ምርጥ__አባባሎችና ወርቃማ አባባሎች

ምርጥ__አባባሎች
1 አንዳንድ ሰዎች የሌሎችን ድክመት በመናገር
* * * ራሳቸውን ጠንካራ ያስመስላሉ ! * * *
2 ሰው ጉብዝናህን በሹክሹክታ ድከመትህን
በኡኡታ ያውራልና አትጨነቅ !
3 አላስተዋይ ሰው ብትችል ዝም በል ያለዚያ ግን
ያንተን ማንነት ከጀርባህ ሸሽገህ ስለ ሰው
አታውራ !
4 በስንዴው ማሳ ላይ እራሳቸውን ከፍ ከፍ ያደረጉ
ሁሉ እንክርዳዶች ናቸውና ራስክን አቀርቅር !
5 ምንም ቢሉህ ደካማ አስተሳሰብ ያለው ሰው
እዘንለት እንጂ አትዘንበት ምክንያቱም
የሚያስበው የሚያቀውን ያህል ነው ! እሱን
በመጥላት የምታባክነው ጊዜ
ራስህን ውደድበት !. !
6 በራስ መተማመን ማለት ሌሎች ሲቀልዱብህ
እና ሲያሾፉብህ በዝምታ ማለፍ ነው !
ለምን... ? ... ብትል ...
አንተ ማን እንደሆንክ እና እነሱ ማን እንደሆኑ
ጠንቅቀህ ስለምታውቅ ነው ፡፡
7 ከአንተ ጀርባ ሆነው ስለሚያወሩ ሰዎች አትጨነቅ
እነሱ የራሳቸውን የህይወት መንገድ መስመር
ተስኗቸው ?
የአንተን ስህተት በመፈለግ የተጠመዱ ናቸው ፡፡
ስለ እነሱ አትጨነቅ ምክንያቱም አንተ ሰዎች
ምን ይሉኛል ብለህ የምትጨነቅ ከሆነ የሰዎች
እስረኛ ነህ !
8 ስራህ ከበረዶ 10ሺ የነጣ ቢሆንም ከሰው ትችት
አታመልጥምና ለሰው ወሬ ጆሮ አትስጥ ! ! "
አንተ እንደገባህ እንጅ ሰዎች እንደ ተረዱህ
አትኑር ?
ከአንተ በላይ ስለ አንተ የሚያውቅ ማንም
የለምና !
9 ሰው ከትልቅ ደግነት ይልቅ ትንሿን ስህተትህ
የያል
የሰው ፍፁም ስለሌለ አትጨነቅ ! ! !
ለህሊናህ ስትል ታመን መልካም አድርግ ጥሩ
ስራ ?
ከህሊናህ በላይአለቃ የለምና !
10 ትክክለኛ_ሰው_ከሆኑ ፦ • • • ?
ማንንም አይተቹ ትችት የሰዎችን ሞሯል ዝቅ
ያደርጋል
የበረታን ሰው ማበርታታት የነፍስ ኦክስጅን
መስጠት ነው !
ሞሯል ሰውን ከፍ ና ጠንካራ የሚያደርግ
መሰላል ነው !
#
11 ስህተት_ፈላጊ_አይሁኑ ፦ • • • ?
ከነገሮች ሁሉ ርካሽ ና ቀላል ስራ
የሰውን ስህተት ብቻ እየተከታተሉ ማውጣት
ነው !
በዚህ ምድር ላይ የሌላውን ድክመት ለማውቅ
ከመፈጠር ና ከመጣር የበለጠ ትልቅ ድክመት
የለም
12 ሳይታክቱ_ፍቅርን_ይስጡ ፦ • • • ?
⇄ለጠላትዎ ይቅርታን ያስበልጡ
⇄ለተቃዋሚዎ ፅናትን ያበርክቱ
⇄ለጓደኛዎ ሐሳብዎን ያወያዩ
⇄ለሚቀርብዎ ደግነትን ያሳዩ
13 ለሰው _ _ _ _ ሁሉ _ _ _ _ ጥሩነትን ይለግሱ
ሳይተቹ ይበርቱ ሰዎችን ያሞግሱ
መልካምነትን ይላበሱ ! ! !,
14 በህይወታችን ደግነትን እናብዛ,,,,,,,,,,,

ወርቃማ አባባሎች
~~~~~
ከልምዶች ሁሉ ጎጂ ጭንቀት!
የሚያኮራ ስራ. ሰወችን መርዳት
አስቀያሚ ባህሪ. ራስ ወዳድነት
መጥፎ ልማድ መስረቅ
ትልቅ የተፈጥሮ ሀብት=ወጣትነት
ትልቅ መሳሪያ = ብርታት
መጥፎ ፀባይ = ይሉኝታ
ቆንጆ ጌጥ =ፈገግታ
አደገኛ ስብከት አሉባልታ
ትልቅ ስጦታ =ምክር
የሰዉ ልጅ እንቆቅልሽ =ኑሮ
አደገኛ መሳርያ= ምላስ
ራስን የመጉዳት ዘዴ = ማልቀስ
በሀይል የተሞላ ቃል = እችላለሁ
ታላቅ ተስፋ = እኖራለሁ
ዉድ ሀብት እምነት
ሀይለኛ የመገናኛ መሳርያ=ፀሎት
ልንፈታዉ የሚገባን ችግር = ፍርሀት
ዉጤታማ የእንቅልፍ ክኒን =የአእምሮ እረፍት
መጥፎ የዉድቀት በሽታ =ከስህተት ይቅርታን
አለመጠየቅ
የህይወት ሀይለኛ ጉልበት = አእምሮ
ከህይወት ልምዶች የምድር ታላቅ ደስታ
መስጠት
⚂ወዳጀ ሆይ⚂
ትላንት ታሪክ ነዉና ተርከዉ
ዛሬ ቁምነገር ነዉና ተጠቀምበት
ነገ ምስጢር ነዉና ድረስበት
ለመነሳት ከፈለክ መዉደቅህን አምነህ ተቀበል★

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)