#risingethio
አይሰው
🔑ራቁትክን ትወለዳለህ፤ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ 🔑 በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ፤ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ። 🔐የሕይወትን ትግል እየዳህ ትጀምራለህ፤ አጎንብሰህ ትጨርሳለህ፡፡ 🌍ዘመንም ተምኔታዊ ነው፡፡ 🌅መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሃል፤ ሠኞ ማክሠኞ ብለህ ተጉዘህ፤ እንደገና ሠኞ ትላለህ፡፡ እናም ሕይወት አዙሪት ናት! 🌽መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው፤የጀመርክበትን አትርሳ፤ መጨረሻህ ነውና፡፡የጀመርክበትን አትናቀው፤ ትጨርስበታለህና፡፡ ተራ ሠው ሆነህ ትጀምራለህ፤ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምርም፤ ነግደህ ሃብት ብታገኝ፤ ተሹመህ በሕዝብ ላይ ብትሠለጥን፤ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ፤ የምትጨርሠው እንደተራ ሠው አፈር ለብሠህ ነው
ምላሽ ይስጡሰርዝYour Publisher ID:
pub-3901521692965434