አእምሮ
አእምሮ
አእምሮ የሚሰራበት ሁለት ክፍሎች አሉት። አንደኛው
ንቁ (conscious) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በከፊል ንቁ
(subconscious) የሚባለው የአእምሮ ክፍል ነው።
የምናስበውና ለመጀመርያ ግዜ ለነገሮች የምነሰጠውን
ምላሽ የሚወስነው ንቁ የሚባለው ክፍል ሲሆን ያሰብናቸው
ሀሳቦችና ስሜቶች ለመጪው ጊዜ ለተመሳሳይ ነገር ምላሽ
ለመስጠት ተከማችተው የሚቀመጡት በከፊል ንቁ የሆነው
ክፍል ውስጥ ነው።
ከሚያስገርመው የአእምሮአችን ባህሪ ውስጥ በከፊል
ንቁ የሆነው ይህ የአእምሮ ክፍል የቱ ጥሩ ወይም የቱ
መጥፎ እንደሆነ አለማወቁ ነው። አንድን ሀሳብና አንድን
ነገር በንቁው የአእምሮአችን ክፍል ጥሩ ነው ብለን ካሰብን
በሚቀጥለው ጊዜ ይህ ነገር ምንም መጥፎ ነገር ቢሆን
እንኳን በከፊል ንቁ ክፍል ጥሩ ብሎ ይተረጉመዋል። ይህ
በከፊል ንቁ የሆነው የአእምሮ ክፍል በራሱ ማሰብ
የማይችል የንቁው አእምሮ ሀሳቦች ጥርቅም ነው።
ለዚህም አንዳንዴ እውሩ የአእምሮ ክፍል ተብሎም
ይጠራል። የሰው ልጅ ይላሉ ሳይንቲስቶች በቀን በአቭሬጅ
6000 ሀሳቦችን በውስጡ ያስባል። ከነዚህም 95%
የሚሆነው ሀሳብ ተደጋጋሚና አሉታዊ የሆኑ ሀሳቦችን ነው።
በከፊል ንቁ የሆነው የአእምሮ ክፍልም እንዚህን ሀሳቦች
መዝግቦ ያስቀምጣል። አንድ ሁኔታ ወይም ክስተት በንቁው
የአእምሮአችን ክፍል የሚታሰበው አንዴ ብቻ ነው። ድግሞ
ያ ክስተት ከተከሰተ አፃፋውን የሚመልሰው በከፊል ንቁ
የሆነው ክፍል ነው።ይህም የሚሆነው አውቶማትካሊ ነው።
በከፊል የሚያስበው የአእምሮ ክፍል የሚያስጨንቀው
አንድ ነገር ብቻ ነው። እሱም ንቁው የአእምሮ ክፍል ከዚህ
ቀደም ለዚህ ድርጊት ምን አይነት አፀፋ ሰጠ የሚል ነው።
ንቁው የአእምሮ ክፍል ነገሮችን ሁሌ በአሉታዊ(negative)
መንገድ ሚፈታ ከሆነ በከፊል ንቁው የሆነው ክፍል
በአሉታዊ ምላሾች ይጥለቀለቃል። እንዲ አይነት
ሰውምከፍተኛ ህይወቱ በችግር የተሞላች ትሆናለች።
አከባቢውም በአሉታዊ ነግር ይሞላል። ሁሉም ሰው አለምን
ሚያየው በዚሁ የክፊል ንቁ የአእምሮ ክፍል ነው። የሰው
ውጫዊ አለም በዚሁ የውስጥ አለም ላይ ይመሰረታል።
ለዚህም ነው አስተሳሰብ ህይወት ላይ ለውጥ ያመጣል
የሚባለው። የከፊሉ የአእምሮ ክፍል በሰውነታችን ላይ ፤
በማህበራዊ የቀን ለቀን ግንኙነት ላይ የሚጫወተው ሚና
ከፍ ያለ ነው። በኡሉታዊ ሀሳብ ከተሞላ አሉታዊ ሁኔታዎች
ተተርፈርፈው ይመጡለታል። አንዳንድ ምንም ቢሉ ምንም
ቢናገሩነገር ዞረው ዞረው ማማረር መውቀስ ማላዘን ማማት
ላይ ጊዜያቸውን የሚያጠፉ ሰዎች አይታችሁ ታውቃላችሁ?
ህይወታቸው ምን እንደሚመስል እስኪ ተመልከቱ
በእርግጠኝነት በአስቸጋሪ ሁኔታ የታሞላ ነው። እናንተም
ብትሆኑ ስለ አንድ ሰው ቀድማችሁ ውስጣቹ እስኪያምን
ድረስ ጥላቻ ካሳደራችሁ ምንም ጥሩ ቢያደርጉላችሁ እንኳን
አያስደስታችሁም። በአንፃሩ ጥሩ ብላችሁ እራሳችሁን
ያሳመናችሁት ሰዎች ደግሞ ምንም መጥፎ ቢያደርጉ እንኲን
ለመጥላት አትችሉም።
አሉታዊ ሀሳብ ይዋለዳል። ለምሳሌ አስተውላችሁ ከሆነ
ስለ አንድ ነገር በጣም ሁሌ ባማረራችሁ ቁጥር ነገሩ ጥሩ
ከመሆን ይልቅ ጭራሽ እየባሰበትና ሌላ ችግር እያመጣ
ይሄዳል። በአሉታዊነት የተሞላ የከፊል አእምሮ ባህሪ
ወይም መገልጫው ምንድነው? መገለጫው በትንሽ ነገር
ስንናደድ ነገሩን ከመተው ይልቅ ከዚህ በፊት የገጠሙንን
ችግሮችና ሆኔታዎች ጋር እያያዝን ንዴቱን አጡዘን
እናስቀጥለዋለን። ሰው ሲቀልድ ቀልዱን እንደሹፈጥ
እንቆጥራለን። ነገሮችን ከሆኑት በላይ ሌላ ነገር
እንሰጣቸዋለን።
በከፊል ንቁ የሆነው የአእምሮን ክፍል ልክ እንደ ምድር
አፈር ብንወስደው ንቁውን የአእምሮ ክፍል ደግሞ ዘር
የሚዘራው ይሆናል። ሀሳብ ደግሞ እንደ ዘር ይሆናል።
መሬት የተሰጠውን ሁሉ እንደሚያበቅል ሁሉ ንቁው
የአእምሮ ክፍል አረጋግጦ ያስተላለፈለትን ነገር ሁሉ በከፊል
የሚያስበው አእምሮ ተቀብሎ ማንነትን እና ሁኔታን
ይፈጥራል።
የሰመመን ህክምናንhypnotism )እንውሰደ።
የሰመመን ህክምና መርህ በሳይንሳዊ መንገድ በከፊል ንቁ
የሆነውን አእምሮ ክፍል አክሰሰ እንዲያደርጉ ማድረግ ነው።
ለምሳሌ ሰመመን ውስጥ ሰው መክተት በህግ
እስከተከለከለበት ጊዜ ድረስ እንደ መዝናኛ ይቆጠር ነበር።
የhypnotism ባለሞያው አንዴ ሰውን ሰመመን ውስጥ
ከከተተ ቡዕላ ሰውዬው እንዲሆንለት የሚፈልገውን ሁሉ
እንዲሆን ያደርገዋል። ዘፈን ዘፍኖ ያማያቅ ሰው ተስረቅራቂ
ድምፅ ያወጣል ፤ ተገልብጦ የማያውቅ ሰው
ይንከረባበታል። ይህ ክፍል ነኝ ብሎ ያሰባውን ሁሉ
ይሆናል። ነገር ግን ይህ በህግ ተከልክሏል። አደገኛ ነውና።
እኛም ሁሌ ሳናውቀው በአሉታዊ ሰመመን ውስጥ ከረጅም
ጊዜ ጀምሮ እራሳችንን ከተናል። ጥሩው ዜና ግን ከገባንበት
ሰመመን እራሳችንን ማላቀቅ እንደምንችል ነው። እንዴት?
በከፊል ንቁ የሆነውን የአእምሮ ክፍል እስከዛሬ ከነበረበት
ሀሳብ አላቆ ጥሩ ጥሩ ጠቃሚ የሆነ የሃሳብ ዘርን ላዮ ላይ
በመዝራት። እስከዛሬ ያሰብነው እስከዛሬ የሆነውን
አድርጎናል ፤ ከአሁን ቡዕላ የምንሆነውን
በሀሳባችንየሚያበራ የመምረጥ መብት አለን።
ምን እንፈልጋለን? ፍቅርን? ውስጣዊ ሰላምን? ጥሩ
ግንኙነትን? እንደ ፀሀይ ስብዕናን? በረከትን? እንግዲህ
ሁሉንም በከፊሉ የአእምሮ ክፍል ላይ በምንዘራው ሀሳብ
ወደፊት የምናገኘው ይሆናል። ሀሴትና ጥሩ ህይወት የምርጫ ጉዳይ ነው። መምረጥ ደግሞ ሀሳብን ነው።
ስንመርጥ ግን በሙሉ ልብ መሆን አለበት። ቁርጠኝነት ።
መልካምን ለማግኘት ሁሌ መልካም መስራትንና የማሰብን ቁርጠኝነት ይጠይቃል። ወለም ዘለም የማይል ውሳኔ።
በነገሮች ላይ የማይደግፍ ውሳኔ ያስፈልጋል። መጅመርያ አከባቢ ይከብዳል ፤ ልምድ እየሆን ሲመጣ ግን ከምንም በላይ ቀላል ነው። የሚከብደውን ጊዜ ለማለፍ መወስን ያስፈልጋል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ