አማራ
እኔ ሰው ብቻ ነኝ፣ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ እኔ ስልጡን ነኝ፣እኔ ምሁር ነኝ ፣ እኔ ሀይማኖተኛ ነኝ፣ እኔ ፖለቲካ አልወድም፣ እኔ በራሴ ፍልስፍና ነው የምመራው" የሚሉት ባህሪያት እንደአማራ አንድ ላይ ቆመን በአማራነቱ የገጠውን ፈተና አማራዊ መልስ ስጥቶ ነፃ እንዳይወጣ ያደረገው #በአባ_ባህርይ ዘመን የነበረው #የባህሪይ _ውርስ ነው ማነህ የእኛን ያህል የተገፋህ? እኛ ማለት እኮ... ➔አሀዳዊያን ተብለን የምንወዳትን አገር እንጠላ ዘንድ ማለቂያ የለሽ ግፍ የተፈጸመብን፤ ➔ "አማራ የለም" ተብሎ በሚዲያ ሲወራ የሰማን፤ ➔ዜግነትም ሆነ ማንነት የለሽ ሕዝብ መሆናችንን የሚገልጽ መጽሐፍ ተጽፎ ያነበብን፤ ➔"ሕዝብ ሳትሆኑ መንግሥት ናችሁ" በሚል የትግል ማኒፌስቶ ድምጽ የለሽ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የተፈጸመብን፤ ➔አማራን የሚያንቋሽሹና የሚያጠለሹ ሚዲያዎች ሪሲቨራችን ላይ የተጫነብን፤ ➔"አማራ ጠላት ሕዝብ ነው" ብለው የሚያምኑ ድርጅቶች ጥምረት ፈጥረው ጦርነት ያወጁብን፤ ➔ያልያዝነውን ሥልጣን እናስረክብ ዘንዳ "ዳውን ዳውን" የተባልን፤ ➔በእነ አቦይ ስብሐት አንደበት "እንዳያንሰራሩ አድርገን ሰብረናቸዋል" የሚል ጥናት የቀረበብን፤ ➔በቋንቋችን የተሳደድን፣ በማንነታችን የተጠቃን፣ በአገራዊ ፍቅራችን የተጣላን፤ ደስ የሚለው ነገር ታዲያ ይሄን ሁሉ በዴል የፈጸመብንና ጠላት ያደራጀብን አሸባሪ "አማራ ላይ የማወራርደው ሒሳብ አለኝ" በሚል እብሪት ወረራ ፈጽሞ ከእግራችን ስር መውደቁ ነው። በጎጃም፣ በጎንደር፣ በሸዋ ምድር የሚኖረው አማራም ወሎ መሬት ላይ ተሰባስቦ "አንቀጥቅጨዋለሁ" ባለው ተራራ ላይ እንደ ወባ እያንዘፈዘፈው ነው። ታዲያ ይሄን ታሪካዊ ክስ...