ልጥፎች

ከማርች, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ተስፋ

.ተሰፋ አንቆርጥም...(ሳሙኤል አዳነ) ውሀ በፈረቃ ፣ መብራት በፈረቃ፣ ስልጣን በፈረቃ ፣ ላገር ሲታደሉ ፣ ውሀ አጣጭ ፈለጋ መብራት ጠፋ ብለሽ ፣ ከባለ ስልጣን ጋር ትዞሪያለሽ አሉ ። ይሁና .. ውሀ የመጣለት ... ገላዬን ታጥቤ፣ ልብሴን አሳጥቤ ፣ ስልጣንም ካገኘሁ ፣ እሱን ተረክቤ መብራትም ይመጣና፣ በግዙፍ አዳራሽ ሰርጌን አከብራለሁ ፣ ብትመጭ አታጭኝም ፣ ግን አታገቢኝም ፣ ካሁኑ ሄጃለሁ ። እናም የዛንለት ... በእጣ ፈንታችን መንግስት እንወቅሳለን ፣ ሀገር እንከሳለን፣ ቆይቶ..ቆይቶ..ቆይቶ.. ጩህታችን ሰምሮ ፣ በሌላ ፈረቃ እንገናኛለን ። ተሰፋ አንቆርጥም 12/09/2011 ከጧቱ 12:00 ሰአት መብራት ሳይጠፋ

የእንግሊዝ ዲፕሎማሲ

#የእንግሊዝ_ዲፕሎማሲ_መበላሸት ጥቅምት 29፣ 1854 ላይ አጼ ቴዎድሮስ ሁለት ተመሳሳይ ደብዳቤወችን ለእንግሊዟ ንግስት ቪክቶሪያና ለፈረንሳዩ ናፖሊዮን ሳልሳዊ ላኩ። የደብዳቤያቸው ፍሬ ነገር የቱርኮች በኢትዮጵያ ግዛት መኖርን የሚቃወምና እነርሱን ከኢትዮጵያ ምድር ለማባረር ድጋፍ እንዲሰጡ ነበር።[83] ደብዳቤው በ1854 የእንግሊዝ ቆንጽላ በኢትዮጵያ ተብሎ በተሾመው ካፕቴን ካሜሮን አማካኘት የተላከ ነበር። በዚሁ ደብዳቤ ንጉሠ ነገሥቱ ጆን ቤልና ዋልተር ፕላውዴን ለንጉሱ የገቡትን ቃል አስታውሶ ንግስት ቪክቶሪያ የንጉስ "ታላቅ ንግስት" እንደሆነችና "የክርስቲያኖች ወዳጅ" እንደሆነች ያስታውሳል።[83] በዚህ ምክንያት እንግሊዝን እንደሚወዱ በደብዳቤው አስፍረዋል።[83] ከዚህ በተጨማሪ የቱርኮች በኢትዮጵያ ባህር ወደብ ላይ መንሰራፋት በቀይ ባህርል ላይ ጉዞ እንዳያደርጉ የሚከለክልና አምባሳደርም እንዳይልኩ ያደረጋቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።[84] ጥር 12፣ 1854 ላይ የቴዎድሮስ ደብዳቤ ለንድን ቢደረሰም።[84] የታቀደውን አላማ አልፈጸመም። ለዚህ ምክንያቱ ሩሲያውያን የእንግሊዝን የህንድ ግዛት መገዳደራቸው ነበር።[84] ስለሆነም እንግሊዝ ሩሲያን በጠላትነት ፈርጃ ክሩሲያ ጠላቶች -ከቱርኮች ጋር የጠበቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማድረግ ሩሲያን አንድ ላይ የሚታገሉበት ወቅት ነበር።[84] ስለሆነም የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መሰሪያ ቤት ለቴዎድሮስ ደብዳቤ መልስ እንኳ ሳይጽፍ እንዲሁ በተመላሽ ደብዳቤውን ለእንግሊዝ ወኪል በህንድ ላከ።[84] የህንዱም መስሪያ ቤት ደብዳቤውን ወደ ጎን ከማስቀመጥ ውጭ መልስ አልላከም ነበር።[84] በዚያው አመት ሚያዚያ 1854 ካፒቴን ካሜሮን ክእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ጸሃፊ ኸርል ረስል በደረሰው ደብዳቤ የእን...

ታጠቅ

ምስል
#ዓጼ ቴወድሮስ የቋራ አስተዳዳሪ የነበሩት ደጃዝማች ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደ ጊዮርጊስ (ባጭሩ ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ) ልጅ ናቸው። እናታቸው ወይዘሮ አትጠገብ ወንድበወሰን ሲባሉ አመጣጣቸውም ከጎንደር ከተማ ባላባቶች ነበር። የወይዘሮ አትጠገብ እናት ወይዘሮ ትሻል ስትባል የበጌምድር ክፍል መሳፍንት ዘር ነበረች፣ በአባቷ በኩል አያቷ ራስ ወዳጆ በዘመናቸው ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው ባላባት ነበሩ። የወይዘሮ አትጠገብ ድህነት በታሪክ መጻህፍት በተደጋጋሚ የሚጠቀስ ቢሆንም አመጣጡ እንዲህ ነበር፡ የህጻኑ ቴወድሮስ አባት ደጃች ሃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ ከሱዳኖች ጋር በተነሳ ጦርነት በጀግንነት ሲወድቁ እናት ገና ሁለት አመት የሆነውን ልጇን ይዛ ከቋራ ወደ ጎንደር ከተማ ሄደች። በዚህ ወቅት ሁለተኛ ላታገባ በመቁረብ ልጇን ብቻዋን ማሳደግ ግድ አላት። አንዳንዶች በዚህ ምክንያት እራሷን ለማስተዳደር ኮሶ ትሸጥ ነበር ሲሉ ጸሃፊው ጳውሎስ ኞኞ ወይዘሮ አትጠገብ መቼውንም ኮሶ አትሸጥም ነበር ይላል (ኮሶ ትሸጥ ነበር የሚለው የልጁ ጠላቶች ፈጠራ ወሬ ነበር በማለት ያስረዳል)። ሆኖም ቀረ ህጻኑ ቴወድሮስ በድህነት እንዳላደገ ሁሉም የታሪክ ጸሃፊያን ይስማማሉ። አንድ ለናቱ ቴወድሮስ በእናቱ በኩል እህትም ሆነ ወንድም አልነበረውም። የወደፊቱ አጼ ቴዎድሮስ በ፲፰፻፴፱ ዓ.ም. ተዋበች አሊ የተባለችውን የዘመነ መሳፍንት ታላቅ ባላባት፣ የራስ አሊ አሉላን፣ ልጅ አገባ። ተዋበች በጊዜው የ፲፭ ዓመት ወጣት የነበረች ሲሆን ቁንጅናዋና አስተሳሰቡዋ በጊዜው በነበሩ ሰወች ዘንድ የተደነቀ ነበር። ሁለቱ በፍቅር በመውደቃቸው ቴወድሮስ በአባቷ ራስ አሊና በአያቷ እቴጌ መነን ላይ ሲያምጽ ባሏን ትደግፍ ነበር። አጼ ቴወድሮስ የሚስታቸውን መታመም ከዘመቻ መልስ በ፲፰፻፵፰ ዓ.ም ላይ ከሰሙ በኋላ እቴጌ ተዋበች...

ቴወድሮስ

ምስል
#ቴዎድሮስ_ቀደምት_የተንሰራፋውን_የባሪያ_ንግድ_ስርዓት ያጠቃ ንጉስ ነበር ። በዚህ ወቅት ባሪያ መሸጥም ሆነ መለወጥ እንዲሁም ማጓጓዝን የሚያግዱ ብዙ ድንጋጌወችን ንጉሱ በማወጅ ቀደምት የባርነት ስርዓት ተቃዋሚ ንጉስ ሆነ። ለምሳሌ ጎጃም፣ ባሶ ውስጥ ባደረገው ዘመቻ በገበያው የተገኙ ባሪያወችን በነጻ ለቋል። ወሎ ውስጥ የተማረኩ ባሪያወች እንዳይሸጡ አግዷል።ሆኖም ግን ከህጉ ውጭ በኮንትሮባንድ ውስጥ ለውስጥ በአገሪቷ ዳርቻወች ባሪያ መሸጡና መለወጡ አላቆመም። #ከባህል አንጻር የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ንጉሥ ዘመን ማደግና መሻሻል አሳይቷል። ከፍተኛው የመንግስት ስራ በአማርኛ ይካሄድ ነበር። ዜና መዋእላቸውን በአማርኛ ለመጀሚርያ ጊዜ ያስጻፉ ንጉሥ ነበሩ።]፣ ከዚህ በፊት በግዕዝ ነበር። ከዚህ በኋላ አማርኛ የአገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ ሆነ።ቴዎድሮስ ከግዕዝ ይልቅ ሰወች በሚረዱት አማርኛ መጽሃፍ ቅዱስ እንዲተረጎም አደርጉ። #የመጀመሪያው_የጂዖግራፊያ መጽሃፍ በአማርኛ የታተመውም በኒሁ ንጉስ ዘመን ነበር። # ህዝቡ ለጋብቻ ከፍተኛ ዋጋ እንዲሰጥም በጣም ጥረት አድርገዋል፣ እራሳቸውም በአንድ ሴት በመወሰን መሪ ምሳሌ ለመሆን ሞክረዋል።  #ከቴዎድሮስ በፊት ይሰራበት የነበረውን ከወገብ በላይ እራቁት መሆን የአለባበስ ዘዴን በማስቀረት ሹሞች በጥሩ ሁኔታ እንዲለብሱ አድርገዋል። በአጠቃላይ ህዝቡ የሃይማኖትና የባህል ህጎችን አጥብቆ እንዲከተል ጥረት አድርገዋል። #ከአስተዳደር ስልት አንጻር ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ እስከፈጸሙት ድረስ የነበረውን አገሪቱን በማዕከላዊ ሃይል የማስተዳደር ስራ ጀምረዋል። በአዲሱ ስርዓት መሰረት የግብር እና የፍርድ ባለስልጣናት ከማዕከላዊ መንግስት ደመወዛቸውን እንዲያገኙ ተደረገ፣ ይህም በየቦታው የነበሩ ባላባቶችን የመፍለጥ የመቁረጥ ሃይል የቀነሰ ተግ...

ድንጋይ እንዴት ስድብ ይሆናል?

ጤና ይስጥልኝ # ድንጋይ_እንዴት_ስድብ_ይሆናል? ambachew44 ከሰሜን እስከ ደቡብ ያለውን የኢትዮጵያውያንን አንድነትስ ቢሆን ከድንጋይ በተሻለ ማን ይመሰክረዋል፡፡ አንድ ሰው እንዳ ለው «እስክስታ እና ድንጋይን ያህል የኢትዮጵያን ሕዝቦች አንድነት የሚያሳይ ባሕላዊ ገጽታ የለም»፡፡ ትግራይ ላይ ከወደ አንገት እና ትከሻ የጀመረው እስክስታ፣ አገው እና አማራ ላይ ሲደርስ አንገትን ከትከሻ ያያይዝና፤ ኦሮሚያ ላይ አንገትን ፣ ትከሻን እና ወገብን ከእጅ እንቅስቃሴ ጋር ያዛምዳል፡፡ ወላይታ እና ሐድያ ላይ ሲወርድ ደግሞ ወገብን ታክኮ ወደ ዳሌ ዝቅ ይላል፡፡ ከዚያም ደቡብ ጫፍ ሐመሮች ላይ ሲገባ እስክስታው በእግር ይጨርሳል፡፡ ያኔም ኢትዮጵያ አንድ ሰው ሆና ትታያለች ማለት ነው፡ ድንጋይም እንዲሁ ነው፡፡ ከሰሜን አኩስም እስከ ባሌ ተራሮች፣ ከምዕራብ ኦጋዴን እስከ አሶሳ፣ ኢትዮጵያ በታሪካዊ የድንጋይ ሐውልቶች የተሞላች ናት፡፡ በጣም የሚገርመው ደግሞ እነዚህ የድንጋይ ሐውልቶች ከመቃብር እና ከታሪካዊ ሁነቶች ጋር የተያያዙ መሆናቸው ነው፡፡  የአኩስም ሐውልት በታላላቅ የአኩስም ነገሥታት መቃብር ላይ መታሰቢያ ሆኖ ቆሟል፡፡ ከአዲስ አበባ ደቡብ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ጀምሮ በሲዳማ፣ ወላይታ፣ ሐድያ፣ ስልጤ፣ ከምባታ፣ በሰሜን በአዋሳ ሐይቅ፣ በምዕራብ ደግሞ በአባያ ሐይቅ ተከብቦ የሚገኘውና ከ150 በላይ ታሪካዊ ሥፍራዎችን የያዘው የድንጋይ ሐውልቶች ስብስብ፣ እንደ ሰሜኑ ሁሉ የመቃብር ሥፍራዎችን እና ታሪካዊ ሁነቶችን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ በኦሮሚያ ክልል በተለይም በአርሲ እና ባሌ የምናገኛቸው ሐውልቶችም ይህንኑ የሰሜን እና ደቡብ እሴት ተጋርተው፣ አንድነታችንንም መስክረው ይሄው ዛሬም ይታያሉ ድንጋይ ሥልጣኔያችንን ብቻ ሳይሆን ጀግንነታችንንም ሲመሰክር የኖረ ነው...

Africa

ምስል
# አውሮፓ_🇪🇺_እና #አሜሪካ _የእኛን_ገንዘብ_እስከተቆጣጠሩ_ድረስ_ኢኮኖሚያችንን_ይቆጣጠራሉ -እኛ የምንፈልገው በዶላር ወይም በዩሮ ሳይሆን በሀብቶቻችን የሚደገፈው የአፍሪካ የጋራ ገንዘብ ነው ፡፡ ግን እኛ የምንፈልጋቸውን የፈለግነውን ለመጠየቅ የውጭ ምንዛሪ (ምንዛራቸው) የምንፈልግ ከሆነ ለምን እኛ ደግሞ እነሱ የሚፈልጉትን እኛ ለመፈለግ የውጭ ምንዛሪ (የእኛ ምንዛሬ) ለምን አያስፈልጉም? እኛ የውጭ ምንዛሬ እንፈልጋለን ፣ እነሱ የእኛን ዋጋ ይፈልጋሉ ፡፡ የእነሱ ወረቀት የበለጠ ዋጋ ያለው ወይም በእሴታችን ሀብቶች እና ሸቀጦች ላይ እኩል ዋጋ ያለው ነው ብለን እንድናስብ በፕሮግራም ተይዘናል ፡፡ የእኛ ወረቀት ግን ለሀብቶቻቸው እና ለሸቀጦቻቸው ዋጋ የለውም የእኛ የኢኮኖሚ አስተዳደር ቡድኖች መረዳት የጀመሩት ፣ ምንም ያህል ሀብታችን በአስተያየታቸው በዓይናቸው ቢታይም ፣ ዋጋ ቢስ ስለሆኑ በእኛ ምንዛሬዎች መሸጥ አለባቸው ፡፡ በሌሎች ምንዛሬዎች እንዲሸጡ መፍቀድ ማለት በጭራሽ ምንም ዋጋ እንዳላቸው አናውቅም ማለት ነው ፡፡ As long as Europe 🇪🇺 and America 🇺🇸 Control our Money, they will Control our Economy: We need an African Common Currency backed by our Resources not by Dollar or by Euro Africa may never be able to build any of the prosperous economies we built in the past because we are nearly working entirely to support the economies of others while every value we have on our land is made to be taken away for free....

አድዋ

#risingethio https://Facebook.com/risingethiop https://twitter.com/ambachew44 https://imstagram.com/ambachew44 https://telegram.com/ambachew44 https://facebook.com/mulernews

አድዋ

ምስል
በአድዋ ማግስት የሮማ ጳጳስ ልመና ለእምዬ ምኒልክ ! 💚💛❤ በጣም ኃያል ለሆኑት ምኒልክ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ ሰላምና ገናናነት ለርስዎ ይሁን። ዛሬ አንድ ንጉሳዊ ልግስና እንዲያደርጉ የምክር ቃላችንን ክርስቲያናዊና ንጉሳዊ ለሆነው ልብዎ ለመላክ አሰብን። ይህ ድል ብዙ ምርኮኞች በእጅዎ ጥሎልዎታል። እነዚህ ምርኮዎች በወጣትነት ዘመን የኑሮኣቸው ተስፋ ባበበትና የብርሃን ጎህ በቀደደበት ሰዓት ከአገራቸው ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው ይገኛሉ። የነርሱ ምርኮ የግርማዊነትዎን ዝናና ገናናነት ምንም ሊያስፋፋው አይችልም። ይልቅ የምርኮ ዘመን ጊዜ በረዘመ መጠን በሺህ የሚቆጠሩት ቤተሰቦቻቸው የመንፈስ ሀዘን እየበዛ ሄዷል። ከእየሱስ ክርስቶስ በተቀበልነው የተቀደሰ መልእክት እንደ ልጆቻችን እንወዳቸዋለን። ስለዚህ ያንድ ልብ በቅድስት ስላሴ በተባረከችይቱ ድንግል ወይም ከዚህ ዓለም በሚወዱት ስም የሚያቀርብልዎትን ልመና ይቀበሉና ሳይዘገዩ ነፃነታቸውን ይስጡዋቸው። ኃያሉ ንጉሠ ነገስት ሆይ ይኽን የደግነት ስራ ባለመስራት እምቢታዎን ባለም ነገስታት ዐይን ፊት አይግለፁ። በወንድማማችነት እና በሰብአዊ ተግባር አንፃር ያለው የጦር መብትዎ ምንድን ነው የዚህን ብድር ርኀሩኅ አባት እግዚያብሔር በብዙ ይክስዎታል። ይህን ክብር ያላትን ደብዳቤ በመንግስትዎ ዜና መዋዕል ያስመዝግቧት። እስከዚያው ለንጉሳዊ ቤተሰብ እግዚያብሔር በረከት እንዲያወርድ እንለምናለን። ሮማ ቅዱስ ጴጥሮስ ግንቦት 11 ቀን 1896 ዓ.ም በ19ኛው ዘመነ ጵጵስና ተፃፈ ዋቢ፦ አፄ ምኒሊክና የኢትዮጵያ አንድነት The day after Adwa, the Pope's request to Menelik! 💚💛❤ To the most powerful Menelik Emperor Zeitopia Peace and prosp...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ 125ኛውን የዐድዋ ድል በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ መልዕክት ቀጥሎ ይቀርባል፡፡ እንኳን ለ125ኛው የዐድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የዐድዋ ድል የኢትዮጵያውያን የጀግነት፣ የሀገር ፍቅር ስሜትና የጦርነት ጥበብ ውጤት ነው። ጎራዴ ታጥቆ መድፈኛን ለመጣል ከመንደርደር የበለጠ ጀግንነት የለም። ልዩነትን ወደ ጎን ጥሎ በጋራ ለአንድ ሀገር ግንባርን ለባሩድ፣ አንገትን ለካራ ከማቅረብ በላይ የጠለቀ የሀገር ፍቅር ከየትም አይመጣም። ሰፊ ጊዜ ወስዶ ራሱን በሴራና በስትራቴጂ ሲያዘጋጅ እና ከሌሎች በሚያገኘው እገዛ ሲደራጅ የከረመ ኃይልን ጥቃት መክቶ መልሶ በማጥቃት ማሸነፍ በቀላል ብልሃት የሚሆን አይደለም። በደምና በላብ የወዛ፣ በሥጋና በአጥንት የቆመ፣ በጥበብና በመደመር የደመቀ የዐድዋ ድላችንን እኛ ለኢትዮጵያውያን የተለየ ትርጉም ሰጥተን እንድናከብረው የሚያደርጉን ብዙ ምክንያቶች አሉ። ከእነዚህ መሐል አንዱ፥ የዐድዋ ድል ሀገራችንን ማንም ሊያወርዳት ከማይችልበት ከፍታ ላይ የሰቀላት በመሆኑ ነው። ሀገራችንን ከዚህ ከፍታ ላይ ገፍትሮ ለመጣል ባለፉት ብዙ ዘመናት አያሌ ጥረቶች ተደርገዋል። በቅርቡ ታሪካችንም እንዲሁ። ግን አልተቻለም። ኢትዮጵያን ለመከፋፈልና ለማለያየት፣ ለማበጣበጥና ለማባላት፣ የተደረጉት ሙከራዎች ሁሉ የከሸፉት በዚህ የተነሣ ነው። ዐድዋ በከፍታ ላይ ከሰቀላቸው የኢትዮጵያ ዕሴቶች አንዱ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ነው። ከምዕራብና ከምሥራቅ፣ ከሰሜንና ከደቡብ የዘመቱ፤ በሃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በባህል፣ በመልክና በሞያ ኅብር የሆኑ፤ ነገር ግን ኢትዮጵያን ከቅኝ ግዛት የማዳን የአንድነት ዓላማ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ያስገኙት ድል ነው። በዐድዋ ዘመቻ ከ10 ዓመት ሕጻን...