የኢትዮጵያ ጦር

የኢትዮጵያ ወታደሮች ሕይወት እንቆቅልሽ ጨዋታ ።
የዚያድባሬ እብሪት ።
ብኢኮ (ሜቴክ)ከሰራው እጅግ የመረረ በደል እነሆ ።
""""""""""""""""""""""""""""""""""""twitter.com/ambachew123
እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ የታሪክ ባላንጋራ ከሆኑ እነሆ 45 ዓመታት ሆናቸው ።
በመንግሥቱ ሀይለማሪያም ዘመነ መንግሥት ጣልያን እና እንግሊዝን የጀርባ አጥንት
( back bone of the war) በማድረግ ኢትዮጵያን በመውረር የግዛት አድማሷን
በማስፋፋት ኦጋዴን እና አዋሽ መፋሰሻን እስከ ናዝሬት የመጠቅለል እቅድ ይዛ ተነሳች ።
በቅጡ መንበሩን ያላስተካከለው የመንግሥቱ ሀይለማሪያም ወታደራዊ የሽግግር
መንግሥት አስር ሺህ ወታደር የማይሞሉ ወታደሮች ወቅቱ ነበረው ። በአንፃሩ ሱማሊያ
በድብቅ ለብዙ ዓመታት ያሰለጠነቻቸው እና በሚገባ የታጠቀ የነቃ የበቃ ድፍን ሁለት መቶ
ሃምሳ ሺህ ወታደሮች ወታደሮችን አሰልፋ ኢትዮጵያን ወረረች ። ኢትዮጵያን አንድም በድሮ
ቂም በቀል ሁለትም በምንከተለው ርዕዮተ ዓለም የሶሻሊዝም አቀንቃኝነቱ ሦስትም
የነበረንን የገናና እና የስትራቴጂ ቦታ ለመቀራመት ሶማሊያን በመጠቀም ወረራውን ድንገት
የጦርነት ማብሰሪያ ጥይቷን ወደላይ በመተኮስ አስጀመረች። ደርግ በአንፃሩ በውስጥ
የነበረውን የጠራ አቋም እና ተቃዋሚ ድርጅቶች መፍትሔ ያልሰጠበት ጊዜ በመሆኑ ጦርነቱ
ለሶማሊያ ድል ያለ አጋጣሚ ነበር ። ሆኖም ግን አያሌ አርበኞች ገበሬዎች እና እነ
ሶሻሊስቶችን በመጠቀም ጦርነቱ በእልህ አስጨራሽ ወኔ ብቻ የናዝሬቱ ድንበር እቅድ
ካራማራን ተሻግሮ ኦጋዴን ነፃ ወጥቶ ጅጅጋ ፣ ቀብሪደሃር ፣ ቀብሪበያ ፣ ቶጎውጫሌ ፣ተፈሪ
በር፣ ተሻግሮ አፈር ደም ጠጥቶ ዳግም እንዳይነሳ ሆኖ ለዘለዓለም በርበራ ወደብ ላይ
ተቀበረ።
ዘመነ ሕወሓት የፈጠራቸው የእንቆቅልሽ የሆነው አልሻባብ የሃሳብ አሸባሪ እንጂ ለአፍታም
የማይታይ መሆኑ ጨዋታው እዚህ ላይ ነው ። የኢትጵያ ጦር በዘመነ ኢህአዴግ ሱማሊያ
ከገባ እነሆ አሥራ ምናምን ዓመታት ሆነው ።
ጉዳዩ ወዲህ ነው ። ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የሚጣልላትን ዶላር ለማግኘት አልሻባብ
የሚባለው የሃሳብ አሸባሪ መኖር አለበት ። መጥፋትም የለበትም ። ለዚህም ያመች ዘንድ
ሜቴክ የሚከተለውን አደረገ።
ለሶማሊያ በበሰበሱ እና ከጥቅም ውጭ መሆን ከነበረባቸው ሁለት መርከቦች አባይ እና
አንድነት የሚባሉትን የሌላ ሀገር ሰንደቅ በመጠቀም ለሶማሊያ መሣሪያ ማቅረብ ነበረበት
። ምክንያቱም አልሻባብ በመሳሪያ እጥረት ሊጠፋ ይችላል እና ። ከኢራን መሣሪያ እየጫኑ
ለሶማሊያው አልሻባብን በመጠኑ ማጠናከር እና ከኢትዮጵያ ምስኪን ወታደሮች ጋር ጦርነት
ማስገባት ድብቅ ዓላማ ነበር ።
በዚህም እስከ አሁን ድረስ መክሰም እና መጥፋት የነበረበት አልሻባብ ፣ አሊትሀድ እና
የመሳሰሉ አሸባሪ ተብዬ ድርጅቶች በጎን በምስጢር የሚደግፉ ለፖለቲካ ፍጆታ የሚውሉ
ዳሩ ግን ወንድሞቻችን ባላወቁት ነገር ደማቸውን አፍስሰው ነፍሳቸውን እየገበሩ ያለቁት
ሳይታወቅ የቆሰሉት ሳይቆጠሩ የገባውን የሠራዊት መጠን እየቆጠሩ እየነገሩን አለን
እንዳለን ። ሜቴክ እና ስውር የጦር መሣሪያ ንግዱ ።ይሄ አንድ ቅንጣት ታሪክ እንጂ ቀሪ
የበደል እና የሀገር ክህደት ልኩን በገዛ ሕወሓታዊ አንባገነን ጄኔራሎች በገዙት መሣሪያ
የሞቱት ወታደር ወንድሞቻችን ቤት ይቁጠረው ፣
መሣሪያ በጎን ለአልሸባብ እየቸበቸቡ ወገንን መጨረስ የክህደት ሁሉ ክህደት ታሪክ
የሚወጣው ሃቅ ይሆናል ።
የተቀበረው እና አብጦ የፈነዳው ዚያድባሬ በየት ይነሳ እና ????

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

አይሰው

እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ)