞ የተነሣ ፈጣሪን ረሳ ማለት እንግዲህ
እዚህ ላይ ነው፡፡ ይወቁት – አማራ በቡድንና በማኅበረሰብ
ደረጃ የማንም ጠላት አልነበረም፤አይደለም፤አይሆንምም፡፡
ግን ግን በስሙ የነገዱ ሆዳምና ራስ ወዳድ አማሮችና ሌሎች
ዘውጎችም ነበሩ፡፡ ሴትዮዋ “ዕድሌ ሆኖ ፈሴ ይሸታል”
እንዳለችው ባለቤት የታጣላቸው ታሪካዊ ስህተቶች ሳይቀሩ
በአማራው እየተላከኩ ይህን ምሥኪን ሕዝብ በኢትዮጵያና
በ‹ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ› ዘንድ እንዲጠላ ሙከራ ይደረጋል
እንጂ አሁን ቆም ብለን ወደኋላ ብናይ አማራ ሠራው የተባለው
ነውር የአሁኑ የብዔልዘቡል መንግሥት ከሠራውና እየሠራው
ካለው ነውር ጋር ሲወዳደር ልዩነቱ በአንድ ኩሬና ከአሥር
በላይ በሚገመቱ ውቅያኖሦች የሚመሰል ነው፡፡ ለአፍ አቀበት
ስለሌለው ግን ጆሮ አይሰማው የለምና የእምዬን ወደአብዬ
ሲያላክኩ አፋችንን በሀፍረት እየተመተምን መስማትን
ቀጥለናል – እስከ አንድ ቀን ድረስ፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ